పవిత్ర ఖురాన్ యొక్క భావార్థాల అనువాదం - అమ్హారిక్ అనువాదం - ఆఫ్రికా అకాడమీ

పేజీ నెంబరు:close

external-link copy
23 : 34

وَلَا تَنفَعُ ٱلشَّفَٰعَةُ عِندَهُۥٓ إِلَّا لِمَنۡ أَذِنَ لَهُۥۚ حَتَّىٰٓ إِذَا فُزِّعَ عَن قُلُوبِهِمۡ قَالُواْ مَاذَا قَالَ رَبُّكُمۡۖ قَالُواْ ٱلۡحَقَّۖ وَهُوَ ٱلۡعَلِيُّ ٱلۡكَبِيرُ

23. ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም:: ከልቦቻቸው ላይ ድንጋጤው በተገለጠ ጊዜ ተማላጆቹ «ጌታችሁ ምን አለ?» ይላሉ:: አማላጆቹም: «እውነትን አለ። እርሱም ከፍተኛውና ታላቁ ጌታ ነው።» ይላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 34

۞ قُلۡ مَن يَرۡزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ قُلِ ٱللَّهُۖ وَإِنَّآ أَوۡ إِيَّاكُمۡ لَعَلَىٰ هُدًى أَوۡ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ

24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ)፤ «ከሰማያትና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማነው?» በላቸው። «አላህ ነው እኛ ወይም እናንተ በትክክለኛው መንገድ ላይ ወይም በግልጽ መሳሳት ውስጥ ነን።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
25 : 34

قُل لَّا تُسۡـَٔلُونَ عَمَّآ أَجۡرَمۡنَا وَلَا نُسۡـَٔلُ عَمَّا تَعۡمَلُونَ

25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ !)«ካጠፋነው ጥፋት አትጠየቁም:: ከምትሰሩትም ስራ አንጠየቅም።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 34

قُلۡ يَجۡمَعُ بَيۡنَنَا رَبُّنَا ثُمَّ يَفۡتَحُ بَيۡنَنَا بِٱلۡحَقِّ وَهُوَ ٱلۡفَتَّاحُ ٱلۡعَلِيمُ

26.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል። ከዚያም በመካከላችን በእውነት ይፈርዳል:: እርሱም በትክክል ፈራጁና አዋቂው ነው።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
27 : 34

قُلۡ أَرُونِيَ ٱلَّذِينَ أَلۡحَقۡتُم بِهِۦ شُرَكَآءَۖ كَلَّاۚ بَلۡ هُوَ ٱللَّهُ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ

27.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያን ተጋሪዎች አድርጋችሁ በእሱ ያስጠጋችኋቸውን ጣዖታት እስቲ አሳዩኝ:: ተው አታጋሩ:: በእውነት እርሱ አሸናፊዉና ጥበበኛው አላህ ነው።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
28 : 34

وَمَآ أَرۡسَلۡنَٰكَ إِلَّا كَآفَّةٗ لِّلنَّاسِ بَشِيرٗا وَنَذِيرٗا وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ

28. አንተንም ለሰዎች ሁሉ በመላ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ቢሆን እንጂ አልላክንህም:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም:: info
التفاسير:

external-link copy
29 : 34

وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلۡوَعۡدُ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

29. «እውነተኞችም እንደ ሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
30 : 34

قُل لَّكُم مِّيعَادُ يَوۡمٖ لَّا تَسۡتَـٔۡخِرُونَ عَنۡهُ سَاعَةٗ وَلَا تَسۡتَقۡدِمُونَ

30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ለእናንተ ከእርሱ አንዳችንም ሰዓት የማትዘገዩበት የማትቀድሙበትም የቀጠሮ ቀን አላችሁ።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
31 : 34

وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَن نُّؤۡمِنَ بِهَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانِ وَلَا بِٱلَّذِي بَيۡنَ يَدَيۡهِۗ وَلَوۡ تَرَىٰٓ إِذِ ٱلظَّٰلِمُونَ مَوۡقُوفُونَ عِندَ رَبِّهِمۡ يَرۡجِعُ بَعۡضُهُمۡ إِلَىٰ بَعۡضٍ ٱلۡقَوۡلَ يَقُولُ ٱلَّذِينَ ٱسۡتُضۡعِفُواْ لِلَّذِينَ ٱسۡتَكۡبَرُواْ لَوۡلَآ أَنتُمۡ لَكُنَّا مُؤۡمِنِينَ

31. እነዚያም የካዱት «በዚህ ቁርኣንና በዚያ ከበፊቱ ባለዉም መጽሐፍ በጭራሽ አናምንም።» አሉ:: በዳዮችም ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ንግግርን የሚመላላሱ ሆነው በጌታቸው ዘንድ በሚቆሙ ጊዜ ብታይ ኖሮ አስደናቂን ነገር ታይ ነበር:: እነዚያ የተዋረዱት ለእነዚያ ለኮሩት «እናንተ ባልነበራችሁ ኖሮ ትክክለኛ አማኞች በሆንን ነበር።» ይላሉ:: info
التفاسير: