《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。

页码:close

external-link copy
96 : 7

وَلَوۡ أَنَّ أَهۡلَ ٱلۡقُرَىٰٓ ءَامَنُواْ وَٱتَّقَوۡاْ لَفَتَحۡنَا عَلَيۡهِم بَرَكَٰتٖ مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِ وَلَٰكِن كَذَّبُواْ فَأَخَذۡنَٰهُم بِمَا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ

96. የከተሞቹ (ሰዎችም) በትክክል ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ በእነርሱ ላይ ከሰማይና ከምድር በረከቶችን በከፈትንላቸው ነበር:: ግን አስተባበሉ:: ይሠሩት በነበሩትም ኃጢአት ምክኒያት ቀጣናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
97 : 7

أَفَأَمِنَ أَهۡلُ ٱلۡقُرَىٰٓ أَن يَأۡتِيَهُم بَأۡسُنَا بَيَٰتٗا وَهُمۡ نَآئِمُونَ

97. የከተሞቹ (ሰዎች) የተኙ ሆነው ቅጣታችን ሌሊት ሊመጣባቸው አይፈሩምን? info
التفاسير:

external-link copy
98 : 7

أَوَأَمِنَ أَهۡلُ ٱلۡقُرَىٰٓ أَن يَأۡتِيَهُم بَأۡسُنَا ضُحٗى وَهُمۡ يَلۡعَبُونَ

98. የከተሞቹ ሰዎችም የሚጫወቱ ሆነው ሳሉ ቅጣታችን ቀን በረፋዱ ሊመጣባቸው አይፈሩምን? info
التفاسير:

external-link copy
99 : 7

أَفَأَمِنُواْ مَكۡرَ ٱللَّهِۚ فَلَا يَأۡمَنُ مَكۡرَ ٱللَّهِ إِلَّا ٱلۡقَوۡمُ ٱلۡخَٰسِرُونَ

99. የአላህን ማዘናጋት አይፈሩምን? ተማመኑን? የአላህን ማዘናጋት ከከሳሪዎች ሕዝቦች በስተቀር ማንም የሚተማመን የለም:: info
التفاسير:

external-link copy
100 : 7

أَوَلَمۡ يَهۡدِ لِلَّذِينَ يَرِثُونَ ٱلۡأَرۡضَ مِنۢ بَعۡدِ أَهۡلِهَآ أَن لَّوۡ نَشَآءُ أَصَبۡنَٰهُم بِذُنُوبِهِمۡۚ وَنَطۡبَعُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ فَهُمۡ لَا يَسۡمَعُونَ

100. ለእነዚያ ምድርን ከባለቤቶቿ ጥፋት በኋላ ለሚወርሱት ብንሻ ኖሮ በኃጢአቶቻቸው ምክኒያት የምንቀጣቸው መሆናችን አልተገለጸላቸዉምን? በልቦቻቸውም ላይ እናትማለን:: ስለዚህም እነርሱ አይሰሙም:: info
التفاسير:

external-link copy
101 : 7

تِلۡكَ ٱلۡقُرَىٰ نَقُصُّ عَلَيۡكَ مِنۡ أَنۢبَآئِهَاۚ وَلَقَدۡ جَآءَتۡهُمۡ رُسُلُهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ فَمَا كَانُواْ لِيُؤۡمِنُواْ بِمَا كَذَّبُواْ مِن قَبۡلُۚ كَذَٰلِكَ يَطۡبَعُ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِ ٱلۡكَٰفِرِينَ

101. እነዚህ ከተሞች ከወሬዎቻቸው ባንተ ላይ እንተርካለን:: መልዕክተኞቻቸዉም በግልጽ ተዓምራት መጥተውላቸዋል:: ከመምጣታቸው በፊት ባስተባበሉትም ነገር የሚያምኑ አልሆነም:: ልክ እንደዚሁ አላህ በከሓዲያን ልቦች ላይ ያትማል:: info
التفاسير:

external-link copy
102 : 7

وَمَا وَجَدۡنَا لِأَكۡثَرِهِم مِّنۡ عَهۡدٖۖ وَإِن وَجَدۡنَآ أَكۡثَرَهُمۡ لَفَٰسِقِينَ

102. ለብዙዎቻቸው በቃል ኪዳናቸው መሙላትን አላገኘንም:: ይልቁንም አብዛኞቻቸውን አመጸኞች ሆነው አገኘናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
103 : 7

ثُمَّ بَعَثۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِم مُّوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَآ إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ وَمَلَإِيْهِۦ فَظَلَمُواْ بِهَاۖ فَٱنظُرۡ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُفۡسِدِينَ

103. ከዚያም ከበኋላቸው ነብዩ ሙሳን ወደ ፈርዖንና ወደ መማክርቶቹ ተዓምራታችንን አስይዘን ላክነው:: በእርሷም ካዱ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የአጥፊዎች መጨረሻ እንዴት እንደነበረ እስቲ ተመልከት:: info
التفاسير:

external-link copy
104 : 7

وَقَالَ مُوسَىٰ يَٰفِرۡعَوۡنُ إِنِّي رَسُولٞ مِّن رَّبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

104. ሙሳም አለ፡- «ፈርዖን! ሆይ እኔ ከዓለማት ጌታ የተላኩ መልክተኛ ነኝ? info
التفاسير: