د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي

د مخ نمبر:close

external-link copy
28 : 23

فَإِذَا ٱسۡتَوَيۡتَ أَنتَ وَمَن مَّعَكَ عَلَى ٱلۡفُلۡكِ فَقُلِ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِي نَجَّىٰنَا مِنَ ٱلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ

28. አንተም አብረውህ ካሉት ፍጡሮች ጋር በታንኳይቱ ላይ በተደላደልክ ጊዜ በል: «ምስጋና ሁሉ ለዚያ ከበደለኛ ህዝቦች ላዳነን አላህ ይገባው። info
التفاسير:

external-link copy
29 : 23

وَقُل رَّبِّ أَنزِلۡنِي مُنزَلٗا مُّبَارَكٗا وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلۡمُنزِلِينَ

29. «ጌታዬ ሆይ! ብሩክ የሆነን ማውረድ አውርደኝ:: አንተም ከአደላዳዮች ሁሉ በላጭ ነህና።» በል። info
التفاسير:

external-link copy
30 : 23

إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ وَإِن كُنَّا لَمُبۡتَلِينَ

30. በዚህ ውስጥ ለሃያልነታችን አያሌ ተዓምራት አሉበት:: እነሆ እኛ (የኑሕን ሰዎች) ፈታኞች ነበርን:: info
التفاسير:

external-link copy
31 : 23

ثُمَّ أَنشَأۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِمۡ قَرۡنًا ءَاخَرِينَ

31. ከዚያ ከኋላቸው ሌሎችን የክፍለ ዘመናት ህዝቦች አስገኘን:: info
التفاسير:

external-link copy
32 : 23

فَأَرۡسَلۡنَا فِيهِمۡ رَسُولٗا مِّنۡهُمۡ أَنِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥٓۚ أَفَلَا تَتَّقُونَ

32. በውስጣቸዉም ከእነርሱ የሆኑን መልዕክተኛ አላህን ተገዙ ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የላችሁም:: አትጠነቀቁምን? በማለት ላክን። info
التفاسير:

external-link copy
33 : 23

وَقَالَ ٱلۡمَلَأُ مِن قَوۡمِهِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَكَذَّبُواْ بِلِقَآءِ ٱلۡأٓخِرَةِ وَأَتۡرَفۡنَٰهُمۡ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا مَا هَٰذَآ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُكُمۡ يَأۡكُلُ مِمَّا تَأۡكُلُونَ مِنۡهُ وَيَشۡرَبُ مِمَّا تَشۡرَبُونَ

33. ከህዝቦቹም እነዚያ የካዱት ሰዎች በመጨረሻይቱም ቀን መገናኘት ያስተባበሉት በቅርቢቱም ህይወት ያቀማጠልናቸው ታላላቅ ሰዎች አሉ: «ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም። ከምትበሉት ምግብ ይበላል፤ ከምትጠጡትም ውሃ ይጠጣል። info
التفاسير:

external-link copy
34 : 23

وَلَئِنۡ أَطَعۡتُم بَشَرٗا مِّثۡلَكُمۡ إِنَّكُمۡ إِذٗا لَّخَٰسِرُونَ

34. «የናንተው ብጤያችሁ የሆነን ሰው ብትታዘዙ በእርግጥ የተሞኛችሁ ናችሁ። info
التفاسير:

external-link copy
35 : 23

أَيَعِدُكُمۡ أَنَّكُمۡ إِذَا مِتُّمۡ وَكُنتُمۡ تُرَابٗا وَعِظَٰمًا أَنَّكُم مُّخۡرَجُونَ

35. «‹እናንተ ሞታችሁ አፈርና አጥንቶችም በሆናችሁ ጊዜ እናንተ ከመቃብር ትወጣላችሁ› በማለት ያስፈራራችኋልን? info
التفاسير:

external-link copy
36 : 23

۞ هَيۡهَاتَ هَيۡهَاتَ لِمَا تُوعَدُونَ

36. «ያ የምትስፈራሩበት ነገር ከእውነት ራቀ፤ በጣም ራቀ info
التفاسير:

external-link copy
37 : 23

إِنۡ هِيَ إِلَّا حَيَاتُنَا ٱلدُّنۡيَا نَمُوتُ وَنَحۡيَا وَمَا نَحۡنُ بِمَبۡعُوثِينَ

37. «እርሷ (ህይወት) ማለት ቅርቢቱ ህይወታችን ብቻ እንጂ ሌላ አይደለችም:: እንሞታለን። ህያዉም እንሆናለን። እኛም ፈጽሞ ተቀስቃሾች አይደለንም" (አሉ)። info
التفاسير:

external-link copy
38 : 23

إِنۡ هُوَ إِلَّا رَجُلٌ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبٗا وَمَا نَحۡنُ لَهُۥ بِمُؤۡمِنِينَ

38. «እርሱ በአላህ ላይ ውሸትን የቀጠፈ ሰው እንጂ ሌላ አይደለም:: እኛም በእርሱ አማኞች አይደለንም።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
39 : 23

قَالَ رَبِّ ٱنصُرۡنِي بِمَا كَذَّبُونِ

39. መልዕክተኛዉም «ጌታዬ ሆይ! ስላስተባበሉኝ በእነርሱ ላይ እርዳኝ።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
40 : 23

قَالَ عَمَّا قَلِيلٖ لَّيُصۡبِحُنَّ نَٰدِمِينَ

40. አላህም «ከጥቂት ጊዜ በኋላ በጥፋታቸው በእርግጥ ተጸጻቾች ይሆናሉ።» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
41 : 23

فَأَخَذَتۡهُمُ ٱلصَّيۡحَةُ بِٱلۡحَقِّ فَجَعَلۡنَٰهُمۡ غُثَآءٗۚ فَبُعۡدٗا لِّلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ

41. ወዲያዉም (የጥፋት) ጩኸቲቱ በእውነት ያዘቻቸው፤ እንደ ጎርፍ ግብስባሽም አደረግናቸው:: ለበደለኞች ህዝቦችም ከእዝነት መራቅ ተገባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
42 : 23

ثُمَّ أَنشَأۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِمۡ قُرُونًا ءَاخَرِينَ

42. ከዚያም ከእነርሱ በኋላ ሌሎችን የክፍለ ዘመናት ህዝቦች አስገኘን:: info
التفاسير: