د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - محمد صادق

د مخ نمبر:close

external-link copy
40 : 26

لَعَلَّنَا نَتَّبِعُ ٱلسَّحَرَةَ إِن كَانُواْ هُمُ ٱلۡغَٰلِبِينَ

«ድግምተኞቹን እነሱ አሸናፊዎች ቢኾኑ እንከተል ዘንድ» (ተባለ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
41 : 26

فَلَمَّا جَآءَ ٱلسَّحَرَةُ قَالُواْ لِفِرۡعَوۡنَ أَئِنَّ لَنَا لَأَجۡرًا إِن كُنَّا نَحۡنُ ٱلۡغَٰلِبِينَ

«ድግምተኞቹም በመጡ ጊዜ ለፈርዖን እኛ አሸናፊዎች ብንሆን ለእኛ በእርግጥ ዋጋ አለን?» አሉት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
42 : 26

قَالَ نَعَمۡ وَإِنَّكُمۡ إِذٗا لَّمِنَ ٱلۡمُقَرَّبِينَ

«አዎን፤ እናንተም ያን ጊዜ ከባለሟሎቹ ትኾናላችሁ» አላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
43 : 26

قَالَ لَهُم مُّوسَىٰٓ أَلۡقُواْ مَآ أَنتُم مُّلۡقُونَ

ሙሳ «ለእነርሱ እናንተ የምትጥሉትን ጣሉ» አላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
44 : 26

فَأَلۡقَوۡاْ حِبَالَهُمۡ وَعِصِيَّهُمۡ وَقَالُواْ بِعِزَّةِ فِرۡعَوۡنَ إِنَّا لَنَحۡنُ ٱلۡغَٰلِبُونَ

ገመዶቻቸውንና በትሮቻቸውንም ጣሉ፡፡ «በፈርዖንም ክብር ይኹንብን፡፡ እኛ በእርግጥ አሸናፊዎቹ እኛ ነን» አሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
45 : 26

فَأَلۡقَىٰ مُوسَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِيَ تَلۡقَفُ مَا يَأۡفِكُونَ

ሙሳም በትሩን ጣለ፡፡ ወዲያውም እርሷ የሚያስመስሉትን ሁሉ ትውጣለች፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
46 : 26

فَأُلۡقِيَ ٱلسَّحَرَةُ سَٰجِدِينَ

ድግምተኞቹም ሰጋጆች ኾነው ወደቁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
47 : 26

قَالُوٓاْ ءَامَنَّا بِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

(እነሱም) አሉ «በዓለማት ጌታ አመንን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
48 : 26

رَبِّ مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ

«በሙሳና በሃሩን ጌታ፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
49 : 26

قَالَ ءَامَنتُمۡ لَهُۥ قَبۡلَ أَنۡ ءَاذَنَ لَكُمۡۖ إِنَّهُۥ لَكَبِيرُكُمُ ٱلَّذِي عَلَّمَكُمُ ٱلسِّحۡرَ فَلَسَوۡفَ تَعۡلَمُونَۚ لَأُقَطِّعَنَّ أَيۡدِيَكُمۡ وَأَرۡجُلَكُم مِّنۡ خِلَٰفٖ وَلَأُصَلِّبَنَّكُمۡ أَجۡمَعِينَ

(ፈርዖንም) «ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት ለእርሱ አመናችሁን? እርሱ ያ ድግምትን ያስተማራችሁ ታላቃችሁ ነው፡፡ ወደፊትም (የሚያገኛችሁን) በእርግጥ ታውቃላችሁ፡፡ እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን (ቀኝና ግራን) በማናጋት እቆረርጣለሁ፡፡ ሁላችሁንም እሰቅላችኋለሁም» አለ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
50 : 26

قَالُواْ لَا ضَيۡرَۖ إِنَّآ إِلَىٰ رَبِّنَا مُنقَلِبُونَ

(እነርሱም) አሉ «ጉዳት የለብንም፡፡ እኛ ወደ ጌታችን ተመላሾች ነን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
51 : 26

إِنَّا نَطۡمَعُ أَن يَغۡفِرَ لَنَا رَبُّنَا خَطَٰيَٰنَآ أَن كُنَّآ أَوَّلَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

«እኛ የምእምናን መጀመሪያ በመኾናችን ጌታችን ኀጢአቶቻችንን ለእኛ ሊምር እንከጅላለን፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
52 : 26

۞ وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ أَنۡ أَسۡرِ بِعِبَادِيٓ إِنَّكُم مُّتَّبَعُونَ

ወደ ሙሳም «ባሮቼን ይዘህ ሌሊት ኺድ፡፡ እናንተ የሚከተሉዋችሁ ናችሁና» ስንል ላክን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
53 : 26

فَأَرۡسَلَ فِرۡعَوۡنُ فِي ٱلۡمَدَآئِنِ حَٰشِرِينَ

ፈርዖንም በየከተሞቹ ሰብሳቢዎችን (እንዲህ ሲል) ላከ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
54 : 26

إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ لَشِرۡذِمَةٞ قَلِيلُونَ

«እነዚህ ጥቂቶች ጭፈሮች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
55 : 26

وَإِنَّهُمۡ لَنَا لَغَآئِظُونَ

«እነርሱም ለእኛ አስቆጪዎች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
56 : 26

وَإِنَّا لَجَمِيعٌ حَٰذِرُونَ

«እኛም ብዙዎች ጥንቁቆች ነን፤» (አለ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
57 : 26

فَأَخۡرَجۡنَٰهُم مِّن جَنَّٰتٖ وَعُيُونٖ

አወጣናቸውም፡፡ ከአትክልቶችና ከምንጮች፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
58 : 26

وَكُنُوزٖ وَمَقَامٖ كَرِيمٖ

ከድልቦችም ከመልካም መቀመጫዎችም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
59 : 26

كَذَٰلِكَۖ وَأَوۡرَثۡنَٰهَا بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ

እንደዚሁ ለእስራኤል ልጆች አወረስናትም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
60 : 26

فَأَتۡبَعُوهُم مُّشۡرِقِينَ

ፀሐይዋ ስትወጣም ተከተሉዋቸው፡፡ info
التفاسير: