Salin ng mga Kahulugan ng Marangal na Qur'an - Salin sa Wikang Amhariko ni Muhammad Sadiq

አል አህቃፍ

external-link copy
1 : 46

حمٓ

ሓ ሚም info
التفاسير:

external-link copy
2 : 46

تَنزِيلُ ٱلۡكِتَٰبِ مِنَ ٱللَّهِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡحَكِيمِ

የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊ ጥበበኛ ከኾነው አላህ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 46

مَا خَلَقۡنَا ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ وَمَا بَيۡنَهُمَآ إِلَّا بِٱلۡحَقِّ وَأَجَلٖ مُّسَمّٗىۚ وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ عَمَّآ أُنذِرُواْ مُعۡرِضُونَ

ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በምርና የተወሰነ ጊዜንም በመለካት እንጅ (ለቀልድ) አልፈጠርናቸውም፡፡ እነዚያ የካዱትም ከተስፈራሩት ነገር (ትተው) ዘዋሪዎች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 46

قُلۡ أَرَءَيۡتُم مَّا تَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَرُونِي مَاذَا خَلَقُواْ مِنَ ٱلۡأَرۡضِ أَمۡ لَهُمۡ شِرۡكٞ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِۖ ٱئۡتُونِي بِكِتَٰبٖ مِّن قَبۡلِ هَٰذَآ أَوۡ أَثَٰرَةٖ مِّنۡ عِلۡمٍ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

«ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸውን አያችሁን? ከምድር ምንን እንደ ፈጠሩ አሳዩኝ፡፡ ወይም በሰማያት ለእነርሱ (ከአላህ ጋር) መጋራት አላቸውን? (ያማልዱናል በማለታችሁ) እውነተኞች እንደ ኾናችሁ ከዚህ (ቁርኣን) በፊት የኾነን መጽሐፍ ወይም ከዕውቀት የኾነ ቅርስን አምጡልኝ» በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 46

وَمَنۡ أَضَلُّ مِمَّن يَدۡعُواْ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَن لَّا يَسۡتَجِيبُ لَهُۥٓ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ وَهُمۡ عَن دُعَآئِهِمۡ غَٰفِلُونَ

እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልስለትን (ጣዖት) ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው፡፡ info
التفاسير: