அல்குர்ஆன் மொழிபெயர்ப்பு - அம்ஹாரிக் மொழிபெயர்ப்பு - முஹம்மத் சாதிக்

ጣሃ

external-link copy
1 : 20

طه

ጧ ሃ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 20

مَآ أَنزَلۡنَا عَلَيۡكَ ٱلۡقُرۡءَانَ لِتَشۡقَىٰٓ

ቁርኣንን ባንተ ላይ እንድትቸገር አላወረድንም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 20

إِلَّا تَذۡكِرَةٗ لِّمَن يَخۡشَىٰ

ግን አላህን ለሚፈራ ሰው መገሰጫ ይኾን ዘንድ (አወረድነው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 20

تَنزِيلٗا مِّمَّنۡ خَلَقَ ٱلۡأَرۡضَ وَٱلسَّمَٰوَٰتِ ٱلۡعُلَى

ምድርንና የላይኛዎቹን ሰማያት ከፈጠረ አምላክ ተወረደ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 20

ٱلرَّحۡمَٰنُ عَلَى ٱلۡعَرۡشِ ٱسۡتَوَىٰ

(እርሱ) አልረሕማን ነው በዐርሹ ላይ (ለሱ ክብር በሚስማማ መልኩ) ተደላደለ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
6 : 20

لَهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَا وَمَا تَحۡتَ ٱلثَّرَىٰ

በሰማያት ያለው፣ በምድርም ያለው፣ በመካከላቸውም ያለው፣ ከዐፈር በታችም ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
7 : 20

وَإِن تَجۡهَرۡ بِٱلۡقَوۡلِ فَإِنَّهُۥ يَعۡلَمُ ٱلسِّرَّ وَأَخۡفَى

በንግግር ብትጮህ (አላህ ከጩኸቱ የተብቃቃ ነው)፡፡ እርሱ ምስጢርን በጣም የተደበቀንም ያውቃልና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
8 : 20

ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ لَهُ ٱلۡأَسۡمَآءُ ٱلۡحُسۡنَىٰ

አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ለእርሱ መልካሞች የኾኑ ስሞች አልሉት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
9 : 20

وَهَلۡ أَتَىٰكَ حَدِيثُ مُوسَىٰٓ

የሙሳም ወሬ በእርግጥ መጥቶሃል? info
التفاسير:

external-link copy
10 : 20

إِذۡ رَءَا نَارٗا فَقَالَ لِأَهۡلِهِ ٱمۡكُثُوٓاْ إِنِّيٓ ءَانَسۡتُ نَارٗا لَّعَلِّيٓ ءَاتِيكُم مِّنۡهَا بِقَبَسٍ أَوۡ أَجِدُ عَلَى ٱلنَّارِ هُدٗى

እሳትን ባየና ለቤተሰቦቹ፡- (እዚህ) «ቆዩ፤ እኔ እሳትን አየሁ፡፡ ከእርሷ ችቦን ላመጣላችሁ፤ ወይም እሳቲቱ ዘንድ መሪን ላገኝ እከጅላለሁ» ባለጊዜ (አስታውስ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
11 : 20

فَلَمَّآ أَتَىٰهَا نُودِيَ يَٰمُوسَىٰٓ

በመጣትም ጊዜ «ሙሳ ሆይ» በማለት ተጠራ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
12 : 20

إِنِّيٓ أَنَا۠ رَبُّكَ فَٱخۡلَعۡ نَعۡلَيۡكَ إِنَّكَ بِٱلۡوَادِ ٱلۡمُقَدَّسِ طُوٗى

«እኔ ጌታህ እኔ ነኝ ጫማዎችህንም አውልቅ፡፡ አንተ በተቀደሰው ሸለቆ በጡዋ ነህና፡፡ info
التفاسير: