د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي

د مخ نمبر:close

external-link copy
156 : 7

۞ وَٱكۡتُبۡ لَنَا فِي هَٰذِهِ ٱلدُّنۡيَا حَسَنَةٗ وَفِي ٱلۡأٓخِرَةِ إِنَّا هُدۡنَآ إِلَيۡكَۚ قَالَ عَذَابِيٓ أُصِيبُ بِهِۦ مَنۡ أَشَآءُۖ وَرَحۡمَتِي وَسِعَتۡ كُلَّ شَيۡءٖۚ فَسَأَكۡتُبُهَا لِلَّذِينَ يَتَّقُونَ وَيُؤۡتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَٱلَّذِينَ هُم بِـَٔايَٰتِنَا يُؤۡمِنُونَ

156. «ጌታችን ሆይ! ለእኛ በዚች በቅርቢቱ ዓለም መልካሟን በመጨረሻይቱም ዓለም መልካሟን ጻፍልን:: እኛ ወደ አንተ ተመልሰናል።» (ሲል ሙሳ ጌታውን ለመነ):: አላህም አለ: «ቅጣቴ በእርሱ ልቀጣው የምፈልገውን ሰው እቀጣበታለሁ:: ችሮታዬ ከሁሉም ነገር የሰፋ ነው:: ለእነዚያ ለሚጠነቀቁ ዘካንም ለሚሰጡ ለእነዚያም በአናቅጻችን ለሚያምኑ ሁሉ በእርግጥ እጽፈዋለሁ::» info
التفاسير:

external-link copy
157 : 7

ٱلَّذِينَ يَتَّبِعُونَ ٱلرَّسُولَ ٱلنَّبِيَّ ٱلۡأُمِّيَّ ٱلَّذِي يَجِدُونَهُۥ مَكۡتُوبًا عِندَهُمۡ فِي ٱلتَّوۡرَىٰةِ وَٱلۡإِنجِيلِ يَأۡمُرُهُم بِٱلۡمَعۡرُوفِ وَيَنۡهَىٰهُمۡ عَنِ ٱلۡمُنكَرِ وَيُحِلُّ لَهُمُ ٱلطَّيِّبَٰتِ وَيُحَرِّمُ عَلَيۡهِمُ ٱلۡخَبَٰٓئِثَ وَيَضَعُ عَنۡهُمۡ إِصۡرَهُمۡ وَٱلۡأَغۡلَٰلَ ٱلَّتِي كَانَتۡ عَلَيۡهِمۡۚ فَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ بِهِۦ وَعَزَّرُوهُ وَنَصَرُوهُ وَٱتَّبَعُواْ ٱلنُّورَ ٱلَّذِيٓ أُنزِلَ مَعَهُۥٓ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ

157. ለእነዚያ ያንን እነርሱ ዘንድ በተውራትና በኢንጂል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብን መልዕክተኛ የሚከተሉ ለሆኑ (ሁሉ በእርግጥ እጽፋታለሁ):: በበጎ ሥራ ያዛቸዋል:: ከክፉም ነገር ይከለክላቸዋል:: መልካም ነገሮችንም ለእነርሱ ይፈቅድላቸዋል:: መጥፎ ነገሮችንም በነሱ ላይ እርም ያደርግባቸዋል:: ከእነርሱም ላይ ሸክማቸውንና እነዚያንም በእነርሱ ላይ የነበሩትን እንደ እንዛዝላ ይከብዱ የነበሩ ከባድ ህግጋትን ያነሳላቸዋል:: እነዚያ በእርሱ ያመኑ፤ ያከበሩት፤ የረዱትና ያንን ከርሱ ጋር የተወረደውን ብርሃን የተከተሉ ሁሉ እነዚያ እነርሱ ከቅጣት የሚድኑ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
158 : 7

قُلۡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنِّي رَسُولُ ٱللَّهِ إِلَيۡكُمۡ جَمِيعًا ٱلَّذِي لَهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ يُحۡيِۦ وَيُمِيتُۖ فَـَٔامِنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِ ٱلنَّبِيِّ ٱلۡأُمِّيِّ ٱلَّذِي يُؤۡمِنُ بِٱللَّهِ وَكَلِمَٰتِهِۦ وَٱتَّبِعُوهُ لَعَلَّكُمۡ تَهۡتَدُونَ

158. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎች ሆይ! እኔ ወደ እናንተ ወደ ሁላችሁም የአላህ መልዕክተኛ ነኝ:: እርሱም ያ የሰማያትና የምድር ንግስና ለእርሱ ብቻ የሆነ ነው:: እርሱ እንጂ ሌላ አምላክ የለም:: ህያው ያደርጋል:: ይገድላልም:: በአላህ በዚያም በአላህና በቃላቶቹ በሚያምነው የማይጽፍ የማያነብ በሆነው መልዕክተኛውም እመኑ:: ወደ ቅኑ መንገድ ትመሩ ዘንድም ተከተሉት።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
159 : 7

وَمِن قَوۡمِ مُوسَىٰٓ أُمَّةٞ يَهۡدُونَ بِٱلۡحَقِّ وَبِهِۦ يَعۡدِلُونَ

159. ከሙሳ ህዝቦች መካከል በእውነት የሚመሩና በእውነት ፍርድን የሚያስተካከሉ ቡድኖችም አሉ:: info
التفاسير: