ߞߎ߬ߙߣߊ߬ ߞߟߊߒߞߋ ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߡߎߤߊߙߌߞߊ߲ ߘߟߊߡߌ߬ߘߊ - ߡߎ߬ߤ߭ߊߡߡߊߘߎ߫ ߛ߫ߊ߯ߘߌߞ߫ߎ߫ ߓߟߏ߫

ߞߐߜߍ ߝߙߍߕߍ:close

external-link copy
56 : 27

۞ فَمَا كَانَ جَوَابَ قَوۡمِهِۦٓ إِلَّآ أَن قَالُوٓاْ أَخۡرِجُوٓاْ ءَالَ لُوطٖ مِّن قَرۡيَتِكُمۡۖ إِنَّهُمۡ أُنَاسٞ يَتَطَهَّرُونَ

የሕዝቦቹም መልስ የሉጥን ቤተሰቦች «ከከተማችሁ አውጡ፡፡ እነርሱ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸውና» ማለት እንጅ ሌላ አልነበረም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
57 : 27

فَأَنجَيۡنَٰهُ وَأَهۡلَهُۥٓ إِلَّا ٱمۡرَأَتَهُۥ قَدَّرۡنَٰهَا مِنَ ٱلۡغَٰبِرِينَ

እርሱንና ቤተሰቦቹንም አዳን፡፡ ሚስቱ፤ ብቻ ስትቀር፡፡ (በጥፋቱ ውስጥ) ከቀሪዎቹ አደረግናት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
58 : 27

وَأَمۡطَرۡنَا عَلَيۡهِم مَّطَرٗاۖ فَسَآءَ مَطَرُ ٱلۡمُنذَرِينَ

በእነርሱም ላይ (የድንጋይ) ዝናብን አዘነብንባቸው፡፡ የተስፈራሪዎቹም ዝናብ ከፋ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
59 : 27

قُلِ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ وَسَلَٰمٌ عَلَىٰ عِبَادِهِ ٱلَّذِينَ ٱصۡطَفَىٰٓۗ ءَآللَّهُ خَيۡرٌ أَمَّا يُشۡرِكُونَ

(ሙሐመድ ሆይ) በል «ምስጋና ለአላህ ይግባው፡፡ በእነዚያም በመረጣቸው ባሮቹ ላይ ሰላም ይውረድ፡፡ አላህ በላጭ ነውን ወይስ ያ የሚያጋሩት (ጣዖት)?፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
60 : 27

أَمَّنۡ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ وَأَنزَلَ لَكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَأَنۢبَتۡنَا بِهِۦ حَدَآئِقَ ذَاتَ بَهۡجَةٖ مَّا كَانَ لَكُمۡ أَن تُنۢبِتُواْ شَجَرَهَآۗ أَءِلَٰهٞ مَّعَ ٱللَّهِۚ بَلۡ هُمۡ قَوۡمٞ يَعۡدِلُونَ

ወይም ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረና ከሰማይም ለእናንተ ውሃን ያወረደው (ይበልጣል ወይስ የሚያጋሩት?) በእርሱም ባለውበት የኾኑትን የታጠሩ አትክልቶችን ዛፍዋን ልታበቅሉ ለናንተ ችሎታ ያልነበራችሁን አበቀልን፡፡ ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? (የለም)፡፡ ግን እነርሱ (ከእውነት) የሚያዘነብሉ ሕዝቦች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
61 : 27

أَمَّن جَعَلَ ٱلۡأَرۡضَ قَرَارٗا وَجَعَلَ خِلَٰلَهَآ أَنۡهَٰرٗا وَجَعَلَ لَهَا رَوَٰسِيَ وَجَعَلَ بَيۡنَ ٱلۡبَحۡرَيۡنِ حَاجِزًاۗ أَءِلَٰهٞ مَّعَ ٱللَّهِۚ بَلۡ أَكۡثَرُهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ

ወይም ያ ምድርን መርጊያ ያደረገና በመካከሏም ወንዞችን ያደረገ፣ ለእርሷም ጋራዎችን ያደረገ፣ በሁለቱ ባሕሮችም (በጣፋጩና በጨው ባሕር) መካከል ግርዶን ያደረገ (ይበልጣልን ወይስ የሚያጋሩት?) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
62 : 27

أَمَّن يُجِيبُ ٱلۡمُضۡطَرَّ إِذَا دَعَاهُ وَيَكۡشِفُ ٱلسُّوٓءَ وَيَجۡعَلُكُمۡ خُلَفَآءَ ٱلۡأَرۡضِۗ أَءِلَٰهٞ مَّعَ ٱللَّهِۚ قَلِيلٗا مَّا تَذَكَّرُونَ

ወይም ያ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል፣ መከራንም የሚያስወግድ፣ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደረጋችሁ፤ (ይበልጣልን ወይስ የሚያጋሩት?) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ጥቂትንም አትገሠጹም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
63 : 27

أَمَّن يَهۡدِيكُمۡ فِي ظُلُمَٰتِ ٱلۡبَرِّ وَٱلۡبَحۡرِ وَمَن يُرۡسِلُ ٱلرِّيَٰحَ بُشۡرَۢا بَيۡنَ يَدَيۡ رَحۡمَتِهِۦٓۗ أَءِلَٰهٞ مَّعَ ٱللَّهِۚ تَعَٰلَى ٱللَّهُ عَمَّا يُشۡرِكُونَ

ወይም ያ በየብስና በባሕር ጨለማዎች ውስጥ የሚመራችሁ ነፋሶችንም ከዝናሙ በፊት አብሳሪ ኾነው የሚልክ (ይበልጣልን ወይስ የሚያጋሩት?) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? አላህ (በእርሱ) ከሚያጋሩዋቸው ሁሉ ላቀ፡፡ info
التفاسير: