ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - أكاديمية أفريقيا

رقم الصفحة:close

external-link copy
98 : 11

يَقۡدُمُ قَوۡمَهُۥ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ فَأَوۡرَدَهُمُ ٱلنَّارَۖ وَبِئۡسَ ٱلۡوِرۡدُ ٱلۡمَوۡرُودُ

በትንሳኤ ቀን ህዝቦቹን ይቀድማል፡፡ ከዚያም ወደ አሳት ያወርዳቸዋል፡፡ የሚገቡትም አገባብ ምንኛ ከፋ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
99 : 11

وَأُتۡبِعُواْ فِي هَٰذِهِۦ لَعۡنَةٗ وَيَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۚ بِئۡسَ ٱلرِّفۡدُ ٱلۡمَرۡفُودُ

99. በዚችም በቅርቢቱ ዓለም እርግማንን አስከተልናቸው:: በትንሳኤም ቀን እንደዚሁ። የተሰጡት ስጦታ ምንኛ ከፋ! info
التفاسير:

external-link copy
100 : 11

ذَٰلِكَ مِنۡ أَنۢبَآءِ ٱلۡقُرَىٰ نَقُصُّهُۥ عَلَيۡكَۖ مِنۡهَا قَآئِمٞ وَحَصِيدٞ

100. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ከላይ የተነገረው ከከተሞቹ ወሬዎች የተወሰነው ነው:: ባንተ ላይ እንተርከዋለን:: ከእርሷ ቋሚና እጭድም የሆነ አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
101 : 11

وَمَا ظَلَمۡنَٰهُمۡ وَلَٰكِن ظَلَمُوٓاْ أَنفُسَهُمۡۖ فَمَآ أَغۡنَتۡ عَنۡهُمۡ ءَالِهَتُهُمُ ٱلَّتِي يَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مِن شَيۡءٖ لَّمَّا جَآءَ أَمۡرُ رَبِّكَۖ وَمَا زَادُوهُمۡ غَيۡرَ تَتۡبِيبٖ

101. እኛም አልበደልናቸዉም:: ግን ነፍሶቻቸውን በደሉ:: የጌታህ ጉዳይ በመጣ ጊዜ እነዚያ ከአላህ ሌላ የሚገዟቸው አማልክቶቻቸው ሁሉ በምንም አላዳኗቸዉም:: ከማክሰርም በስተቀር ምንም አልጨመሩላቸዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
102 : 11

وَكَذَٰلِكَ أَخۡذُ رَبِّكَ إِذَآ أَخَذَ ٱلۡقُرَىٰ وَهِيَ ظَٰلِمَةٌۚ إِنَّ أَخۡذَهُۥٓ أَلِيمٞ شَدِيدٌ

102. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህ ቅጣት የከተሞችን ሰዎች በዳዮች ሲሆኑ በቀጣቸው ጊዜ ልክ እንደዚህ ነው:: ቅጣቱ በእርግጥ አሳማሚና ብርቱ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
103 : 11

إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗ لِّمَنۡ خَافَ عَذَابَ ٱلۡأٓخِرَةِۚ ذَٰلِكَ يَوۡمٞ مَّجۡمُوعٞ لَّهُ ٱلنَّاسُ وَذَٰلِكَ يَوۡمٞ مَّشۡهُودٞ

103. በዚህ ውስጥ የመጨረሻውን ቀን ቅጣት ለሚፈሩ ሁሉ መገሰጫ አለ:: ይህ የትንሳኤ ቀን ሰዎች በእርሱ የሚሰበሰቡበት ቀን ነው:: ይህ የሚጣዱት ቀን ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
104 : 11

وَمَا نُؤَخِّرُهُۥٓ إِلَّا لِأَجَلٖ مَّعۡدُودٖ

104. ይህንን ቀን ለተቆጠረም (ለተወሰነ) ጊዜ እንጂ አናቆየዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
105 : 11

يَوۡمَ يَأۡتِ لَا تَكَلَّمُ نَفۡسٌ إِلَّا بِإِذۡنِهِۦۚ فَمِنۡهُمۡ شَقِيّٞ وَسَعِيدٞ

105. በሚመጣ ቀን ማንኛዉም ነፍስ በእርሱ ፈቃድ ቢሆን እንጂ አትናገርም:: ከእነርሱም መናጢም (እድለቢስ) እድለኛም አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
106 : 11

فَأَمَّا ٱلَّذِينَ شَقُواْ فَفِي ٱلنَّارِ لَهُمۡ فِيهَا زَفِيرٞ وَشَهِيقٌ

106. እነዚያ ያመጹትማ በእሳት ውስጥ ናቸው:: ለእነርሱ በእርሷ ውስጥ ማናፋትና መንሰቅሰቅ አላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
107 : 11

خَٰلِدِينَ فِيهَا مَا دَامَتِ ٱلسَّمَٰوَٰتُ وَٱلۡأَرۡضُ إِلَّا مَا شَآءَ رَبُّكَۚ إِنَّ رَبَّكَ فَعَّالٞ لِّمَا يُرِيدُ

107. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ከፈለገው በስተቀር ሰማያትና ምድር እስከዘወተሩ ድረስ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲሆኑ በእሳት ውስጥ ይኖራሉ:: ጌታህ የሚፈልገውን ሠሪ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
108 : 11

۞ وَأَمَّا ٱلَّذِينَ سُعِدُواْ فَفِي ٱلۡجَنَّةِ خَٰلِدِينَ فِيهَا مَا دَامَتِ ٱلسَّمَٰوَٰتُ وَٱلۡأَرۡضُ إِلَّا مَا شَآءَ رَبُّكَۖ عَطَآءً غَيۡرَ مَجۡذُوذٖ

108. እነዚያ እድለኞቹማ ጌታ ከሻው በስተቀር ሰማያትና ምድር እስከ ዘወተሩ ድረስ በውስጧ ዘውታሪዎች ሆነው በገነት ውስጥ ይኖራሉ:: የማያቋርጥ ስጦታን ተሰጡ:: info
التفاسير: