ترجمة معاني القرآن الكريم - الترجمة الأمهرية - محمد صادق

رقم الصفحة:close

external-link copy
62 : 3

إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلۡقَصَصُ ٱلۡحَقُّۚ وَمَا مِنۡ إِلَٰهٍ إِلَّا ٱللَّهُۚ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ

ይህ እርሱ በእርግጥ እውነተኛ ታሪክ ነው፡፡ አምላክም ከአላህ በስተቀር ምንም የለም፡፡ አላህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
63 : 3

فَإِن تَوَلَّوۡاْ فَإِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمُۢ بِٱلۡمُفۡسِدِينَ

(ከማመን) እንቢ ቢሉም አላህ አጥፊዎቹን በእርግጥ ዐዋቂ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
64 : 3

قُلۡ يَٰٓأَهۡلَ ٱلۡكِتَٰبِ تَعَالَوۡاْ إِلَىٰ كَلِمَةٖ سَوَآءِۭ بَيۡنَنَا وَبَيۡنَكُمۡ أَلَّا نَعۡبُدَ إِلَّا ٱللَّهَ وَلَا نُشۡرِكَ بِهِۦ شَيۡـٔٗا وَلَا يَتَّخِذَ بَعۡضُنَا بَعۡضًا أَرۡبَابٗا مِّن دُونِ ٱللَّهِۚ فَإِن تَوَلَّوۡاْ فَقُولُواْ ٱشۡهَدُواْ بِأَنَّا مُسۡلِمُونَ

የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ (እርሷም) አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤ በላቸው፡፡ እምቢ ቢሉም፡- እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
65 : 3

يَٰٓأَهۡلَ ٱلۡكِتَٰبِ لِمَ تُحَآجُّونَ فِيٓ إِبۡرَٰهِيمَ وَمَآ أُنزِلَتِ ٱلتَّوۡرَىٰةُ وَٱلۡإِنجِيلُ إِلَّا مِنۢ بَعۡدِهِۦٓۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ

እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በኢብራሂም ለምን ትከራከራላችሁ ተውራትና ኢንጂልም ከርሱ በኋላ እንጅ አልተወረዱም፡፡ ልብ አታደርጉምን በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
66 : 3

هَٰٓأَنتُمۡ هَٰٓؤُلَآءِ حَٰجَجۡتُمۡ فِيمَا لَكُم بِهِۦ عِلۡمٞ فَلِمَ تُحَآجُّونَ فِيمَا لَيۡسَ لَكُم بِهِۦ عِلۡمٞۚ وَٱللَّهُ يَعۡلَمُ وَأَنتُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ

ንቁ! እናንተ እነዚያ ለእናንተ በርሱ ዕውቀት ባላችሁ ነገር የተከራከራችሁ ናችሁ፡፡ ታዲያ ለእናንተ በርሱ ዕውቀት በሌላችሁ ነገር ለምን ትከራከራላችሁ አላህም ያውቃል፡፡ እናንተ ግን አታውቁም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
67 : 3

مَا كَانَ إِبۡرَٰهِيمُ يَهُودِيّٗا وَلَا نَصۡرَانِيّٗا وَلَٰكِن كَانَ حَنِيفٗا مُّسۡلِمٗا وَمَا كَانَ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ

ኢብራሂም ይሁዳዊም ክርስቲያንም አልነበረም፡፡ ግን ወደ ቀጥተኛው ሃይማኖት የተዘነበለ ሙስሊም ነበረ፡፡ ከአጋሪዎችም አልነበረም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
68 : 3

إِنَّ أَوۡلَى ٱلنَّاسِ بِإِبۡرَٰهِيمَ لَلَّذِينَ ٱتَّبَعُوهُ وَهَٰذَا ٱلنَّبِيُّ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْۗ وَٱللَّهُ وَلِيُّ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

ከሰው ሁሉ በኢብራሂም ተገቢዎቹ እነዚያ የተከተሉትና ይህ ነቢይ እነዚያም ያመኑት ናቸው፡፡ አላህም የምእምናን ረዳት ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
69 : 3

وَدَّت طَّآئِفَةٞ مِّنۡ أَهۡلِ ٱلۡكِتَٰبِ لَوۡ يُضِلُّونَكُمۡ وَمَا يُضِلُّونَ إِلَّآ أَنفُسَهُمۡ وَمَا يَشۡعُرُونَ

ከመጽሐፉ ባለቤቶች የኾኑ ጭፍሮች ነፍሶቻቸውን እንጂ የማያሳስቱ ሲኾኑ ሊያሳስቱዋችሁ ተመኙ ግን አያውቁም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
70 : 3

يَٰٓأَهۡلَ ٱلۡكِتَٰبِ لِمَ تَكۡفُرُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَأَنتُمۡ تَشۡهَدُونَ

የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ በአላህ አንቀጾች ለምን ትክዳላችሁ info
التفاسير: