د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - محمد صادق

د مخ نمبر: 58:50 close

external-link copy
71 : 3

يَٰٓأَهۡلَ ٱلۡكِتَٰبِ لِمَ تَلۡبِسُونَ ٱلۡحَقَّ بِٱلۡبَٰطِلِ وَتَكۡتُمُونَ ٱلۡحَقَّ وَأَنتُمۡ تَعۡلَمُونَ

«የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ» info
التفاسير:

external-link copy
72 : 3

وَقَالَت طَّآئِفَةٞ مِّنۡ أَهۡلِ ٱلۡكِتَٰبِ ءَامِنُواْ بِٱلَّذِيٓ أُنزِلَ عَلَى ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَجۡهَ ٱلنَّهَارِ وَٱكۡفُرُوٓاْ ءَاخِرَهُۥ لَعَلَّهُمۡ يَرۡجِعُونَ

ከመጽሐፉ ባለቤቶች የኾኑ ጭፍሮችም አሉ፡- «በነዚያ በአመኑት ላይ በተወረደው (ቁርኣን) በቀኑ መጀመሪያ ላይ እመኑበት፡፡ በመጨረሻውም ካዱት፡፡ እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
73 : 3

وَلَا تُؤۡمِنُوٓاْ إِلَّا لِمَن تَبِعَ دِينَكُمۡ قُلۡ إِنَّ ٱلۡهُدَىٰ هُدَى ٱللَّهِ أَن يُؤۡتَىٰٓ أَحَدٞ مِّثۡلَ مَآ أُوتِيتُمۡ أَوۡ يُحَآجُّوكُمۡ عِندَ رَبِّكُمۡۗ قُلۡ إِنَّ ٱلۡفَضۡلَ بِيَدِ ٱللَّهِ يُؤۡتِيهِ مَن يَشَآءُۗ وَٱللَّهُ وَٰسِعٌ عَلِيمٞ

እናንተ የተሰጣችሁትን ብጤ አንድም ሰው መሰጠቱን ወይም እጌታችሁ ዘንድ የሚከራከሩዋችሁ መኾንን ሃይማኖታችሁን ለተከተለ ሰው ቢኾን እንጂ አትመኑ (አትግለጹ አሉ)፡፡ «መምሪያው የአላህ መምሪያ ብቻ ነው» በላቸው፡፡ «ችሮታ በአላህ እጅ ነው፡፡ ለሚሻው ይሰጠዋል፡፡ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
74 : 3

يَخۡتَصُّ بِرَحۡمَتِهِۦ مَن يَشَآءُۗ وَٱللَّهُ ذُو ٱلۡفَضۡلِ ٱلۡعَظِيمِ

በችሮታው (በነቢይነት) የሚሻውን ይመርጣል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
75 : 3

۞ وَمِنۡ أَهۡلِ ٱلۡكِتَٰبِ مَنۡ إِن تَأۡمَنۡهُ بِقِنطَارٖ يُؤَدِّهِۦٓ إِلَيۡكَ وَمِنۡهُم مَّنۡ إِن تَأۡمَنۡهُ بِدِينَارٖ لَّا يُؤَدِّهِۦٓ إِلَيۡكَ إِلَّا مَا دُمۡتَ عَلَيۡهِ قَآئِمٗاۗ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ قَالُواْ لَيۡسَ عَلَيۡنَا فِي ٱلۡأُمِّيِّـۧنَ سَبِيلٞ وَيَقُولُونَ عَلَى ٱللَّهِ ٱلۡكَذِبَ وَهُمۡ يَعۡلَمُونَ

ከመጽሐፉ ሰዎችም በብዙ ገንዘብ ብታምነው ወዳንተ የሚመልስ ሰው አልለ፡፡ ከእነሱም በአንድ ዲናር እንኳ ብታምነው፤ ሁል ጊዜ በርሱ ላይ የምትጠባበቅ ካልኾንክ በስተቀር የማይመልስ ሰው አልለ፡፡ «ይህ በመሃይምናን (በምናደርገው) በእኛ ላይ ምንም መንገድ የለብንም» ስለሚሉ ነው፡፡ እነርሱ እያወቁም በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
76 : 3

بَلَىٰۚ مَنۡ أَوۡفَىٰ بِعَهۡدِهِۦ وَٱتَّقَىٰ فَإِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلۡمُتَّقِينَ

አይደለም (አለባቸው እንጅ)፡፡ በቃል ኪዳኑ የሞላና የተጠነቀቀ ሰው አላህ ጥንቁቆችን ይወዳል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
77 : 3

إِنَّ ٱلَّذِينَ يَشۡتَرُونَ بِعَهۡدِ ٱللَّهِ وَأَيۡمَٰنِهِمۡ ثَمَنٗا قَلِيلًا أُوْلَٰٓئِكَ لَا خَلَٰقَ لَهُمۡ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ وَلَا يُكَلِّمُهُمُ ٱللَّهُ وَلَا يَنظُرُ إِلَيۡهِمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ وَلَا يُزَكِّيهِمۡ وَلَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ

እነዚህ በአላህ ቃል ኪዳንና በመሐላዎቻቸው ጥቂትን ዋጋ የሚለውጡ እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም ምንም ዕድል የላቸውም፡፡ በትንሣኤ ቀንም አላህ አያነጋግራቸውም፡፡ ወደ እነርሱም አይመለከትም አያነጻቸውምም፡፡ ለነሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡ info
التفاسير: