ߞߎ߬ߙߣߊ߬ ߞߟߊߒߞߋ ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߡߎߤߊߙߌߞߊ߲ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߞߊ߬ߘߌߡߌߘߌ ߊߝߙߌߞߌߟߊ

ߞߐߜߍ ߝߙߍߕߍ:close

external-link copy
34 : 40

وَلَقَدۡ جَآءَكُمۡ يُوسُفُ مِن قَبۡلُ بِٱلۡبَيِّنَٰتِ فَمَا زِلۡتُمۡ فِي شَكّٖ مِّمَّا جَآءَكُم بِهِۦۖ حَتَّىٰٓ إِذَا هَلَكَ قُلۡتُمۡ لَن يَبۡعَثَ ٱللَّهُ مِنۢ بَعۡدِهِۦ رَسُولٗاۚ كَذَٰلِكَ يُضِلُّ ٱللَّهُ مَنۡ هُوَ مُسۡرِفٞ مُّرۡتَابٌ

34. ዩሱፍም ከዚህ በፊት ግልጽ ማስረጃዎችን በእርግጥ አመጣላችሁ:: ከዚያ እርሱ ካመጣላችሁ ነገር ከመጠራጠር አልተወገዳችሁም:: በጠፋም ጊዜ «አላህ ከእርሱ በኋላ መልዕክተኛን በጭራሽ አይልክም» አላችሁ፤ አላህ እንደዚሁ ድንበር አላፊ ተጠራጣሪ የሆነን ሰው ያሳስታል። info
التفاسير:

external-link copy
35 : 40

ٱلَّذِينَ يُجَٰدِلُونَ فِيٓ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ بِغَيۡرِ سُلۡطَٰنٍ أَتَىٰهُمۡۖ كَبُرَ مَقۡتًا عِندَ ٱللَّهِ وَعِندَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْۚ كَذَٰلِكَ يَطۡبَعُ ٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ قَلۡبِ مُتَكَبِّرٖ جَبَّارٖ

35. እነዚያ የመጣላቸው አስረጅ ሳይኖር በአላህ ታዓምራቶች የሚከራከሩ (ክርክራቸው) አላህ ዘንድና እነዚያም ያመኑት ዘንድ መጠላቱ በጣም ተለቀ:: እንደዚሁ አላህ በኩሩ ጨካኝ ልብ ሁሉ ላይ ያትማል:: info
التفاسير:

external-link copy
36 : 40

وَقَالَ فِرۡعَوۡنُ يَٰهَٰمَٰنُ ٱبۡنِ لِي صَرۡحٗا لَّعَلِّيٓ أَبۡلُغُ ٱلۡأَسۡبَٰبَ

36. ፈርዖንም አለ፡- «ሃማን ሆይ! መንገዶችን እደርስ ዘንድ ረዥም ህንፃን ካብልኝ። የሰማያትን መንገዶች እደርስ ዘንድ። info
التفاسير:

external-link copy
37 : 40

أَسۡبَٰبَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ فَأَطَّلِعَ إِلَىٰٓ إِلَٰهِ مُوسَىٰ وَإِنِّي لَأَظُنُّهُۥ كَٰذِبٗاۚ وَكَذَٰلِكَ زُيِّنَ لِفِرۡعَوۡنَ سُوٓءُ عَمَلِهِۦ وَصُدَّ عَنِ ٱلسَّبِيلِۚ وَمَا كَيۡدُ فِرۡعَوۡنَ إِلَّا فِي تَبَابٖ

37. «የሰማያትን መንገዶች እደርስ ዘንድ። ከዚያ ወደ ሙሳ አምላክ እመለከት ዘንድ። እኔም ውሸታም ነው ብዬ እጠረጥረዋለሁ።» አለ:: ልክ እንደዚሁ ለፈርዖን መጥፎ ስራው ተሸለመለት:: ከቅኑ መንገድም ታገደ:: የፈርዖንም ተንኮል በከሳራ ውስጥ እንጂ አይደለም:: info
التفاسير:

external-link copy
38 : 40

وَقَالَ ٱلَّذِيٓ ءَامَنَ يَٰقَوۡمِ ٱتَّبِعُونِ أَهۡدِكُمۡ سَبِيلَ ٱلرَّشَادِ

38. ያ ያመነውም አለ፡- «ወገኖቼ ሆይ! ተከተሉኝ ቀጥታውን መንገድ እመራችኋለሁና:: info
التفاسير:

external-link copy
39 : 40

يَٰقَوۡمِ إِنَّمَا هَٰذِهِ ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَا مَتَٰعٞ وَإِنَّ ٱلۡأٓخِرَةَ هِيَ دَارُ ٱلۡقَرَارِ

39. «ወገኖቼ ሆይ! ይህች ቅርቢቱ ሕይወት የጥቂት ቀናት መጣቀሚያ ብቻ ናት፤ መጨረሻይቱ ዓለም ግን እርሷ ትክክለኛ መርጊያ አገር ናት:: info
التفاسير:

external-link copy
40 : 40

مَنۡ عَمِلَ سَيِّئَةٗ فَلَا يُجۡزَىٰٓ إِلَّا مِثۡلَهَاۖ وَمَنۡ عَمِلَ صَٰلِحٗا مِّن ذَكَرٍ أَوۡ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤۡمِنٞ فَأُوْلَٰٓئِكَ يَدۡخُلُونَ ٱلۡجَنَّةَ يُرۡزَقُونَ فِيهَا بِغَيۡرِ حِسَابٖ

40. «መጥፎን የሰራ ሰው ብጤዋን እንጅ አይመነዳም:: እርሱ ምዕመን ሆኖ ከወንድ ወይም ከሴት በጎ የሰራም እነዚያ ገነትን ይገባሉ:: በእርሷ ውስጥም ያለ ቁጥር ይለገሳሉ። info
التفاسير: