పవిత్ర ఖురాన్ యొక్క భావార్థాల అనువాదం - అమ్హారిక్ అనువాదం - ఆఫ్రికా అకాడమీ

አል ሙጃደላ

external-link copy
1 : 58

قَدۡ سَمِعَ ٱللَّهُ قَوۡلَ ٱلَّتِي تُجَٰدِلُكَ فِي زَوۡجِهَا وَتَشۡتَكِيٓ إِلَى ٱللَّهِ وَٱللَّهُ يَسۡمَعُ تَحَاوُرَكُمَآۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعُۢ بَصِيرٌ

1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ የዚያችን በባሏ ጉዳይ ላይ የምትከራከርህንና ወደ አላህ ስሞታን የምታሰማውን ሴትዮ ቃል ሰማ:: አላህ በንግግር መመላለሳችሁን (መወያየታችሁን) ይሰማል:: አላህ (ለሚባለው) ሁሉ ሰሚ (ለሚፈጸመው ሁሉ ነገር) አዋቂ ነውና። info
التفاسير:

external-link copy
2 : 58

ٱلَّذِينَ يُظَٰهِرُونَ مِنكُم مِّن نِّسَآئِهِم مَّا هُنَّ أُمَّهَٰتِهِمۡۖ إِنۡ أُمَّهَٰتُهُمۡ إِلَّا ٱلَّٰٓـِٔي وَلَدۡنَهُمۡۚ وَإِنَّهُمۡ لَيَقُولُونَ مُنكَرٗا مِّنَ ٱلۡقَوۡلِ وَزُورٗاۚ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَعَفُوٌّ غَفُورٞ

2. እነዚያ ከናንተ መካከል ሚስቶቻቸውን እንደእናቶቻቸው ጀርባዎች ይሁኑብን በማለት የሚምሉ ሰዎች እነርሱ እናቶቻቸው አይደሉም:: ትክክለኛ እናቶቻቸው እነዚያ የወለዷቸው ሴቶች ብቻ ናቸው:: እነርሱ በዚህ ቃል የተጠላ ንግግርንና ውሸትን በእርግጥ ይናገራሉ:: አላህ ለሚጸጸት ሰው ሁሉ ይቅር ባይና መሀሪ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 58

وَٱلَّذِينَ يُظَٰهِرُونَ مِن نِّسَآئِهِمۡ ثُمَّ يَعُودُونَ لِمَا قَالُواْ فَتَحۡرِيرُ رَقَبَةٖ مِّن قَبۡلِ أَن يَتَمَآسَّاۚ ذَٰلِكُمۡ تُوعَظُونَ بِهِۦۚ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ خَبِيرٞ

3. እነዚያ ሚስቶቻቸውን እንደእናቶቻቸው ጀርባዎች ይሁኑብን በማለት የሚምሉና ከዚያ ወደ ተናገሩት የሚመለሱ ሳይነካኩ በፊት በባርነት የተያዘችዋን ጫንቃ ነፃ ማውጣት ግዴታ አለባቸው:: ይህ ህግ (የተጠቀሰው ህግ) በእርሱ ትገሰጹበታላችሁ:: አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
4 : 58

فَمَن لَّمۡ يَجِدۡ فَصِيَامُ شَهۡرَيۡنِ مُتَتَابِعَيۡنِ مِن قَبۡلِ أَن يَتَمَآسَّاۖ فَمَن لَّمۡ يَسۡتَطِعۡ فَإِطۡعَامُ سِتِّينَ مِسۡكِينٗاۚ ذَٰلِكَ لِتُؤۡمِنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦۚ وَتِلۡكَ حُدُودُ ٱللَّهِۗ وَلِلۡكَٰفِرِينَ عَذَابٌ أَلِيمٌ

4. ይህን ላላገኘም ሰው ከመነካካታቸው በፊት ሁለት ተከታታይ ወሮችን መፆም አለበት:: ይህን ላልቻለም ሰው ስልሳ ድሆችን ማብላት አለበት:: ይህ በአላህና በመልዕክተኛው እንድታምኑ ነው:: እነኚህ ህግጋት የአላህ ህግጋት ናቸው:: (እናም አትተላለፏቸው::) ለከሓዲያንም ሁሉ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 58

إِنَّ ٱلَّذِينَ يُحَآدُّونَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ كُبِتُواْ كَمَا كُبِتَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ وَقَدۡ أَنزَلۡنَآ ءَايَٰتِۭ بَيِّنَٰتٖۚ وَلِلۡكَٰفِرِينَ عَذَابٞ مُّهِينٞ

5. ግልጽ ማስረጃዎችን ያወረድን ስንሆን እነዚያ አላህንና መልዕክተኛውን የሚከራከሩ ሰዎች እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩ ሰዎች እንደተዋረዱት ሁሉ ተዋርደዋል:: ለከሓዲያን አዋራጅ ቅጣት አለባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 58

يَوۡمَ يَبۡعَثُهُمُ ٱللَّهُ جَمِيعٗا فَيُنَبِّئُهُم بِمَا عَمِلُوٓاْۚ أَحۡصَىٰهُ ٱللَّهُ وَنَسُوهُۚ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ شَهِيدٌ

6. አላህ ሁላቸውንም በአንድ አድርጎ (አንድም ሳይቀር በአንድ ዓይነት) በሚቀሰቅሳቸው ቀን (ይቀጣቸዋል):: ከዚያም በዚህ ዓለም የሰሩትን ነገር ሁሉ ይነግራቸዋል:: እነርሱ የረሱት ሲሆን (መዝገባቸው ተመዝግቦ ያገኙታል) አላህ ግን አንድም ሳይቀር አውቆታል:: አላህ ሁሉንም ነገር ተመልካች ነውና:: info
التفاسير: