د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي

د مخ نمبر: 355:350 close

external-link copy
44 : 24

يُقَلِّبُ ٱللَّهُ ٱلَّيۡلَ وَٱلنَّهَارَۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَعِبۡرَةٗ لِّأُوْلِي ٱلۡأَبۡصَٰرِ

44. አላህ ሌሊትንና ቀንን ያገላብጣል፤ በዚህም ለአስተዋዮች በእርግጥ ማስረጃ አለበት። info
التفاسير:

external-link copy
45 : 24

وَٱللَّهُ خَلَقَ كُلَّ دَآبَّةٖ مِّن مَّآءٖۖ فَمِنۡهُم مَّن يَمۡشِي عَلَىٰ بَطۡنِهِۦ وَمِنۡهُم مَّن يَمۡشِي عَلَىٰ رِجۡلَيۡنِ وَمِنۡهُم مَّن يَمۡشِي عَلَىٰٓ أَرۡبَعٖۚ يَخۡلُقُ ٱللَّهُ مَا يَشَآءُۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ

45. አላህም ተንቀሳቃሽን ሁሉ ከውሃ ፈጠረ:: ከእነርሱም መካከል በሆዱ ላይ የሚሄድ አለ፤ ከእነርሱም መካከል በሁለት እግሮቹ ላይ የሚሄድ አለ፤ ከእነርሱም መካከል በአራት እግሩ የሚሄድ አለ:: አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
46 : 24

لَّقَدۡ أَنزَلۡنَآ ءَايَٰتٖ مُّبَيِّنَٰتٖۚ وَٱللَّهُ يَهۡدِي مَن يَشَآءُ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ

46. አብራሪን አናቅጽ በእርግጥ አወረድን፤ አላህ የሚሻውን ወደ ቀጥተኛ መንገድ ይመራዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
47 : 24

وَيَقُولُونَ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَبِٱلرَّسُولِ وَأَطَعۡنَا ثُمَّ يَتَوَلَّىٰ فَرِيقٞ مِّنۡهُم مِّنۢ بَعۡدِ ذَٰلِكَۚ وَمَآ أُوْلَٰٓئِكَ بِٱلۡمُؤۡمِنِينَ

47. (አስመሳዮች) «በአላህና በመልዕክተኛው አምነናል ታዘናልም» ይላሉ። ከዚያም ከዚህ በኋላ ከእነርሱ ከፊሉ ይሸሻል:: እነዚያም ትክክለኛ አማኞች አይደሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
48 : 24

وَإِذَا دُعُوٓاْ إِلَى ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ لِيَحۡكُمَ بَيۡنَهُمۡ إِذَا فَرِيقٞ مِّنۡهُم مُّعۡرِضُونَ

48. ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛዉም በመካከላቸው ለሚከሰቱ ጉዳዮች ሊፈርድ በተጠሩ ጊዜ ከእነርሱ መካከል ከፊሉ ወዲያውኑ ይሸሻሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
49 : 24

وَإِن يَكُن لَّهُمُ ٱلۡحَقُّ يَأۡتُوٓاْ إِلَيۡهِ مُذۡعِنِينَ

49. እውነቱም (ሐቁ) ለእነርሱ ቢሆን ወደ እርሱ ታዛዣች ሆነው ይመጣሉ። info
التفاسير:

external-link copy
50 : 24

أَفِي قُلُوبِهِم مَّرَضٌ أَمِ ٱرۡتَابُوٓاْ أَمۡ يَخَافُونَ أَن يَحِيفَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِمۡ وَرَسُولُهُۥۚ بَلۡ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ

50. በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ አለን? ወይስ በነብይነቱ ተጠራጠሩን? ወይስ አላህና መልዕክተኛው በእነርሱ ላይ የሚበድሉ መሆንን ይፈራሉን? ይልቁንም እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
51 : 24

إِنَّمَا كَانَ قَوۡلَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ إِذَا دُعُوٓاْ إِلَى ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ لِيَحۡكُمَ بَيۡنَهُمۡ أَن يَقُولُواْ سَمِعۡنَا وَأَطَعۡنَاۚ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ

51. የምዕምናን ቃል ግን የነበረው ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው በመካከላቸው ሊፈርድ በተጠሩ ጊዜ «ሰማን ታዘዝንም» ማለት ብቻ ነው:: እነዚህ ማለት እነዚያ የፈለጉትን የሚያገኙቱ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
52 : 24

وَمَن يُطِعِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَيَخۡشَ ٱللَّهَ وَيَتَّقۡهِ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡفَآئِزُونَ

52. አላህንና መልዕክተኛውን የሚታዘዝ፤ አላህንም የሚፈራና ቁጣውን የሚጠነቀቀው፤ ፍላጎታቸውን የሚያገኙ እነዚያ እነርሱ ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
53 : 24

۞ وَأَقۡسَمُواْ بِٱللَّهِ جَهۡدَ أَيۡمَٰنِهِمۡ لَئِنۡ أَمَرۡتَهُمۡ لَيَخۡرُجُنَّۖ قُل لَّا تُقۡسِمُواْۖ طَاعَةٞ مَّعۡرُوفَةٌۚ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِيرُۢ بِمَا تَعۡمَلُونَ

53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለዘመቻ ብታዛቸው በእርግጥ እንደሚወጡ የጠነከሩ መሓላዎቻቸውን በአላህ ስም ይምላሉ፤ «አትማሉ:: የታወቀ የንፍቅና መታዘዝ ነውና:: አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው።» በላቸው። info
التفاسير: