ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - محمد صادق

سورة الطلاق - አጥ ጠላቅ

external-link copy
1 : 65

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ إِذَا طَلَّقۡتُمُ ٱلنِّسَآءَ فَطَلِّقُوهُنَّ لِعِدَّتِهِنَّ وَأَحۡصُواْ ٱلۡعِدَّةَۖ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ رَبَّكُمۡۖ لَا تُخۡرِجُوهُنَّ مِنۢ بُيُوتِهِنَّ وَلَا يَخۡرُجۡنَ إِلَّآ أَن يَأۡتِينَ بِفَٰحِشَةٖ مُّبَيِّنَةٖۚ وَتِلۡكَ حُدُودُ ٱللَّهِۚ وَمَن يَتَعَدَّ حُدُودَ ٱللَّهِ فَقَدۡ ظَلَمَ نَفۡسَهُۥۚ لَا تَدۡرِي لَعَلَّ ٱللَّهَ يُحۡدِثُ بَعۡدَ ذَٰلِكَ أَمۡرٗا

አንተ ነቢዩ ሆይ! ሴቶችን መፍታት ባሰባችሁ ጊዜ፤ ለዒዳቸው ፍቱዋቸው፡፡ ዒዳንም ቁጠሩ፡፡ አላህንም ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ግልጽ የኾነችን ጠያፍ ካልሠሩ በስተቀር ከቤቶቻቸው አታውጡዋቸው፤ አይውጡም፡፡ ይህችም የአላህ ሕግጋት ናት፡፡ የአላህንም ሕግጋት የተላለፈ ሰው በእርግጥ ነፍሱን በደለ፡፡ ከዚህ (ፍች) በኋላ አላህ (የመማለስ) ነገርን ምናልባት ያመጣ እንደኾነ አታውቅም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 65

فَإِذَا بَلَغۡنَ أَجَلَهُنَّ فَأَمۡسِكُوهُنَّ بِمَعۡرُوفٍ أَوۡ فَارِقُوهُنَّ بِمَعۡرُوفٖ وَأَشۡهِدُواْ ذَوَيۡ عَدۡلٖ مِّنكُمۡ وَأَقِيمُواْ ٱلشَّهَٰدَةَ لِلَّهِۚ ذَٰلِكُمۡ يُوعَظُ بِهِۦ مَن كَانَ يُؤۡمِنُ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِۚ وَمَن يَتَّقِ ٱللَّهَ يَجۡعَل لَّهُۥ مَخۡرَجٗا

ጊዜያቸውንም ለመዳረስ በተቃረቡ ጊዜ በመልካም ያዙዋቸው፡፡ ወይም በመልካም ተለያዩዋቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶችን አስመስክሩ፡፡ ምስክርነትንም ለአላህ አስተካክሉ፡፡ ይህ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የኾነ ሰው ሁሉ በእርሱ ይገሰጽበታል፡፡ አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 65

وَيَرۡزُقۡهُ مِنۡ حَيۡثُ لَا يَحۡتَسِبُۚ وَمَن يَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱللَّهِ فَهُوَ حَسۡبُهُۥٓۚ إِنَّ ٱللَّهَ بَٰلِغُ أَمۡرِهِۦۚ قَدۡ جَعَلَ ٱللَّهُ لِكُلِّ شَيۡءٖ قَدۡرٗا

ከማያስበውም በኩል ሲሳየን ይሰጠዋል፡፡ በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው፡፡ አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው፡፡ አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን በእርግጥ አድርጓል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 65

وَٱلَّٰٓـِٔي يَئِسۡنَ مِنَ ٱلۡمَحِيضِ مِن نِّسَآئِكُمۡ إِنِ ٱرۡتَبۡتُمۡ فَعِدَّتُهُنَّ ثَلَٰثَةُ أَشۡهُرٖ وَٱلَّٰٓـِٔي لَمۡ يَحِضۡنَۚ وَأُوْلَٰتُ ٱلۡأَحۡمَالِ أَجَلُهُنَّ أَن يَضَعۡنَ حَمۡلَهُنَّۚ وَمَن يَتَّقِ ٱللَّهَ يَجۡعَل لَّهُۥ مِنۡ أَمۡرِهِۦ يُسۡرٗا

እኒያም ከሴቶቻቸው ከአደፍ ያቋረጡት (በዒዳቸው ሕግ) ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሦስት ወር ነው፡፡ እኒያም ገና አደፍን ያላዩት (ዒዳቸው እንደዚሁ ነው)፡፡ የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው እርጉዛቸውን መውለድ ነው፡፡ አላህንም የሚፈራ ሰው ከነገሩ ሁሉ ለርሱ መግራትን ያደርግለታል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 65

ذَٰلِكَ أَمۡرُ ٱللَّهِ أَنزَلَهُۥٓ إِلَيۡكُمۡۚ وَمَن يَتَّقِ ٱللَّهَ يُكَفِّرۡ عَنۡهُ سَيِّـَٔاتِهِۦ وَيُعۡظِمۡ لَهُۥٓ أَجۡرًا

ይህ የአላህ ፍርድ ነው፡፡ ወደእናንተ አወረደው፡፡ አላህንም የሚፈራ ሰው ኀጢኣቶቹን ከእርሱ ይሰርይለታል፡፡ ምንዳንም ለእርሱ ያተልቅለታል፡፡ info
التفاسير: