அல்குர்ஆன் மொழிபெயர்ப்பு - அம்ஹாரிக் மொழிபெயர்ப்பு - ஆபிரிக்கா அகாடமி

பக்க எண்:close

external-link copy
31 : 35

وَٱلَّذِيٓ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ مِنَ ٱلۡكِتَٰبِ هُوَ ٱلۡحَقُّ مُصَدِّقٗا لِّمَا بَيۡنَ يَدَيۡهِۗ إِنَّ ٱللَّهَ بِعِبَادِهِۦ لَخَبِيرُۢ بَصِيرٞ

31. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያ ከመጽሐፉ ወደ አንተ ያወረድነው ከበፊቱ ላለው አረጋጋጭ ሲሆን እርሱ እውነት ነው:: አላህ በእርግጥ በባሮቹ ውስጥ አዋቂና ተመልካች ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
32 : 35

ثُمَّ أَوۡرَثۡنَا ٱلۡكِتَٰبَ ٱلَّذِينَ ٱصۡطَفَيۡنَا مِنۡ عِبَادِنَاۖ فَمِنۡهُمۡ ظَالِمٞ لِّنَفۡسِهِۦ وَمِنۡهُم مُّقۡتَصِدٞ وَمِنۡهُمۡ سَابِقُۢ بِٱلۡخَيۡرَٰتِ بِإِذۡنِ ٱللَّهِۚ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلۡفَضۡلُ ٱلۡكَبِيرُ

32. ከዚያ እነዚያ ከባሮቻችን የመረጥናቸውን መጽሐፉን አወረስናቸው :: ከእነርሱም ነፍሱን በዳይ አለ:: ከእነርሱም መካከለኛ አለ:: ከእነርሱም በአላህ ፈቃድ በበጎ ስራዎች ቀዳሚ አለ:: ያንኑ ማውረስ እርሱ ታላቅ ችሮታ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
33 : 35

جَنَّٰتُ عَدۡنٖ يَدۡخُلُونَهَا يُحَلَّوۡنَ فِيهَا مِنۡ أَسَاوِرَ مِن ذَهَبٖ وَلُؤۡلُؤٗاۖ وَلِبَاسُهُمۡ فِيهَا حَرِيرٞ

33. የመኖሪያ ገነቶችን በውስጧ የወርቅ አንባሮችን ሉልንም የሚሸለሙ ሆነው ይገቡበታል:: በእርሷ ውስጥ አልባሳታቸዉም ሀር ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
34 : 35

وَقَالُواْ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِيٓ أَذۡهَبَ عَنَّا ٱلۡحَزَنَۖ إِنَّ رَبَّنَا لَغَفُورٞ شَكُورٌ

34. ይላሉም «ምስጋና ሁሉ ለዚያ ከእኛ ላይ ሐዘንን ላስወገደልን ይገባው። ጌታችን በጣም መሃሪና አመስጋኝ ነውና። info
التفاسير:

external-link copy
35 : 35

ٱلَّذِيٓ أَحَلَّنَا دَارَ ٱلۡمُقَامَةِ مِن فَضۡلِهِۦ لَا يَمَسُّنَا فِيهَا نَصَبٞ وَلَا يَمَسُّنَا فِيهَا لُغُوبٞ

35. እርሱም ያ ከችሮታው የዘላለም መኖሪያን አገር ያሰፈረን ነው:: በእርሷም ውስጥ መከራ አይነካንም:: በእርሷም ውስጥ ድካም አይነካንም:: info
التفاسير:

external-link copy
36 : 35

وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَهُمۡ نَارُ جَهَنَّمَ لَا يُقۡضَىٰ عَلَيۡهِمۡ فَيَمُوتُواْ وَلَا يُخَفَّفُ عَنۡهُم مِّنۡ عَذَابِهَاۚ كَذَٰلِكَ نَجۡزِي كُلَّ كَفُورٖ

36. እነዚያ በአላህ የካዱት ለእነርሱ የገሀነም እሳት አለላቸው:: ይሞቱ ዘንድም በእነርሱ ላይ ሞት አይፈረድም:: ከቅጣቷም ከእነርሱ አይቀለልላቸዉም:: ልክ እንደዚሁ ከሓዲያንን ሁሉ እንመነዳለን:: info
التفاسير:

external-link copy
37 : 35

وَهُمۡ يَصۡطَرِخُونَ فِيهَا رَبَّنَآ أَخۡرِجۡنَا نَعۡمَلۡ صَٰلِحًا غَيۡرَ ٱلَّذِي كُنَّا نَعۡمَلُۚ أَوَلَمۡ نُعَمِّرۡكُم مَّا يَتَذَكَّرُ فِيهِ مَن تَذَكَّرَ وَجَآءَكُمُ ٱلنَّذِيرُۖ فَذُوقُواْ فَمَا لِلظَّٰلِمِينَ مِن نَّصِيرٍ

37. እነርሱም በእርሷ ውስጥ እርዳታን በመፈለግ በኃይል ይጮሃሉ:: «ጌታችን ሆይ! ከእዚያ እንሠራው ከነበርነው ሌላ በጎ ሥራን እንሠራ ዘንድ አውጣን» (ይላሉ)፡፡ «በእርሱ ውስጥ ያስታወሰ ሰው የሚገሰጽበትን እድሜ አላቆየናችሁምን? አስጠንቃቂዉም መጥቶላችኋል:: አስተባብላችኋልም:: ስለዚህ ቅመሱ:: ለበደለኞችም ምንም ረዳት የላቸዉም» ይባላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
38 : 35

إِنَّ ٱللَّهَ عَٰلِمُ غَيۡبِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ إِنَّهُۥ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ

38. አላህ የሰማያትንና የምድርን ምስጢር በእርግጥ አዋቂ ነው:: እርሱ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ እንኳ አዋቂ ነውና:: info
التفاسير: