పవిత్ర ఖురాన్ యొక్క భావార్థాల అనువాదం - అమ్హారిక్ అనువాదం - ఆఫ్రికా అకాడమీ

አን ነበእ

external-link copy
1 : 78

عَمَّ يَتَسَآءَلُونَ

1. ከምን ነገር ይጠያየቃሉ? info
التفاسير:

external-link copy
2 : 78

عَنِ ٱلنَّبَإِ ٱلۡعَظِيمِ

2. ከታላቁ ዜና (ቁርኣን) ይጠያየቃሉ። info
التفاسير:

external-link copy
3 : 78

ٱلَّذِي هُمۡ فِيهِ مُخۡتَلِفُونَ

3. ስለዚያ እነርሱ በእርሱ ላይ ስለተለያዩበት (ስለተወዛገቡበት):: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 78

كَلَّا سَيَعۡلَمُونَ

4. ጉዳዩ እነርሱ እንደሚሉት አይደለም:: (ትክክለኛውን) ወደ ፊት ያውቃሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 78

ثُمَّ كَلَّا سَيَعۡلَمُونَ

5. ከዚያም ይከልከሉ፤ (ትክክለኛውን) ወደ ፊት ያውቃሉ። info
التفاسير:

external-link copy
6 : 78

أَلَمۡ نَجۡعَلِ ٱلۡأَرۡضَ مِهَٰدٗا

6. ምድርን ምንጣፍ አላደርግንምን? info
التفاسير:

external-link copy
7 : 78

وَٱلۡجِبَالَ أَوۡتَادٗا

7. ጋራዎችንም ችካሎች (አላደረግንምን)? info
التفاسير:

external-link copy
8 : 78

وَخَلَقۡنَٰكُمۡ أَزۡوَٰجٗا

8. ጥንዶች አድርገንም ፈጠርናችሁ። info
التفاسير:

external-link copy
9 : 78

وَجَعَلۡنَا نَوۡمَكُمۡ سُبَاتٗا

9. እንቅልፋችሁንም እረፍት አደረግን። info
التفاسير:

external-link copy
10 : 78

وَجَعَلۡنَا ٱلَّيۡلَ لِبَاسٗا

10. ሌሊቱንም ልባስ አደረግን:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 78

وَجَعَلۡنَا ٱلنَّهَارَ مَعَاشٗا

11. ቀኑንም ለኑሮ መስሪያ (ለጉዳይ መከወኛ) አደረግን። info
التفاسير:

external-link copy
12 : 78

وَبَنَيۡنَا فَوۡقَكُمۡ سَبۡعٗا شِدَادٗا

12. ከበላያቸሁም ሰባት ብርቱዎችን (ሰማያት) ገነባን። info
التفاسير:

external-link copy
13 : 78

وَجَعَلۡنَا سِرَاجٗا وَهَّاجٗا

13. አንጸባራቂ ብርሃንንም አደርግንላችሁ። info
التفاسير:

external-link copy
14 : 78

وَأَنزَلۡنَا مِنَ ٱلۡمُعۡصِرَٰتِ مَآءٗ ثَجَّاجٗا

14. ከአረገዙት ደመናዎችም የሚንቧቧ ውሃን አወረድን:: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 78

لِّنُخۡرِجَ بِهِۦ حَبّٗا وَنَبَاتٗا

15.በእርሱ እህልንና ቅጠላ ቅጠልን፤ እናወጣ ዘንድ(አወረድን)። info
التفاسير:

external-link copy
16 : 78

وَجَنَّٰتٍ أَلۡفَافًا

16. የተቆላለፉ አትክልቶችንም :: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 78

إِنَّ يَوۡمَ ٱلۡفَصۡلِ كَانَ مِيقَٰتٗا

17. (በህዝቦች መካከልም) የመለያው ቀን የተወሰነ ጊዜ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
18 : 78

يَوۡمَ يُنفَخُ فِي ٱلصُّورِ فَتَأۡتُونَ أَفۡوَاجٗا

18. (ይሀዉም) በቀንዱ በሚነፋበትና በቡድን በቡድን ሆናችሁም በምትመጡበት ቀን ነው። info
التفاسير:

external-link copy
19 : 78

وَفُتِحَتِ ٱلسَّمَآءُ فَكَانَتۡ أَبۡوَٰبٗا

19. ሰማይም በምትከፈትና ባለ ብዙ ደጃፎችም በምትሆንበት ቀን፤ info
التفاسير:

external-link copy
20 : 78

وَسُيِّرَتِ ٱلۡجِبَالُ فَكَانَتۡ سَرَابًا

20. ጋራዎችም በሚናዱበትና እንደ ሲሪብዶም በሚሆንበትም ቀን ነው። info
التفاسير:

external-link copy
21 : 78

إِنَّ جَهَنَّمَ كَانَتۡ مِرۡصَادٗا

21. ገሀነም (ለከሓዲያን) መጠባበቂያ ኬላ (ስፍራ) ናት:: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 78

لِّلطَّٰغِينَ مَـَٔابٗا

22. ለህግ ተላላፊዎች መመላለሻ ስትሆን። info
التفاسير:

external-link copy
23 : 78

لَّٰبِثِينَ فِيهَآ أَحۡقَابٗا

23. በውስጧ ብዙ ዘመናትን ነዋሪዎች ሲሆኑ፤ info
التفاسير:

external-link copy
24 : 78

لَّا يَذُوقُونَ فِيهَا بَرۡدٗا وَلَا شَرَابًا

24. በውስጧ ቅዝቃዜንም መጠጠንም አይቀምሱም (አያገኙም)። info
التفاسير:

external-link copy
25 : 78

إِلَّا حَمِيمٗا وَغَسَّاقٗا

25. ሙቅ የፈላ ውሃንና እዥን እንጂ info
التفاسير:

external-link copy
26 : 78

جَزَآءٗ وِفَاقًا

26. ተመጣጣኝን ምንዳ ይመነዳሉ። info
التفاسير:

external-link copy
27 : 78

إِنَّهُمۡ كَانُواْ لَا يَرۡجُونَ حِسَابٗا

27. ምርመራ (እንዳለባቸው) ቅንጣት አይጠብቁም ነበርና። info
التفاسير:

external-link copy
28 : 78

وَكَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا كِذَّابٗا

28. በአናቅጻችንም ማስተባበልን አስተባበሉ። info
التفاسير:

external-link copy
29 : 78

وَكُلَّ شَيۡءٍ أَحۡصَيۡنَٰهُ كِتَٰبٗا

29. ነገሩን ሁሉ የተፃፈ ሲሆን አጠቃለልነው። info
التفاسير:

external-link copy
30 : 78

فَذُوقُواْ فَلَن نَّزِيدَكُمۡ إِلَّا عَذَابًا

30. «(የጃችሁን) ቅመሱም፤ ቅጣትን እንጂ ሌላን አንጨምርላችሁም» (ይባላሉም)። info
التفاسير:

external-link copy
31 : 78

إِنَّ لِلۡمُتَّقِينَ مَفَازًا

31. ለጥንቅቆቹ (አላህን ለሚፈሩ) ስኬት አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
32 : 78

حَدَآئِقَ وَأَعۡنَٰبٗا

32. አትክልቶችና ወይኖችም፤ info
التفاسير:

external-link copy
33 : 78

وَكَوَاعِبَ أَتۡرَابٗا

33. በእድሜ እኩያዎች የሆኑ ጡተ ጉችማዎችም፤ info
التفاسير:

external-link copy
34 : 78

وَكَأۡسٗا دِهَاقٗا

34. የተሞሉ ብርጭቆዎችም፤ info
التفاسير:

external-link copy
35 : 78

لَّا يَسۡمَعُونَ فِيهَا لَغۡوٗا وَلَا كِذَّٰبٗا

35. በውስጧ ትርፍ ቃልንም፤ ማስዋሸትንም አይሰሙም:: info
التفاسير:

external-link copy
36 : 78

جَزَآءٗ مِّن رَّبِّكَ عَطَآءً حِسَابٗا

36. ከጌታህ የሆነን ምንዳ፤ በቂ ስጦታን ተሰጡ:: info
التفاسير:

external-link copy
37 : 78

رَّبِّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَا ٱلرَّحۡمَٰنِۖ لَا يَمۡلِكُونَ مِنۡهُ خِطَابٗا

37. የሰማያትና የምድር በመካከላቸዉም ላለው ሁሉ ጌታ ከሆነውና በጣም አዛኝ ከሆነው ተመነዱ፤ ከእርሱ ጋር መነጋገርን አይችሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
38 : 78

يَوۡمَ يَقُومُ ٱلرُّوحُ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ صَفّٗاۖ لَّا يَتَكَلَّمُونَ إِلَّا مَنۡ أَذِنَ لَهُ ٱلرَّحۡمَٰنُ وَقَالَ صَوَابٗا

38. መልአኩ (ጅብሪል) እና ሌሎች መላዕክትም የተሰለፉ ሆነው በሚቆሙበት ቀን አረህማን ለእርሱ የፈቀደለትና ትክክለኛን ቃል ያለ ብቻ ቢሆን እንጂ መነጋገርን አይችሉም። info
التفاسير:

external-link copy
39 : 78

ذَٰلِكَ ٱلۡيَوۡمُ ٱلۡحَقُّۖ فَمَن شَآءَ ٱتَّخَذَ إِلَىٰ رَبِّهِۦ مَـَٔابًا

39. ያ! የእውነት ቀን ነው። የፈለገ ሰው ወደ ጌታው በመልካም ተግባር መመለስን ተግባሩ አድርጎ ይይዛል። info
التفاسير:

external-link copy
40 : 78

إِنَّآ أَنذَرۡنَٰكُمۡ عَذَابٗا قَرِيبٗا يَوۡمَ يَنظُرُ ٱلۡمَرۡءُ مَا قَدَّمَتۡ يَدَاهُ وَيَقُولُ ٱلۡكَافِرُ يَٰلَيۡتَنِي كُنتُ تُرَٰبَۢا

40. እኛ ቅርብ የሆነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ። ሰዎች ሁሉ በሁለት እጆቻቸው ያስቀደሙትን በግልጽ የሚያይበትና ከሓዲያን ሁሉ «ዋ ምኞቴ! ምንነው አፈር በሆንኩ ባልተቀሰቀስኩኝ» የሚሉበት ቀን። info
التفاسير: