《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。

页码:close

external-link copy
6 : 2

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ سَوَآءٌ عَلَيۡهِمۡ ءَأَنذَرۡتَهُمۡ أَمۡ لَمۡ تُنذِرۡهُمۡ لَا يُؤۡمِنُونَ

6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ (በአላህ ፤ በአንተ መልዕክተኛነትና በአላህ አናቅጽ) የካዱት ሰዎች ብታስጠነቅቃቸዉም ባታስጠነቅቃቸዉም ለእነርሱ ሁሉም እኩል ነው:: (ምንም ለውጥ አያመጣም) አያምኑምና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
7 : 2

خَتَمَ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمۡ وَعَلَىٰ سَمۡعِهِمۡۖ وَعَلَىٰٓ أَبۡصَٰرِهِمۡ غِشَٰوَةٞۖ وَلَهُمۡ عَذَابٌ عَظِيمٞ

7. አላህ እነዚያ እውነትን እያወቁ የካዱ ሰዎችን በልቦቻቸው እና በመስሚያቸው ላይ አትሞባቸዋል:: በዓይኖቻቸው ላይም መሸፈኛ አለ:: ለእነርሱም በጀሀነም ውስጥ ከባድ ቅጣት አለባቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
8 : 2

وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَقُولُ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَبِٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِ وَمَا هُم بِمُؤۡمِنِينَ

8. ከሰዎች መካከል ለይስሙላ «በአላህና በመጨረሻው ቀን አምነናል» የሚሉ ክፍሎች አሉ:: እነርሱ ግን (የሚዋሹ እንጂ) ትክክለኛ አማኞች አይደሉም። info
التفاسير:

external-link copy
9 : 2

يُخَٰدِعُونَ ٱللَّهَ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَمَا يَخۡدَعُونَ إِلَّآ أَنفُسَهُمۡ وَمَا يَشۡعُرُونَ

9. አላህንና እነዚያን በትክክል በአላህ ያመኑትን ሰዎች ያታልላሉ:: ነገር ግን በዚህ ተግባራቸው ነፍሶቻቸውን እንጂ ሌላን ማንንም አያታልሉም:: እነርሱ ግን ይህ መሆኑን በትክክል አያውቁም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
10 : 2

فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٞ فَزَادَهُمُ ٱللَّهُ مَرَضٗاۖ وَلَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمُۢ بِمَا كَانُواْ يَكۡذِبُونَ

10. በልቦቻቸው ውስጥ (የንፍቅና) በሽታ ሰርጿል:: አላህም ሌላን በሽታ ጨመረባቸው:: ለእነርሱም ይዋሹ በነበሩበት ምክንያት አሳማሚ ቅጣት አለባቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
11 : 2

وَإِذَا قِيلَ لَهُمۡ لَا تُفۡسِدُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ قَالُوٓاْ إِنَّمَا نَحۡنُ مُصۡلِحُونَ

11. በምድር ላይ ሁከትን አትፍጠሩ በተባሉ ጊዜ እኛ እኮ አስተካካዮች ነን ይላሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
12 : 2

أَلَآ إِنَّهُمۡ هُمُ ٱلۡمُفۡسِدُونَ وَلَٰكِن لَّا يَشۡعُرُونَ

12. (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ:: አጥፊዎች እነርሱ ብቻ ናቸው:: ግን እነርሱ ይህንን አይገነዘቡም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
13 : 2

وَإِذَا قِيلَ لَهُمۡ ءَامِنُواْ كَمَآ ءَامَنَ ٱلنَّاسُ قَالُوٓاْ أَنُؤۡمِنُ كَمَآ ءَامَنَ ٱلسُّفَهَآءُۗ أَلَآ إِنَّهُمۡ هُمُ ٱلسُّفَهَآءُ وَلَٰكِن لَّا يَعۡلَمُونَ

 13, «ሰዎቹ እንዳመኑት ሁሉ እናንተም እመኑ» በተባሉ ጊዜ «ቂሎቹ እንዳመኑት እናምናለንን?» ይላሉ። (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተዉሉ። ቂሎቹ እነርሱ ብቻ ናቸው:: እነርሱ ግን ይህንን አያውቁም። info
التفاسير:

external-link copy
14 : 2

وَإِذَا لَقُواْ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ قَالُوٓاْ ءَامَنَّا وَإِذَا خَلَوۡاْ إِلَىٰ شَيَٰطِينِهِمۡ قَالُوٓاْ إِنَّا مَعَكُمۡ إِنَّمَا نَحۡنُ مُسۡتَهۡزِءُونَ

14. ከእነዚያ በአላህ በትክክል ካመኑት ሰዎች ጋር በተገናኙ ጊዜ «እኛም (ልክ እንደ እናንተው) አምነናል» ይላሉ። ወደ ሰይጣኖቻቸው ባገለሉ ጊዜ ደግሞ «እኛ እኮ ከእናንተ ጋር ነን፤ እኛ በእነርሱ ተሳላቂዎች ብቻ ነን» ይላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
15 : 2

ٱللَّهُ يَسۡتَهۡزِئُ بِهِمۡ وَيَمُدُّهُمۡ فِي طُغۡيَٰنِهِمۡ يَعۡمَهُونَ

15. አላህ በእነርሱ ይሳለቅባቸዋል:: በአመጻቸዉም ውስጥ የሚዋልሉ ሲሆኑ ያቆያቸዋል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
16 : 2

أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ ٱشۡتَرَوُاْ ٱلضَّلَٰلَةَ بِٱلۡهُدَىٰ فَمَا رَبِحَت تِّجَٰرَتُهُمۡ وَمَا كَانُواْ مُهۡتَدِينَ

16. እነዚህ እነዚያ ስህተትን በቅንነት የገዙ (የለወጡ) ሰዎች ናቸው:: እናም ንግዳቸው ትርፋማ አይደለም:: ቅኑን መንገድም አልተከተሉም፡፡ info
التفاسير: