د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي

አዝ ዛሪያት

external-link copy
1 : 51

وَٱلذَّٰرِيَٰتِ ذَرۡوٗا

1. መበተንን በታኝ በሆኑት (ንፋሶች) እምላለሁ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 51

فَٱلۡحَٰمِلَٰتِ وِقۡرٗا

2. ከባድ ዝናብን ተሸካሚዎች በሆኑትም (ዳመናዎች)፤ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 51

فَٱلۡجَٰرِيَٰتِ يُسۡرٗا

3. ገር መንሻለልን ተንሻላዩች በሆኑትም (መርከቦች) እምላለሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 51

فَٱلۡمُقَسِّمَٰتِ أَمۡرًا

4. ጉዳይን ሁሉ አከፋፋዮች በሆኑትም (መላዕክት) እምላለሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 51

إِنَّمَا تُوعَدُونَ لَصَادِقٞ

5. የምተቀጠሩት ትንሳኤ እውነት ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 51

وَإِنَّ ٱلدِّينَ لَوَٰقِعٞ

6. (እንደየስራው) ዋጋን ማግኘትም የማይቀር ነው። info
التفاسير:

external-link copy
7 : 51

وَٱلسَّمَآءِ ذَاتِ ٱلۡحُبُكِ

7.የ(ከዋክብት) መንገዶች ባለቤት በሆነችው ሰማይ እምላለሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 51

إِنَّكُمۡ لَفِي قَوۡلٖ مُّخۡتَلِفٖ

8. እናንተ በተለያየ ቃል ውስጥ ናችሁ። info
التفاسير:

external-link copy
9 : 51

يُؤۡفَكُ عَنۡهُ مَنۡ أُفِكَ

9. ከእርሱ የሚዝዞር ሰው ይዝዞራል:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 51

قُتِلَ ٱلۡخَرَّٰصُونَ

10. በግምት የሚናገሩ ውሸታሞች ተረገሙ:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 51

ٱلَّذِينَ هُمۡ فِي غَمۡرَةٖ سَاهُونَ

11. እነዚያ እነርሱ በሚሸፍን ስህተት ውስጥ ዘንጊዎች የሆኑት:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 51

يَسۡـَٔلُونَ أَيَّانَ يَوۡمُ ٱلدِّينِ

12. የዋጋ መስጫው ቀን መቼ እንደሆነ ይጠይቃሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 51

يَوۡمَ هُمۡ عَلَى ٱلنَّارِ يُفۡتَنُونَ

13. (እነርሱ) በእሳት ላይ በሚፈተኑበት ቀን ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 51

ذُوقُواْ فِتۡنَتَكُمۡ هَٰذَا ٱلَّذِي كُنتُم بِهِۦ تَسۡتَعۡجِلُونَ

14. «መከራችሁን ቅመሱ ይህ ያ በእርሱ ትቻኮሉበት የነበራችሁት ነው» (ይባላሉ):: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 51

إِنَّ ٱلۡمُتَّقِينَ فِي جَنَّٰتٖ وَعُيُونٍ

15. አላህን ፈሪዎቹ በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 51

ءَاخِذِينَ مَآ ءَاتَىٰهُمۡ رَبُّهُمۡۚ إِنَّهُمۡ كَانُواْ قَبۡلَ ذَٰلِكَ مُحۡسِنِينَ

16. ያንን ጌታቸው የሰጣቸውን ተቀባዮች ሆነው በገነት ውስጥ ይሆናሉ:: እነርሱ ከዚህ በፊት መልካም ሰሪዎች ነበሩና:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 51

كَانُواْ قَلِيلٗا مِّنَ ٱلَّيۡلِ مَا يَهۡجَعُونَ

17. ከሌሊቱ ጥቂቱን ብቻ ይተኙ ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 51

وَبِٱلۡأَسۡحَارِ هُمۡ يَسۡتَغۡفِرُونَ

18. በሌሊቱ መጨረሻዎችም እነርሱ ምህረትን ይለምናሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
19 : 51

وَفِيٓ أَمۡوَٰلِهِمۡ حَقّٞ لِّلسَّآئِلِ وَٱلۡمَحۡرُومِ

19. በገንዘቦቻቸዉም ውስጥ ለለማኝና ከልመና ለተከለከለም (በችሮታቸው) መብት አለ። info
التفاسير:

external-link copy
20 : 51

وَفِي ٱلۡأَرۡضِ ءَايَٰتٞ لِّلۡمُوقِنِينَ

20. በምድርም ውስጥ ለሚያረጋግጡ ሰዎች አያሌ ምልክቶች አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 51

وَفِيٓ أَنفُسِكُمۡۚ أَفَلَا تُبۡصِرُونَ

21. (ሰዎች ሆይ!) በነፍሶቻችሁም ውስጥ አያሌ ምልክቶች አሉ:: ታዲያ አትመለከቱምን? info
التفاسير:

external-link copy
22 : 51

وَفِي ٱلسَّمَآءِ رِزۡقُكُمۡ وَمَا تُوعَدُونَ

22. ሲሳያችሁም የምትቀጠሩት (ፍዳና ምንዳ) በሰማይ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
23 : 51

فَوَرَبِّ ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِ إِنَّهُۥ لَحَقّٞ مِّثۡلَ مَآ أَنَّكُمۡ تَنطِقُونَ

23. በሰማይና በምድር ጌታም እምላለሁ። እርሱ እናንተ እንደምትናገሩት ብጤ እርግጠኛ (እውነት) ነው። info
التفاسير:

external-link copy
24 : 51

هَلۡ أَتَىٰكَ حَدِيثُ ضَيۡفِ إِبۡرَٰهِيمَ ٱلۡمُكۡرَمِينَ

24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የተከበሩት የኢብራሂም እንግዶች ወሬ መጥቶሃልን? info
التفاسير:

external-link copy
25 : 51

إِذۡ دَخَلُواْ عَلَيۡهِ فَقَالُواْ سَلَٰمٗاۖ قَالَ سَلَٰمٞ قَوۡمٞ مُّنكَرُونَ

25. በእርሱም ላይ በገቡና «ሰላም» ባሉት ጊዜ ምን እንደሆነ አስታውስ። ሰላም ግና ያልታወቃችሁ ህዝቦች ናችሁ አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
26 : 51

فَرَاغَ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِۦ فَجَآءَ بِعِجۡلٖ سَمِينٖ

26. ወደ ቤተሰቡም ተዘነበለና ወዲያውም የሰባ ወይፈን አመጣ:: info
التفاسير:

external-link copy
27 : 51

فَقَرَّبَهُۥٓ إِلَيۡهِمۡ قَالَ أَلَا تَأۡكُلُونَ

27. ከዚያ ወደ እነርሱ (አዘጋጅቶ) አቀረበውና «አትበሉም ወይ? አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
28 : 51

فَأَوۡجَسَ مِنۡهُمۡ خِيفَةٗۖ قَالُواْ لَا تَخَفۡۖ وَبَشَّرُوهُ بِغُلَٰمٍ عَلِيمٖ

28. ከእነርሱ መፍራትን በልቡ አሳደረ። «አትፍራ» አሉትም በአዋቂ ልጅም አበስሩት:: info
التفاسير:

external-link copy
29 : 51

فَأَقۡبَلَتِ ٱمۡرَأَتُهُۥ فِي صَرَّةٖ فَصَكَّتۡ وَجۡهَهَا وَقَالَتۡ عَجُوزٌ عَقِيمٞ

29. ሚስቱም (በደስታ) እየጮኸች መጣች፤ ፊቷንም መታች «መካን አሮጊት (ነኝ)» አለችም። info
التفاسير:

external-link copy
30 : 51

قَالُواْ كَذَٰلِكِ قَالَ رَبُّكِۖ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡحَكِيمُ ٱلۡعَلِيمُ

30. እነርሱም «ጌታሽ 'እንዲሁ (ይሁን)' ብሏል። እነሆ እርሱ ጥበበኛና ሁሉን አዋቂ ነው» አሏት:: info
التفاسير:

external-link copy
31 : 51

۞ قَالَ فَمَا خَطۡبُكُمۡ أَيُّهَا ٱلۡمُرۡسَلُونَ

31. «እናንተ መልዕክተኞች ሆይ! ታዲያ ነገራችሁ ምንድን ነው?» አላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
32 : 51

قَالُوٓاْ إِنَّآ أُرۡسِلۡنَآ إِلَىٰ قَوۡمٖ مُّجۡرِمِينَ

32. እነርሱም አሉ: «እኛ ወደ አመጸኖች ህዝቦች ተልከናል። info
التفاسير:

external-link copy
33 : 51

لِنُرۡسِلَ عَلَيۡهِمۡ حِجَارَةٗ مِّن طِينٖ

33. «በእነርሱ ላይ ከጭቃ የሆኑ ድንጋዮችን ልንለቅባቸው ተላክን። info
التفاسير:

external-link copy
34 : 51

مُّسَوَّمَةً عِندَ رَبِّكَ لِلۡمُسۡرِفِينَ

34. «በጌታህ ዘንድ ለድንበር አላፊዎቹ በየስማቸው ምልክት የተደረገባት ስትሆን።» አሉ info
التفاسير:

external-link copy
35 : 51

فَأَخۡرَجۡنَا مَن كَانَ فِيهَا مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

35. ከምዕመናም በእርሷ በከተማቸው ውስጥ የነበሩትን አወጣን:: info
التفاسير:

external-link copy
36 : 51

فَمَا وَجَدۡنَا فِيهَا غَيۡرَ بَيۡتٖ مِّنَ ٱلۡمُسۡلِمِينَ

36. በውስጧም ከአንድ ቤት ቤተሰቦች በስተቀር ሙስሊሞችን አላገኘንም:: info
التفاسير:

external-link copy
37 : 51

وَتَرَكۡنَا فِيهَآ ءَايَةٗ لِّلَّذِينَ يَخَافُونَ ٱلۡعَذَابَ ٱلۡأَلِيمَ

37. በውስጧም ለእነዚያ አሳማሚውን ቅጣት ለሚፈሩት ምልክትን አስቀረን:: info
التفاسير:

external-link copy
38 : 51

وَفِي مُوسَىٰٓ إِذۡ أَرۡسَلۡنَٰهُ إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ بِسُلۡطَٰنٖ مُّبِينٖ

38. በሙሳ ወሬ ውስጥም ወደ ፈርዖን በግልጽ ማስረጃ በላክነው ጊዜ (ምልክትን አደረግን):: info
التفاسير:

external-link copy
39 : 51

فَتَوَلَّىٰ بِرُكۡنِهِۦ وَقَالَ سَٰحِرٌ أَوۡ مَجۡنُونٞ

39. ከድጋፉ (ከሰራዊቱ) ጋርም ከእምነት ዞረ:: «እርሱ ድግምተኛ ወይም እብድ ነው» አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
40 : 51

فَأَخَذۡنَٰهُ وَجُنُودَهُۥ فَنَبَذۡنَٰهُمۡ فِي ٱلۡيَمِّ وَهُوَ مُلِيمٞ

40. እርሱንም ሰራዊቱንም ያዝናቸው እርሱ ተወቃሽ ሲሆን በባህር ውስጥ ጣልናቸውም። info
التفاسير:

external-link copy
41 : 51

وَفِي عَادٍ إِذۡ أَرۡسَلۡنَا عَلَيۡهِمُ ٱلرِّيحَ ٱلۡعَقِيمَ

41. በዓድም በእነርሱ ላይ መካን (የሆነች) ንፋስን በላክን ጊዜ ምልክት አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
42 : 51

مَا تَذَرُ مِن شَيۡءٍ أَتَتۡ عَلَيۡهِ إِلَّا جَعَلَتۡهُ كَٱلرَّمِيمِ

42. በላዩ ላይ የመጣችበትን ማንኛዉንም ነገር እንደበሰበሰ አጥነት ያደረገችው ብትሆን እንጂ አትተወዉም። info
التفاسير:

external-link copy
43 : 51

وَفِي ثَمُودَ إِذۡ قِيلَ لَهُمۡ تَمَتَّعُواْ حَتَّىٰ حِينٖ

43. በሰሙድም ለእነርሱ «እስከ ጊዜ (ሞታችሁ) ድረስ ተጣቀሙ።» በተባሉ ጊዜ (ምልክት አለ)። info
التفاسير:

external-link copy
44 : 51

فَعَتَوۡاْ عَنۡ أَمۡرِ رَبِّهِمۡ فَأَخَذَتۡهُمُ ٱلصَّٰعِقَةُ وَهُمۡ يَنظُرُونَ

44. ከጌታቸው ትዕዘዝም ኮሩ:: እነርሱም እያዩ ጩኸቷ ያዘቻቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
45 : 51

فَمَا ٱسۡتَطَٰعُواْ مِن قِيَامٖ وَمَا كَانُواْ مُنتَصِرِينَ

45. መቆምንም አልቻሉም:: እርዳታ የሚደረግላቸውም አልነበሩም:: info
التفاسير:

external-link copy
46 : 51

وَقَوۡمَ نُوحٖ مِّن قَبۡلُۖ إِنَّهُمۡ كَانُواْ قَوۡمٗا فَٰسِقِينَ

46. የኑህንም ህዝቦች (ከዚህ በፊት አጠፋን) እነርሱ አመጸኞች ህዝቦች ነበሩና:: info
التفاسير:

external-link copy
47 : 51

وَٱلسَّمَآءَ بَنَيۡنَٰهَا بِأَيۡيْدٖ وَإِنَّا لَمُوسِعُونَ

47. ሰማይንም በሀይል ገነባናት:: እኛም በእርግጥ የምናስፋት ነን:: info
التفاسير:

external-link copy
48 : 51

وَٱلۡأَرۡضَ فَرَشۡنَٰهَا فَنِعۡمَ ٱلۡمَٰهِدُونَ

48. ምድርንም ዘረጋናት ምን ያማርንም ዘርጊዎች ነን:: info
التفاسير:

external-link copy
49 : 51

وَمِن كُلِّ شَيۡءٍ خَلَقۡنَا زَوۡجَيۡنِ لَعَلَّكُمۡ تَذَكَّرُونَ

49. ትገነዘቡም ዘንድ ከነገሩ ሁሉ ሁለት ተቃራኒ አይነትን ፈጠርን:: info
التفاسير:

external-link copy
50 : 51

فَفِرُّوٓاْ إِلَى ٱللَّهِۖ إِنِّي لَكُم مِّنۡهُ نَذِيرٞ مُّبِينٞ

50. ወደ አላህም ሽሹ እኔ ለእናንተ ከእርሱ ግልጽ አስጠንቃቂ ነኝ። info
التفاسير:

external-link copy
51 : 51

وَلَا تَجۡعَلُواْ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَۖ إِنِّي لَكُم مِّنۡهُ نَذِيرٞ مُّبِينٞ

51. ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አታድርጉ:: እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላኩ:: ግልጽ አስፈራሪ ነኝና:: info
التفاسير:

external-link copy
52 : 51

كَذَٰلِكَ مَآ أَتَى ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِم مِّن رَّسُولٍ إِلَّا قَالُواْ سَاحِرٌ أَوۡ مَجۡنُونٌ

52. ልክ እንደዚሁ እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ከመልዕክተኛ ማንም አልመጣቸዉም:: «እርሱ ድግምተኛ ወይም እብድ ነው» ያሉ ቢሆን እንጂ:: info
التفاسير:

external-link copy
53 : 51

أَتَوَاصَوۡاْ بِهِۦۚ بَلۡ هُمۡ قَوۡمٞ طَاغُونَ

53. በእርሱ (በዚህ ቃል) አደራ ተባብለዋልን? ይልቁን እነርሱ ጥጋበኞች ህዝቦች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
54 : 51

فَتَوَلَّ عَنۡهُمۡ فَمَآ أَنتَ بِمَلُومٖ

54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ዘወር በል (ተዋቸው)፤ አንተ ምንም ተወቃሽ አይደለህምና:: info
التفاسير:

external-link copy
55 : 51

وَذَكِّرۡ فَإِنَّ ٱلذِّكۡرَىٰ تَنفَعُ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

55. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ገስጽም ግሳጼ አማኞችን ትጠቅማለችና:: info
التفاسير:

external-link copy
56 : 51

وَمَا خَلَقۡتُ ٱلۡجِنَّ وَٱلۡإِنسَ إِلَّا لِيَعۡبُدُونِ

56. ጋኔንና ሰዉን ሊገዙኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
57 : 51

مَآ أُرِيدُ مِنۡهُم مِّن رِّزۡقٖ وَمَآ أُرِيدُ أَن يُطۡعِمُونِ

57. ከእነርሱም ምንም ሲሳይን አልፈልግም:: እንዲመግቡኝም አልፈልግም:: info
التفاسير:

external-link copy
58 : 51

إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلرَّزَّاقُ ذُو ٱلۡقُوَّةِ ٱلۡمَتِينُ

58. አላህ ሰጪና የብርቱ ሀይል ባለቤት ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
59 : 51

فَإِنَّ لِلَّذِينَ ظَلَمُواْ ذَنُوبٗا مِّثۡلَ ذَنُوبِ أَصۡحَٰبِهِمۡ فَلَا يَسۡتَعۡجِلُونِ

59. ለእነዚያም ለበደሉት እንደ ጓደኞቻቸው ፋንታ ብጤ የቅጣት ፋንታ አለላቸው:: ስለዚህ አያስቸኩሉኝ:: info
التفاسير:

external-link copy
60 : 51

فَوَيۡلٞ لِّلَّذِينَ كَفَرُواْ مِن يَوۡمِهِمُ ٱلَّذِي يُوعَدُونَ

60. ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከዚያ ከሚቀጠሩት ቀናቸው ወዩላቸው:: info
التفاسير: