ߞߎ߬ߙߣߊ߬ ߞߟߊߒߞߋ ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߡߎߤߊߙߌߞߊ߲ ߘߟߊߡߌ߬ߘߊ - ߡߎ߬ߤ߭ߊߡߡߊߘߎ߫ ߛ߫ߊ߯ߘߌߞ߫ߎ߫ ߓߟߏ߫

ߞߐߜߍ ߝߙߍߕߍ:close

external-link copy
71 : 28

قُلۡ أَرَءَيۡتُمۡ إِن جَعَلَ ٱللَّهُ عَلَيۡكُمُ ٱلَّيۡلَ سَرۡمَدًا إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ مَنۡ إِلَٰهٌ غَيۡرُ ٱللَّهِ يَأۡتِيكُم بِضِيَآءٍۚ أَفَلَا تَسۡمَعُونَ

አያችሁን (ንገሩኝ) «አላህ በእናንተ ላይ ሌሊትን እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ዘውታሪ ቢያደርገው ከአላህ ሌላ ብርሃንን የሚያመጣላችሁ አምላክ ማነው? አትሰሙምን?» በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
72 : 28

قُلۡ أَرَءَيۡتُمۡ إِن جَعَلَ ٱللَّهُ عَلَيۡكُمُ ٱلنَّهَارَ سَرۡمَدًا إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ مَنۡ إِلَٰهٌ غَيۡرُ ٱللَّهِ يَأۡتِيكُم بِلَيۡلٖ تَسۡكُنُونَ فِيهِۚ أَفَلَا تُبۡصِرُونَ

አያችሁን «አላህ በእናንተ ላይ ቀንን እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ዘውታሪ ቢያደርገው ከአላህ ሌላ በውስጡ የምታርፉበትን ሌሊት የሚያመጣላችሁ አምላክ ማን ነው (ንገሩኝ)? አታስተውሉምን?» በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
73 : 28

وَمِن رَّحۡمَتِهِۦ جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيۡلَ وَٱلنَّهَارَ لِتَسۡكُنُواْ فِيهِ وَلِتَبۡتَغُواْ مِن فَضۡلِهِۦ وَلَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ

ከችሮታውም ለእናንተ ሌሊትንና ቀንን በውስጡ ልታርፉበት፣ ከትሩፋቱም ልትፈልጉበት፣ አመስገኞችም ልትኾኑ አደረገላችሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
74 : 28

وَيَوۡمَ يُنَادِيهِمۡ فَيَقُولُ أَيۡنَ شُرَكَآءِيَ ٱلَّذِينَ كُنتُمۡ تَزۡعُمُونَ

የሚጠራባቸውንም ቀንና «እነዚያ ተጋሪዎቼ ትሏቸው የነበራችሁት የት ናቸው/» የሚልበትን (አስታውስ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
75 : 28

وَنَزَعۡنَا مِن كُلِّ أُمَّةٖ شَهِيدٗا فَقُلۡنَا هَاتُواْ بُرۡهَٰنَكُمۡ فَعَلِمُوٓاْ أَنَّ ٱلۡحَقَّ لِلَّهِ وَضَلَّ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ

ከሕዝቦችም ሁሉ መስካሪን እናወጣለን፡፡ መስረጃችሁን አምጡ እንላለን፤ (ያን ጊዜ) እውነተኛውም አምላክነት ለአላህ ብቻ መኾኑን ያውቃሉ፡፡ ይቀጣጥፉት የነበሩትም ከእነርሱ ይጠፋቸዋል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
76 : 28

۞ إِنَّ قَٰرُونَ كَانَ مِن قَوۡمِ مُوسَىٰ فَبَغَىٰ عَلَيۡهِمۡۖ وَءَاتَيۡنَٰهُ مِنَ ٱلۡكُنُوزِ مَآ إِنَّ مَفَاتِحَهُۥ لَتَنُوٓأُ بِٱلۡعُصۡبَةِ أُوْلِي ٱلۡقُوَّةِ إِذۡ قَالَ لَهُۥ قَوۡمُهُۥ لَا تَفۡرَحۡۖ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ ٱلۡفَرِحِينَ

ቃሩን ከሙሳ ነገዶች ነበር፡፡ በእነርሱም ላይ አመጸ፡፡ ከድልቦችም ያንን መከፈቻዎቹ ብቻ የኃይል ባለቤቶች የኾኑ ጭፍሮችን (ሸክሙ) የሚከብድን ሰጠነው፡፡ ወገኖቹ ለእርሱ አትኩራ፤ አላህ ኩራተኞችን አይወድምና ባሉት ጊዜ (አስታውስ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
77 : 28

وَٱبۡتَغِ فِيمَآ ءَاتَىٰكَ ٱللَّهُ ٱلدَّارَ ٱلۡأٓخِرَةَۖ وَلَا تَنسَ نَصِيبَكَ مِنَ ٱلدُّنۡيَاۖ وَأَحۡسِن كَمَآ أَحۡسَنَ ٱللَّهُ إِلَيۡكَۖ وَلَا تَبۡغِ ٱلۡفَسَادَ فِي ٱلۡأَرۡضِۖ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ ٱلۡمُفۡسِدِينَ

«አላህም በሰጠህ ሀብት የመጨረሻይቱን አገር ፈልግ፡፡ ከቅርቢቱም ዓለም ፋንታህን አትርሳ፡፡ አላህም ወደ አንተ መልካምን እንዳደረገልህ (ለሰዎች) መልካምን አድርግ፡፡ በምድርም ውስጥ ማጥፋትን አትፈልግ፡፡ አላህ አጥፊዎችን አይወድምና» (አሉት)፡፡ info
التفاسير: