۞ سَيَقُولُ ٱلسُّفَهَآءُ مِنَ ٱلنَّاسِ مَا وَلَّىٰهُمۡ عَن قِبۡلَتِهِمُ ٱلَّتِي كَانُواْ عَلَيۡهَاۚ قُل لِّلَّهِ ٱلۡمَشۡرِقُ وَٱلۡمَغۡرِبُۚ يَهۡدِي مَن يَشَآءُ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ
142. ቂል የህብረተሰብ ክፍሎች «ከዚያች ከነበሩባት ቂብላቸው (አቅጣጫቻቸው) ምን አዞራቸው?» ይላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ምስራቁም ምዕራቡም የአላህ ነው:: የሻውንም ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል።» በላቸው።
التفاسير: