《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。

external-link copy
273 : 2

لِلۡفُقَرَآءِ ٱلَّذِينَ أُحۡصِرُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ لَا يَسۡتَطِيعُونَ ضَرۡبٗا فِي ٱلۡأَرۡضِ يَحۡسَبُهُمُ ٱلۡجَاهِلُ أَغۡنِيَآءَ مِنَ ٱلتَّعَفُّفِ تَعۡرِفُهُم بِسِيمَٰهُمۡ لَا يَسۡـَٔلُونَ ٱلنَّاسَ إِلۡحَافٗاۗ وَمَا تُنفِقُواْ مِنۡ خَيۡرٖ فَإِنَّ ٱللَّهَ بِهِۦ عَلِيمٌ

273. (ምጽዋት የምትሰጡት ዘካና ልገሳ) ለእነዚያ በአላህ መንገድ በግል ሕይወታቸው ከመንቀሳቀስ (ለታገዱት) ፋታ ላጡ ድሆች ነው:: መሬት ውስጥ መጓዝ (ልመና) አይችሉም:: ከቁጥብነታቸው የተነሳ ውስጣቸውን የማያውቅ ሰው ሁሉ ሀብታሞች ናቸው ብሎ ይገምታቸዋል:: በምልክታቸው ታውቃቸዋለህ:: ሰዎችን በችክታ አይለምኑም:: ከገንዘብም የምትለግሱትን ሁሉ አላህ ሁሉን አዋቂ ነው፡፡ info
التفاسير: