د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي

د مخ نمبر: 473:467 close

external-link copy
59 : 40

إِنَّ ٱلسَّاعَةَ لَأٓتِيَةٞ لَّا رَيۡبَ فِيهَا وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يُؤۡمِنُونَ

59. ሰዓቲቱ በእርግጥ መጪ ናት:: በእርሷ ጥርጥር የለም:: ግን አብዛሀኞቹ ሰዎች አያምኑም:: info
التفاسير:

external-link copy
60 : 40

وَقَالَ رَبُّكُمُ ٱدۡعُونِيٓ أَسۡتَجِبۡ لَكُمۡۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَسۡتَكۡبِرُونَ عَنۡ عِبَادَتِي سَيَدۡخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ

60. (ባሮቼ ሆይ!) ጌታችሁም አለ: «ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና። እነዚያ እኔን ከመገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ገሀነም በእርግጥ ይገባሉ።» info
التفاسير:

external-link copy
61 : 40

ٱللَّهُ ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيۡلَ لِتَسۡكُنُواْ فِيهِ وَٱلنَّهَارَ مُبۡصِرًاۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَذُو فَضۡلٍ عَلَى ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَشۡكُرُونَ

61. አላህ ያ ለእናንተ ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት ጨለማ፤ ቀንኑ ደግሞ ልትሰሩበት የሚያሳይ ብርሃን ያደረገላችሁ ነው:: አላህ በሰዎች ላይ በእርግጥ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነውና:: ግን አብዛሀኞቹ ሰዎች አያመሰግኑም:: info
التفاسير:

external-link copy
62 : 40

ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمۡ خَٰلِقُ كُلِّ شَيۡءٖ لَّآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ فَأَنَّىٰ تُؤۡفَكُونَ

62. ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው:: የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው:: ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: ታዲያ ከእምነት ወዴት ትመለሳላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
63 : 40

كَذَٰلِكَ يُؤۡفَكُ ٱلَّذِينَ كَانُواْ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ يَجۡحَدُونَ

63. ልክ እንደዚሁ እነዚያ በአላህ አናቅጽ ይክዱ የነበሩት ከእምነት ይመለሳሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
64 : 40

ٱللَّهُ ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُمُ ٱلۡأَرۡضَ قَرَارٗا وَٱلسَّمَآءَ بِنَآءٗ وَصَوَّرَكُمۡ فَأَحۡسَنَ صُوَرَكُمۡ وَرَزَقَكُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَٰتِۚ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمۡۖ فَتَبَارَكَ ٱللَّهُ رَبُّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

64. (ሰዎች ሆይ)! አላህ ያ ምድርን መርጊያ ሰማይንም ጣሪያ ያደረገላችሁ ነው፡፡ የቀረፃችሁም ቅርፃችሁንም ያሳመረ፤ ከጣፋጭ ሲሳዮችም የሰጣችሁ ነው:: ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው። የዓለማትም ጌታ አላህ ላቀ:: info
التفاسير:

external-link copy
65 : 40

هُوَ ٱلۡحَيُّ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ فَٱدۡعُوهُ مُخۡلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَۗ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

65. እርሱ ብቻ ሁል ጊዜ ህያው ነው:: ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: ሃይማኖትንም ለርሱ ያጠራችሁ ስትሆኑ «ምስጋና ሁሉ ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው›› የምትሉ ሆናችሁ ተገዙት:: info
التفاسير:

external-link copy
66 : 40

۞ قُلۡ إِنِّي نُهِيتُ أَنۡ أَعۡبُدَ ٱلَّذِينَ تَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ لَمَّا جَآءَنِيَ ٱلۡبَيِّنَٰتُ مِن رَّبِّي وَأُمِرۡتُ أَنۡ أُسۡلِمَ لِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

66. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ ከጌታዬ አስረጂዎች በመጡልኝ ጊዜ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዙዋቸውን እንዳልገዛ ተከልክያለሁ፤ ለዓለማትም ጌታ ብቻም እንድገዛ ታዝዣለሁ።» በላቸው:: info
التفاسير: