పవిత్ర ఖురాన్ యొక్క భావార్థాల అనువాదం - అమ్హారిక్ అనువాదం - ముహమ్మద్ సాదిఖ్

పేజీ నెంబరు:close

external-link copy
104 : 5

وَإِذَا قِيلَ لَهُمۡ تَعَالَوۡاْ إِلَىٰ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ وَإِلَى ٱلرَّسُولِ قَالُواْ حَسۡبُنَا مَا وَجَدۡنَا عَلَيۡهِ ءَابَآءَنَآۚ أَوَلَوۡ كَانَ ءَابَآؤُهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ شَيۡـٔٗا وَلَا يَهۡتَدُونَ

ለእነርሱም አላህ ወደ አወረደውና ወደ መልክተኛው ኑ በተባሉ ጊዜ «አባቶቻችንን በርሱ ላይ ያገኘንበት ነገር ይበቃናል» ይላሉ፡፡ አባቶቻቸው ምንም የማያውቁና የማይመሩ ቢኾኑም (ይኸንን ማለት ይበቃቸዋልን) info
التفاسير:

external-link copy
105 : 5

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ عَلَيۡكُمۡ أَنفُسَكُمۡۖ لَا يَضُرُّكُم مَّن ضَلَّ إِذَا ٱهۡتَدَيۡتُمۡۚ إِلَى ٱللَّهِ مَرۡجِعُكُمۡ جَمِيعٗا فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁን (ከእሳት) ያዙ፤ (ጠብቁ)፡፡ በተመራችሁ ጊዜ የተሳሳተ ሰው አይጎዳችሁም፡፡ የሁላችሁም መመለሻ ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
106 : 5

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ شَهَٰدَةُ بَيۡنِكُمۡ إِذَا حَضَرَ أَحَدَكُمُ ٱلۡمَوۡتُ حِينَ ٱلۡوَصِيَّةِ ٱثۡنَانِ ذَوَا عَدۡلٖ مِّنكُمۡ أَوۡ ءَاخَرَانِ مِنۡ غَيۡرِكُمۡ إِنۡ أَنتُمۡ ضَرَبۡتُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَأَصَٰبَتۡكُم مُّصِيبَةُ ٱلۡمَوۡتِۚ تَحۡبِسُونَهُمَا مِنۢ بَعۡدِ ٱلصَّلَوٰةِ فَيُقۡسِمَانِ بِٱللَّهِ إِنِ ٱرۡتَبۡتُمۡ لَا نَشۡتَرِي بِهِۦ ثَمَنٗا وَلَوۡ كَانَ ذَا قُرۡبَىٰ وَلَا نَكۡتُمُ شَهَٰدَةَ ٱللَّهِ إِنَّآ إِذٗا لَّمِنَ ٱلۡأٓثِمِينَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አንዳችሁን ሞት በመጣበት ጊዜ በኑዛዜ ወቅት የመካከላችሁ ምስክርነት ከእናንተ ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶች የኾኑ ሰዎች ወይም በምድር ብትጓዙና የሞት አደጋ ብትነካችሁ ከሌሎቻችሁ የኾኑ ሁለት ሌሎች ሰዎች (መመስከር) ነው፡፡ ብትጠራጠሩ ከሶላት (ከዐሱር) በኋላ ታቆሟቸውና (የሚመሰክርለት ሰው) የዝምድና ባለቤት ቢኾንም እንኳ «በርሱ ዋጋን አንገዛም የአላህንም ምስክርነት አንደብቅም፤ ያን ጊዜ (ደብቀን ብንገኝ) እኛ ከኃጢአተኞች ነን» ብለው በአላህ ስም ይምላሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
107 : 5

فَإِنۡ عُثِرَ عَلَىٰٓ أَنَّهُمَا ٱسۡتَحَقَّآ إِثۡمٗا فَـَٔاخَرَانِ يَقُومَانِ مَقَامَهُمَا مِنَ ٱلَّذِينَ ٱسۡتَحَقَّ عَلَيۡهِمُ ٱلۡأَوۡلَيَٰنِ فَيُقۡسِمَانِ بِٱللَّهِ لَشَهَٰدَتُنَآ أَحَقُّ مِن شَهَٰدَتِهِمَا وَمَا ٱعۡتَدَيۡنَآ إِنَّآ إِذٗا لَّمِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ

እነርሱም ኃጢአትን (በውሸት መስክረው) የተገቡ መኾናቸው ቢታወቅ ከእነዚያ (ለሟቹ) ቅርቦች በመኾን (ውርስ) ከተገባቸው የኾኑ ሁለት ሌሎች ሰዎች በስፍራቸው (በምስክሮች ስፍራ) ይቆሙና «ምስክርነታችን ከእነሱ ምስክርነት ይልቅ እውነት ነው ወሰንም አላለፍንም ያን ጊዜ እኛ ከበዳዮች ነን» ሲሉ በአላህ ይምላሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
108 : 5

ذَٰلِكَ أَدۡنَىٰٓ أَن يَأۡتُواْ بِٱلشَّهَٰدَةِ عَلَىٰ وَجۡهِهَآ أَوۡ يَخَافُوٓاْ أَن تُرَدَّ أَيۡمَٰنُۢ بَعۡدَ أَيۡمَٰنِهِمۡۗ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَٱسۡمَعُواْۗ وَٱللَّهُ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلۡفَٰسِقِينَ

ይህ ምስክርነትን በተገቢዋ ላይ ለማምጣታቸው ወይም ከመሐላዎቻቸው በኋላ የመሐላዎችን (ወደ ወራሾች) መመለስን ለመፍራት በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ ስሙም፡፡ አላህም አመጸኞች ሕዝቦችን አይመራም፡፡ info
التفاسير: