Salin ng mga Kahulugan ng Marangal na Qur'an - Salin sa Wikang Amhariko ng Akademya ng Aprika

Numero ng Pahina:close

external-link copy
94 : 16

وَلَا تَتَّخِذُوٓاْ أَيۡمَٰنَكُمۡ دَخَلَۢا بَيۡنَكُمۡ فَتَزِلَّ قَدَمُۢ بَعۡدَ ثُبُوتِهَا وَتَذُوقُواْ ٱلسُّوٓءَ بِمَا صَدَدتُّمۡ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ وَلَكُمۡ عَذَابٌ عَظِيمٞ

94. ጫማዎች ከተደላደሉ በኋላ እንዳያንዳልጡ ከአላህ መንገድ በመከልከላችሁ ምክንያት ቅጣትንም እንዳትቀምሱ መሓሎቻችሁን በመካከላችሁ ለክዳት መግቢያ አታድርጉት:: ለእናንተም ያን ጊዜ ታላቅ ቅጣት አላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
95 : 16

وَلَا تَشۡتَرُواْ بِعَهۡدِ ٱللَّهِ ثَمَنٗا قَلِيلًاۚ إِنَّمَا عِندَ ٱللَّهِ هُوَ خَيۡرٞ لَّكُمۡ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ

95. በአላህ ቃል ኪዳን ጥቂትን ዋጋ አትግዙ። የምታውቁ ብትሆኑ አላህ ዘንድ ያለው ምንዳ እርሱ ለእናንተ በላጭ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
96 : 16

مَا عِندَكُمۡ يَنفَدُ وَمَا عِندَ ٱللَّهِ بَاقٖۗ وَلَنَجۡزِيَنَّ ٱلَّذِينَ صَبَرُوٓاْ أَجۡرَهُم بِأَحۡسَنِ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ

96. እናንተ ዘንድ ያለው ሁሉ ያልቃል:: አላህ ዘንድ ያለው ግን ለዘለዓለም ቀሪ ነው (አያልቅም):: እነዚያንም የታገሡትን ይሠሩት በነበሩት በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን:: info
التفاسير:

external-link copy
97 : 16

مَنۡ عَمِلَ صَٰلِحٗا مِّن ذَكَرٍ أَوۡ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤۡمِنٞ فَلَنُحۡيِيَنَّهُۥ حَيَوٰةٗ طَيِّبَةٗۖ وَلَنَجۡزِيَنَّهُمۡ أَجۡرَهُم بِأَحۡسَنِ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ

97. ከወንድም ይሁን ከሴት እርሱ አማኝ ሆኖ በጎን የሠራ ሁሉ መልካም ኑሮን እናኖረዋለን:: ይሠሩት ከነበሩት ነገር በመልካሙም ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን:: info
التفاسير:

external-link copy
98 : 16

فَإِذَا قَرَأۡتَ ٱلۡقُرۡءَانَ فَٱسۡتَعِذۡ بِٱللَّهِ مِنَ ٱلشَّيۡطَٰنِ ٱلرَّجِيمِ

98. ቁርኣንንም ለማንበብ ባሰብክ ጊዜ እርጉም ከሆነው ሰይጣን በአላህ ተጠበቅ:: info
التفاسير:

external-link copy
99 : 16

إِنَّهُۥ لَيۡسَ لَهُۥ سُلۡطَٰنٌ عَلَى ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَلَىٰ رَبِّهِمۡ يَتَوَكَّلُونَ

99. እርሱ በእነዚያ በትክክል ባመኑትና በጌታቸው ላይ በሚጠጉት ላይ ለእርሱ ሥልጣን የለዉምና:: info
التفاسير:

external-link copy
100 : 16

إِنَّمَا سُلۡطَٰنُهُۥ عَلَى ٱلَّذِينَ يَتَوَلَّوۡنَهُۥ وَٱلَّذِينَ هُم بِهِۦ مُشۡرِكُونَ

100. ሥልጣኑ በእነዚያ በሚታዘዙት ላይና በእነዚያም እነርሱ በእርሱ ምክንያት አጋሪዎች በሆኑት ላይ ብቻ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
101 : 16

وَإِذَا بَدَّلۡنَآ ءَايَةٗ مَّكَانَ ءَايَةٖ وَٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِمَا يُنَزِّلُ قَالُوٓاْ إِنَّمَآ أَنتَ مُفۡتَرِۭۚ بَلۡ أَكۡثَرُهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ

101. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአንቀጽም ስፍራ ሌላ አንቀጽን በለወጥን ጊዜ አላህም የሚያወርደውን ነገር አዋቂ ነው:: «አንተ ቀጣፊ እንጂ ሌላ አይደለህም።» ይላሉ:: በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም:: info
التفاسير:

external-link copy
102 : 16

قُلۡ نَزَّلَهُۥ رُوحُ ٱلۡقُدُسِ مِن رَّبِّكَ بِٱلۡحَقِّ لِيُثَبِّتَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَهُدٗى وَبُشۡرَىٰ لِلۡمُسۡلِمِينَ

102. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያን ያመኑትን ሰዎች ለማረጋጋት ሙስሊሞቹንም ለመምራትና ለማብሰር ቁርኣንን ጂብሪል እውነተኛ ሲሆን ከጌታህ አወረደው።» በላቸው:: info
التفاسير: