పవిత్ర ఖురాన్ యొక్క భావార్థాల అనువాదం - అమ్హారిక్ అనువాదం - ఆఫ్రికా అకాడమీ

ኑህ

external-link copy
1 : 71

إِنَّآ أَرۡسَلۡنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوۡمِهِۦٓ أَنۡ أَنذِرۡ قَوۡمَكَ مِن قَبۡلِ أَن يَأۡتِيَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ

1. እኛ ኑህን ህዝቦችህን አሳማሚ ቅጣት ሳይመጣባቸው በፊት አስጠንቅቅ በማለት ወደ ወገኖቹ ላክነው:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 71

قَالَ يَٰقَوۡمِ إِنِّي لَكُمۡ نَذِيرٞ مُّبِينٌ

2. እርሱም አለ፡- «ሀዝቦቼ ሆይ! እኔ ለእናንተ (የቸገራችሁን) ገላጭ የሆንኩ አስጠንቃቂ ነኝ:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 71

أَنِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ وَٱتَّقُوهُ وَأَطِيعُونِ

3. «አላህን ተገዙት፡-ፍሩት፤ እኔንም ታዘዙኝ በማለት አስጠንቃቂ ነኝ። info
التفاسير:

external-link copy
4 : 71

يَغۡفِرۡ لَكُم مِّن ذُنُوبِكُمۡ وَيُؤَخِّرۡكُمۡ إِلَىٰٓ أَجَلٖ مُّسَمًّىۚ إِنَّ أَجَلَ ٱللَّهِ إِذَا جَآءَ لَا يُؤَخَّرُۚ لَوۡ كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ

4. «ለእናንተ ኃጢአታችሁን ይምራል እስከ ተወሰነ ጊዜም ያቆያችኋል:: አላህ የወሰነው ጊዜ በመጣ ወቅት ግን ለአፍታም አይቆይም:: በትክክል የምታውቁት ብትሆኑ ኖሮ በታዘዛችሁ ነበር።» info
التفاسير:

external-link copy
5 : 71

قَالَ رَبِّ إِنِّي دَعَوۡتُ قَوۡمِي لَيۡلٗا وَنَهَارٗا

5. ስለተቃወሙትም «ጌታየ ሆይ! እኔ በሌሊትም ሆነ በቀን ህዝቦቼን ጠራሁ። info
التفاسير:

external-link copy
6 : 71

فَلَمۡ يَزِدۡهُمۡ دُعَآءِيٓ إِلَّا فِرَارٗا

6. «ጥሪየም ይበልጥ መሸሽን እንጂ ሌላ አልጨመረላቸዉም። info
التفاسير:

external-link copy
7 : 71

وَإِنِّي كُلَّمَا دَعَوۡتُهُمۡ لِتَغۡفِرَ لَهُمۡ جَعَلُوٓاْ أَصَٰبِعَهُمۡ فِيٓ ءَاذَانِهِمۡ وَٱسۡتَغۡشَوۡاْ ثِيَابَهُمۡ وَأَصَرُّواْ وَٱسۡتَكۡبَرُواْ ٱسۡتِكۡبَارٗا

7. «እኔም ለእነርሱ ትምራቸው ዘንድ ወደ እምነት በጠራኋቸው ቁጥር ጣቶቻቸውን በጆሮዎቻቸው ውስጥ አደረጉ:: ልብሶቻቸውንም ተከናነቡ:: በመጥፎ ስራቸው ላይ ዘወተሩም:: ያለ ልክ መኩራትንም ኮሩ:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 71

ثُمَّ إِنِّي دَعَوۡتُهُمۡ جِهَارٗا

8. «ከዚያ እኔ በግልጽ ጠራኋቸው። info
التفاسير:

external-link copy
9 : 71

ثُمَّ إِنِّيٓ أَعۡلَنتُ لَهُمۡ وَأَسۡرَرۡتُ لَهُمۡ إِسۡرَارٗا

9. «ከዚያ እኔ ለእነርሱ ጥሪየን ይፋ አደረኩ:: ለእነርሱ መመስጠርን መሰጠርኩም» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
10 : 71

فَقُلۡتُ ٱسۡتَغۡفِرُواْ رَبَّكُمۡ إِنَّهُۥ كَانَ غَفَّارٗا

10. «እንዲህም አልኩ: ጌታችሁን ምህረትን ለምኑት:: እርሱም በጣም መሀሪ ነውና። info
التفاسير:

external-link copy
11 : 71

يُرۡسِلِ ٱلسَّمَآءَ عَلَيۡكُم مِّدۡرَارٗا

11. «በእናንተ ላይ ዝናምን ተከታታይ አድርጎ ይልካል። info
التفاسير:

external-link copy
12 : 71

وَيُمۡدِدۡكُم بِأَمۡوَٰلٖ وَبَنِينَ وَيَجۡعَل لَّكُمۡ جَنَّٰتٖ وَيَجۡعَل لَّكُمۡ أَنۡهَٰرٗا

12. «ገንዘቦችና ልጆችንም ይለግሳችኋል:: ለእናንተ አትክልቶችን ያደርግላችኋል:: ለእናተም ወንዞችን ያደርግላችኋል አልኳቸው።» info
التفاسير:

external-link copy
13 : 71

مَّا لَكُمۡ لَا تَرۡجُونَ لِلَّهِ وَقَارٗا

13. ለአላህ ተገቢውን ልቅና የማትሰጡበት ምክንያት ለእናንተ ምን አላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
14 : 71

وَقَدۡ خَلَقَكُمۡ أَطۡوَارًا

14. በልዩ ልዩ (በተለያዩ) እርከኖች (ሁኔታዎች) በእርግጥ የፈጠራችሁ ሲሆን:: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 71

أَلَمۡ تَرَوۡاْ كَيۡفَ خَلَقَ ٱللَّهُ سَبۡعَ سَمَٰوَٰتٖ طِبَاقٗا

15. አላህ ሰባት ሰማያትን አንዱ በአንዱ ላይ የተነባበረ ሲሆን እንዴት እንደፈጠረ አታዩምን? info
التفاسير:

external-link copy
16 : 71

وَجَعَلَ ٱلۡقَمَرَ فِيهِنَّ نُورٗا وَجَعَلَ ٱلشَّمۡسَ سِرَاجٗا

16. በውስጣቸዉም ጨረቃን አብሪ አደረገ:: ጸሐይንም ብርሃን አደረገ:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 71

وَٱللَّهُ أَنۢبَتَكُم مِّنَ ٱلۡأَرۡضِ نَبَاتٗا

17. አላህም ከምድር ማብቀልን አበቀላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 71

ثُمَّ يُعِيدُكُمۡ فِيهَا وَيُخۡرِجُكُمۡ إِخۡرَاجٗا

18. ከዚያም በውስጧ ይመልሳችኋል:: ማውጣትንም ያወጣችኋል:: info
التفاسير:

external-link copy
19 : 71

وَٱللَّهُ جَعَلَ لَكُمُ ٱلۡأَرۡضَ بِسَاطٗا

19. አላህም ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ አደረጋት። info
التفاسير:

external-link copy
20 : 71

لِّتَسۡلُكُواْ مِنۡهَا سُبُلٗا فِجَاجٗا

20. ከእርሷ ሰፋፊዎችን መንገዶች ትገቡ ዘንድ:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 71

قَالَ نُوحٞ رَّبِّ إِنَّهُمۡ عَصَوۡنِي وَٱتَّبَعُواْ مَن لَّمۡ يَزِدۡهُ مَالُهُۥ وَوَلَدُهُۥٓ إِلَّا خَسَارٗا

21. ኑሕም አለ፡- «ጌታየ ሆይ! እነርሱም አመጹብኝ ገንዘቡና ልጁም ከጥፋት በስተቀር ያልጨመረለትን ሰው ተከተሉ። info
التفاسير:

external-link copy
22 : 71

وَمَكَرُواْ مَكۡرٗا كُبَّارٗا

22. «ከባድንም ተንኮል ያሴሩትን ሰዎች ተከተሉ። info
التفاسير:

external-link copy
23 : 71

وَقَالُواْ لَا تَذَرُنَّ ءَالِهَتَكُمۡ وَلَا تَذَرُنَّ وَدّٗا وَلَا سُوَاعٗا وَلَا يَغُوثَ وَيَعُوقَ وَنَسۡرٗا

23. መሪዎችም አሉ፡- <አማልክቶቻችሁን፤ ወድንም፤ ሰዋዕንም፤ የጉስንም፤ የዑቅንና ነስርንም አትተው።> info
التفاسير:

external-link copy
24 : 71

وَقَدۡ أَضَلُّواْ كَثِيرٗاۖ وَلَا تَزِدِ ٱلظَّٰلِمِينَ إِلَّا ضَلَٰلٗا

24. «በእርግጥ (እነዚህ መሪዎች ወይም ጣኦቶች) ብዙዎችን ሰዎች አሳሳቱ:: ከሓዲያንንም ጥመትን እንጂ ሌላን አትጨምርላቸው» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
25 : 71

مِّمَّا خَطِيٓـَٰٔتِهِمۡ أُغۡرِقُواْ فَأُدۡخِلُواْ نَارٗا فَلَمۡ يَجِدُواْ لَهُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ أَنصَارٗا

25. በኃጢአቶቻቸው ምክንያት ተሰመጡ:: እሳትንም እንዲገቡ ተደረጉ:: ለእነርሱም ከአላህ ሌላ የሆኑ ረዳቶችን አላገኙም:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 71

وَقَالَ نُوحٞ رَّبِّ لَا تَذَرۡ عَلَى ٱلۡأَرۡضِ مِنَ ٱلۡكَٰفِرِينَ دَيَّارًا

26. ኑህም አለ፡- «ጌታየ ሆይ! ከከሓዲያን በምድር ላይ (በዓለም ላይ) የሚኖርን አንድንም አትተው። info
التفاسير:

external-link copy
27 : 71

إِنَّكَ إِن تَذَرۡهُمۡ يُضِلُّواْ عِبَادَكَ وَلَا يَلِدُوٓاْ إِلَّا فَاجِرٗا كَفَّارٗا

27. «አንተ ብትተዋቸው ባሮችህን ያሳስታሉና:: ኃጢአተኛ ከሓዲንም እንጂ ሌላን አይወልዱም። info
التفاسير:

external-link copy
28 : 71

رَّبِّ ٱغۡفِرۡ لِي وَلِوَٰلِدَيَّ وَلِمَن دَخَلَ بَيۡتِيَ مُؤۡمِنٗا وَلِلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِۖ وَلَا تَزِدِ ٱلظَّٰلِمِينَ إِلَّا تَبَارَۢا

28. «ጌታየ ሆይ! ለእኔም ለወላጆቼም ትክክለኛ አማኝ ሆኖ በቤቴ ለገባ ሁሉ ለአማኞችና ለምዕመናትም ምህረት አድርግ:: ከሓዲያንንም ከጥፋት በስተቀር አትጨምርላቸው።» አለ። info
التفاسير: