《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。

页码:close

external-link copy
29 : 11

وَيَٰقَوۡمِ لَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مَالًاۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَى ٱللَّهِۚ وَمَآ أَنَا۠ بِطَارِدِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْۚ إِنَّهُم مُّلَٰقُواْ رَبِّهِمۡ وَلَٰكِنِّيٓ أَرَىٰكُمۡ قَوۡمٗا تَجۡهَلُونَ

29. «ህዝቦቼ ሆይ! በእርሱ የተላክሁበትን በማድረስ ላይ ገንዘብን አልጠይቃችሁም:: ምንዳዬ ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለም:: እኔም እነዚያን በአላህ ያመኑትን ከአጠገቤ አባራሪ አይደለሁም:: እነርሱ ከጌታቸው ጋር የሚገናኙ ናቸውና:: ግን እኔም የምትሳሳቱ ህዝቦች ሆናችሁ አያችኋለሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
30 : 11

وَيَٰقَوۡمِ مَن يَنصُرُنِي مِنَ ٱللَّهِ إِن طَرَدتُّهُمۡۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ

30. «ህዝቦቼ ሆይ! ባባርራቸው ከአላህ ቅጣት የሚያድነኝ ማን ነው? አትገሰጹምን? info
التفاسير:

external-link copy
31 : 11

وَلَآ أَقُولُ لَكُمۡ عِندِي خَزَآئِنُ ٱللَّهِ وَلَآ أَعۡلَمُ ٱلۡغَيۡبَ وَلَآ أَقُولُ إِنِّي مَلَكٞ وَلَآ أَقُولُ لِلَّذِينَ تَزۡدَرِيٓ أَعۡيُنُكُمۡ لَن يُؤۡتِيَهُمُ ٱللَّهُ خَيۡرًاۖ ٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِمَا فِيٓ أَنفُسِهِمۡ إِنِّيٓ إِذٗا لَّمِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ

31. «ለናንተም እኔ ዘንድ የአላህ ግምጃ ቤቶች አሉ:: ሩቅንም አውቃለሁ አልላችሁም:: እኔም መልአክ ነኝ አልላችሁም:: ለእነዚያም ዓይኖቻችሁ ለሚያዋርዷቸው አላህ ደግ ነገርን እምነትን አይሰጣቸዉም አልልም:: አላህ በነፍሶቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ ነገር አዋቂ ነው:: እኔ ያን ጊዜ ከበደለኞች እሆናለሁና።» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
32 : 11

قَالُواْ يَٰنُوحُ قَدۡ جَٰدَلۡتَنَا فَأَكۡثَرۡتَ جِدَٰلَنَا فَأۡتِنَا بِمَا تَعِدُنَآ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ

32. «ኑህ ሆይ! በእርግጥ ተከራከርከን:: እኛን መከራከርህንም አበዛህ:: ከእውነተኞቹም ከሆንክ የምታስፈራራብንን ቅጣት አምጣው እስቲ።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
33 : 11

قَالَ إِنَّمَا يَأۡتِيكُم بِهِ ٱللَّهُ إِن شَآءَ وَمَآ أَنتُم بِمُعۡجِزِينَ

33. አላቸውም: «እርሱን የሚያመጣባችሁ አላህ የፈለገ ከሆነ ብቻ ነው። እናንተም የምታቅቱ አይደላችሁም። info
التفاسير:

external-link copy
34 : 11

وَلَا يَنفَعُكُمۡ نُصۡحِيٓ إِنۡ أَرَدتُّ أَنۡ أَنصَحَ لَكُمۡ إِن كَانَ ٱللَّهُ يُرِيدُ أَن يُغۡوِيَكُمۡۚ هُوَ رَبُّكُمۡ وَإِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ

34. «እናንተም አላህ ሊያጠማችሁ ፈልጎ ከሆነ ልመክራችሁ ብፈልግም ምክሬ አይጠቅማችሁም:: እርሱ ጌታችሁ ነው:: ወደ እርሱም ብቻ ትመለሳላችሁ።» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
35 : 11

أَمۡ يَقُولُونَ ٱفۡتَرَىٰهُۖ قُلۡ إِنِ ٱفۡتَرَيۡتُهُۥ فَعَلَيَّ إِجۡرَامِي وَأَنَا۠ بَرِيٓءٞ مِّمَّا تُجۡرِمُونَ

35. ይልቁንም ቀጠፈው ይላሉን? (ሙሐመድ ሆይ) «ብቀጥፈው ኃጢአቴ ቅጣቱ በእኔ ላይ ነው:: እኔም ከምታጠፉት ጥፋት ሁሉ ንጹህ ነኝ።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
36 : 11

وَأُوحِيَ إِلَىٰ نُوحٍ أَنَّهُۥ لَن يُؤۡمِنَ مِن قَوۡمِكَ إِلَّا مَن قَدۡ ءَامَنَ فَلَا تَبۡتَئِسۡ بِمَا كَانُواْ يَفۡعَلُونَ

36. ወደ ኑህም (እንዲህ በሚል) ተወረደ: «እነሆ ከህዝቦችህ በእርግጥ ካመኑት በስተቀር ወደፊት ሌሎች አያምኑም:: ይሠሩትም በነበሩት ክህደት አትዘን። info
التفاسير:

external-link copy
37 : 11

وَٱصۡنَعِ ٱلۡفُلۡكَ بِأَعۡيُنِنَا وَوَحۡيِنَا وَلَا تُخَٰطِبۡنِي فِي ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓاْ إِنَّهُم مُّغۡرَقُونَ

37. «በጥበቃችንና በትዕዛዛችን ሆነህ መርከቢቱን ሥራ። በእነዚያም በበደሉት ሰዎች ነገር አታናግረኝ። እነርሱ በእርግጥ የሚሰምጡ ናቸውና።» አለው። info
التفاسير: