ߞߎ߬ߙߣߊ߬ ߞߟߊߒߞߋ ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߡߎߤߊߙߌߞߊ߲ ߘߟߊߡߌ߬ߘߊ - ߡߎ߬ߤ߭ߊߡߡߊߘߎ߫ ߛ߫ߊ߯ߘߌߞ߫ߎ߫ ߓߟߏ߫

ߞߐߜߍ ߝߙߍߕߍ:close

external-link copy
16 : 33

قُل لَّن يَنفَعَكُمُ ٱلۡفِرَارُ إِن فَرَرۡتُم مِّنَ ٱلۡمَوۡتِ أَوِ ٱلۡقَتۡلِ وَإِذٗا لَّا تُمَتَّعُونَ إِلَّا قَلِيلٗا

ከሞት ወይም ከመገደል ብትሸሹ መሸሻችሁ ፈጽሞ አይጠቅማችሁም፡፡ ያን ጊዜም ጥቂትን እንጂ የምትጣቀሙ አትደረጉም በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
17 : 33

قُلۡ مَن ذَا ٱلَّذِي يَعۡصِمُكُم مِّنَ ٱللَّهِ إِنۡ أَرَادَ بِكُمۡ سُوٓءًا أَوۡ أَرَادَ بِكُمۡ رَحۡمَةٗۚ وَلَا يَجِدُونَ لَهُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ وَلِيّٗا وَلَا نَصِيرٗا

«(አላህ) በእናንተ ክፉን ነገር ቢሻ ያ ከአላህ የሚጠብቃችሁ ማነው? ወይም ለእናንተ ችሮታን ቢሻ፤ (በክፉ የሚነካችሁ ማነው?)» በላቸው፤ ከአላህም ሌላ ለእነርሱ ወዳጅም ረዳትም አያገኙም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
18 : 33

۞ قَدۡ يَعۡلَمُ ٱللَّهُ ٱلۡمُعَوِّقِينَ مِنكُمۡ وَٱلۡقَآئِلِينَ لِإِخۡوَٰنِهِمۡ هَلُمَّ إِلَيۡنَاۖ وَلَا يَأۡتُونَ ٱلۡبَأۡسَ إِلَّا قَلِيلًا

ከእናንተ ውስጥ የሚያሳንፉትን፣ ለወንድሞቻቸውም «ወደኛ ኑ» የሚሉትን፣ ውጊያንም ጥቂትን እንጂ የማይመጡትን በእርግጥ አላህ ያውቃቸዋል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
19 : 33

أَشِحَّةً عَلَيۡكُمۡۖ فَإِذَا جَآءَ ٱلۡخَوۡفُ رَأَيۡتَهُمۡ يَنظُرُونَ إِلَيۡكَ تَدُورُ أَعۡيُنُهُمۡ كَٱلَّذِي يُغۡشَىٰ عَلَيۡهِ مِنَ ٱلۡمَوۡتِۖ فَإِذَا ذَهَبَ ٱلۡخَوۡفُ سَلَقُوكُم بِأَلۡسِنَةٍ حِدَادٍ أَشِحَّةً عَلَى ٱلۡخَيۡرِۚ أُوْلَٰٓئِكَ لَمۡ يُؤۡمِنُواْ فَأَحۡبَطَ ٱللَّهُ أَعۡمَٰلَهُمۡۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٗا

በእናንተ ላይ (እርዳታን) የነፈጉ ሆነው እንጅ (የማይመጡትን)፣ ሽብሩም በመጣ ጊዜ እንደዚያ ከሞት (መከራ) በርሱ ላይ የሚሸፍን ዐደጋ እንደወደቀበት ዓይኖቻቸው ወዲያና ወዲህ የምትዞር ኾና ወዳንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ፡፡ ሽብሩም በኼደ ጊዜ በገንዘብ ላይ የሚሳሱ ኾነው በተቡ ምላሶች ይነድፏችኋል፡፡ እነዚያ አላመኑም፡፡ ስለዚህ አላህ ሥራዎቻቸውን አበላሸ፡፡ ይህም በአላህ ላይ ገርነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
20 : 33

يَحۡسَبُونَ ٱلۡأَحۡزَابَ لَمۡ يَذۡهَبُواْۖ وَإِن يَأۡتِ ٱلۡأَحۡزَابُ يَوَدُّواْ لَوۡ أَنَّهُم بَادُونَ فِي ٱلۡأَعۡرَابِ يَسۡـَٔلُونَ عَنۡ أَنۢبَآئِكُمۡۖ وَلَوۡ كَانُواْ فِيكُم مَّا قَٰتَلُوٓاْ إِلَّا قَلِيلٗا

(መናፍቆች) አሕዛብን አልኼዱም ብለው ያስባሉ፡፡ አሕዛቦቹም ቢመጡ እነርሱ በዘላኖች ውስጥ በገጠር (የራቁ) ሊሆኑ ይመኛሉ፡፡ ከወሬዎቻችሁ ይጠይቃሉ፡፡ በእናንተ ውስጥ በነበሩም ኖሮ ጥቂትን እንጂ አይዋጉም ነበር፡ info
التفاسير:

external-link copy
21 : 33

لَّقَدۡ كَانَ لَكُمۡ فِي رَسُولِ ٱللَّهِ أُسۡوَةٌ حَسَنَةٞ لِّمَن كَانَ يَرۡجُواْ ٱللَّهَ وَٱلۡيَوۡمَ ٱلۡأٓخِرَ وَذَكَرَ ٱللَّهَ كَثِيرٗا

ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አልላችሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
22 : 33

وَلَمَّا رَءَا ٱلۡمُؤۡمِنُونَ ٱلۡأَحۡزَابَ قَالُواْ هَٰذَا مَا وَعَدَنَا ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥ وَصَدَقَ ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥۚ وَمَا زَادَهُمۡ إِلَّآ إِيمَٰنٗا وَتَسۡلِيمٗا

አማኞቹም አሕዛብን ባዩ ጊዜ «ይህ አላህና መልክተኛው የቀጠሩን ነው፡፡ አላህና መልክተኛውም እውነትን ተናገሩ» አሉ፡፡ (ይህ) እምነትንና መታዘዝንም እንጂ ሌላን አልጨመረላቸውም፡፡ info
التفاسير: