د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي

አል ሑጅራት

external-link copy
1 : 49

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تُقَدِّمُواْ بَيۡنَ يَدَيِ ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦۖ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٞ

1. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልዕክተኛው ፊት ነፍሶቻችሁን አታስቀድሙ:: አላህንም ፍሩ:: አላህ ለሚባለው ሁሉ ሰሚ ለሚፈጸመው ነገር ሁሉ አዋቂ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 49

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَرۡفَعُوٓاْ أَصۡوَٰتَكُمۡ فَوۡقَ صَوۡتِ ٱلنَّبِيِّ وَلَا تَجۡهَرُواْ لَهُۥ بِٱلۡقَوۡلِ كَجَهۡرِ بَعۡضِكُمۡ لِبَعۡضٍ أَن تَحۡبَطَ أَعۡمَٰلُكُمۡ وَأَنتُمۡ لَا تَشۡعُرُونَ

2. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ድምፆቻችሁን ከነብዩ ድምጽ በላይ ከፍ አታድርጉ:: ከፊላችሁ ለከፊሉ እንደሚጮህም ሁሉ በንግግር ለርሱ ስትናገሩ አትጩሁ:: እናንተ የማታውቁ ስትሆኑ ስራዎቻችሁ እንዳይበላሹ (ከዚህ ተከልከሉ):: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 49

إِنَّ ٱلَّذِينَ يَغُضُّونَ أَصۡوَٰتَهُمۡ عِندَ رَسُولِ ٱللَّهِ أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ ٱمۡتَحَنَ ٱللَّهُ قُلُوبَهُمۡ لِلتَّقۡوَىٰۚ لَهُم مَّغۡفِرَةٞ وَأَجۡرٌ عَظِيمٌ

3. እነዚያ በአላህ መልዕክተኛ ዘንድ ድምፆቻቸውን ዝቅ የሚያደርጉ እነዚህ እነዚያ አላህ ልቦቻቸውን ለፍርሃት የፈተናቸው ናቸው:: ለእነርሱም ምህረትና ታላቅ ምንዳ አለላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 49

إِنَّ ٱلَّذِينَ يُنَادُونَكَ مِن وَرَآءِ ٱلۡحُجُرَٰتِ أَكۡثَرُهُمۡ لَا يَعۡقِلُونَ

4. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ከመኖሪያ ክፍሎቹ ውጭ ሆነው የሚጠሩህ አብዛሀኞቻቸው አያውቁም:: info
التفاسير: