ߞߎ߬ߙߣߊ߬ ߞߟߊߒߞߋ ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߡߎߤߊߙߌߞߊ߲ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߞߊ߬ߘߌߡߌߘߌ ߊߝߙߌߞߌߟߊ

ߞߐߜߍ ߝߙߍߕߍ: 526:526 close

external-link copy
27 : 53

إِنَّ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ لَيُسَمُّونَ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ تَسۡمِيَةَ ٱلۡأُنثَىٰ

27. እነዚያ በመጪው ዓለም የማያምኑት መላዕክትን በእንስት ስም ይሰይማሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
28 : 53

وَمَا لَهُم بِهِۦ مِنۡ عِلۡمٍۖ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّۖ وَإِنَّ ٱلظَّنَّ لَا يُغۡنِي مِنَ ٱلۡحَقِّ شَيۡـٔٗا

28. ለእነርሱም በእርሱ እውቀት የላቸውም። እነርሱ የሚከተሉት ጥርጣሬን ብቻ ነው:: ጥርጣሬ ደግሞ ሀቅን አይተካም:: info
التفاسير:

external-link copy
29 : 53

فَأَعۡرِضۡ عَن مَّن تَوَلَّىٰ عَن ذِكۡرِنَا وَلَمۡ يُرِدۡ إِلَّا ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا

29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከቁርኣን አፈንግጦና የዚችን ዓለም ኑሮ እንጂ ሌላ ከማይመኝ ሰው እራስህን አሽሽ:: info
التفاسير:

external-link copy
30 : 53

ذَٰلِكَ مَبۡلَغُهُم مِّنَ ٱلۡعِلۡمِۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعۡلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ وَهُوَ أَعۡلَمُ بِمَنِ ٱهۡتَدَىٰ

30. ይህ የእውቀታቸው ጣሪያ (መጨረሻ) ነው:: ጌታህ ግን መንገዱን የሳተውን ሁሉ አዋቂ ነው:: የተቀናውንም እንዲሁ አዋቂ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
31 : 53

وَلِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ لِيَجۡزِيَ ٱلَّذِينَ أَسَٰٓـُٔواْ بِمَا عَمِلُواْ وَيَجۡزِيَ ٱلَّذِينَ أَحۡسَنُواْ بِٱلۡحُسۡنَى

31. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የአላህ ነው:: እነዚያን ያጠፉትን በተግባራቸው ለመመንዳትና እነዚያን መልካም የሰሩትንም በመልካሟ (በገነት) ሊመነዳ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
32 : 53

ٱلَّذِينَ يَجۡتَنِبُونَ كَبَٰٓئِرَ ٱلۡإِثۡمِ وَٱلۡفَوَٰحِشَ إِلَّا ٱللَّمَمَۚ إِنَّ رَبَّكَ وَٰسِعُ ٱلۡمَغۡفِرَةِۚ هُوَ أَعۡلَمُ بِكُمۡ إِذۡ أَنشَأَكُم مِّنَ ٱلۡأَرۡضِ وَإِذۡ أَنتُمۡ أَجِنَّةٞ فِي بُطُونِ أُمَّهَٰتِكُمۡۖ فَلَا تُزَكُّوٓاْ أَنفُسَكُمۡۖ هُوَ أَعۡلَمُ بِمَنِ ٱتَّقَىٰٓ

32. እነርሱም ከጥቃቅን ጥፋቶች በቀር ከባባድ ወንጀሎችንና አጸያፊ ተግባሮችን የራቁ ናቸው:: ጌታህ ምህረተ ሰፊ ነው:: እርሱ ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜም ሆነ በእናቶቻችሁ ማሕጸን ውስጥ ጽንሶች በሁናችሁበት ጊዜ ያውቃችኋል:: ስለዚህ እራሳችሁን አታሞግሱ:: እርሱ በትክክል የሚፈራውን ሰው ከሁሉም ይበልጥ አዋቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
33 : 53

أَفَرَءَيۡتَ ٱلَّذِي تَوَلَّىٰ

33. ያን ከእምነት የሸሸውን አየህን (እስቲ ንገረኝ)? info
التفاسير:

external-link copy
34 : 53

وَأَعۡطَىٰ قَلِيلٗا وَأَكۡدَىٰٓ

34. ጥቂትን ብቻ ሰጥቶ ያቋረጠውን፤ info
التفاسير:

external-link copy
35 : 53

أَعِندَهُۥ عِلۡمُ ٱلۡغَيۡبِ فَهُوَ يَرَىٰٓ

35, ለመሆኑ የሚያውቀው የሩቅ ሚስጢር አለውና እርሱንም ያያልን? info
التفاسير:

external-link copy
36 : 53

أَمۡ لَمۡ يُنَبَّأۡ بِمَا فِي صُحُفِ مُوسَىٰ

36. ወይስ በሙሳ ፅሁፍ ያለው አልተነገረውም? info
التفاسير:

external-link copy
37 : 53

وَإِبۡرَٰهِيمَ ٱلَّذِي وَفَّىٰٓ

37. በኢብራሂም (ትእዛዛቱን) በፈፀመው ያለውስ አልተነገረዉምን? info
التفاسير:

external-link copy
38 : 53

أَلَّا تَزِرُ وَازِرَةٞ وِزۡرَ أُخۡرَىٰ

38. ይኸዉም ወንጀለኛ ነፍስ የሌላውን ነፍስ ወንጀል በፍጹም አትሸከምም:: info
التفاسير:

external-link copy
39 : 53

وَأَن لَّيۡسَ لِلۡإِنسَٰنِ إِلَّا مَا سَعَىٰ

39. የሰው ልጅም የለፋበትን ብቻ እንጂ ሌላ የለዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
40 : 53

وَأَنَّ سَعۡيَهُۥ سَوۡفَ يُرَىٰ

40. የሰራውም ሁሉ ወደ ፊት ይታያል:: info
التفاسير:

external-link copy
41 : 53

ثُمَّ يُجۡزَىٰهُ ٱلۡجَزَآءَ ٱلۡأَوۡفَىٰ

41. ከዚያም ጌታው ሙሉ ምንዳውን ይመነዳዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
42 : 53

وَأَنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ ٱلۡمُنتَهَىٰ

42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሁሉም መጨረሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
43 : 53

وَأَنَّهُۥ هُوَ أَضۡحَكَ وَأَبۡكَىٰ

43. እርሱ ያ ያሳቀና ያስለቀሰ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
44 : 53

وَأَنَّهُۥ هُوَ أَمَاتَ وَأَحۡيَا

44. እርሱ ያ የገደለና ሕያው ያደረገም ነው:: info
التفاسير: