ߞߎ߬ߙߣߊ߬ ߞߟߊߒߞߋ ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߡߎߤߊߙߌߞߊ߲ ߘߟߊߡߌ߬ߘߊ - ߡߎ߬ߤ߭ߊߡߡߊߘߎ߫ ߛ߫ߊ߯ߘߌߞ߫ߎ߫ ߓߟߏ߫

ߞߐߜߍ ߝߙߍߕߍ:close

external-link copy
77 : 20

وَلَقَدۡ أَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ أَنۡ أَسۡرِ بِعِبَادِي فَٱضۡرِبۡ لَهُمۡ طَرِيقٗا فِي ٱلۡبَحۡرِ يَبَسٗا لَّا تَخَٰفُ دَرَكٗا وَلَا تَخۡشَىٰ

ወደ ሙሳም «ባሮቼን ይዘህ በሌሊት ኺድ፡፡ ለእነሱም በባሕር ውስጥ ደረቅ መንገድን አድርግላቸው፡፡ መገኘትን አትፍራ፡፡ (ከመስጠም) አትጨነቅም፡፡» ስንል በእርግጥ ላክንበት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
78 : 20

فَأَتۡبَعَهُمۡ فِرۡعَوۡنُ بِجُنُودِهِۦ فَغَشِيَهُم مِّنَ ٱلۡيَمِّ مَا غَشِيَهُمۡ

ፈርዖንም ከሰራዊቱ ጋር ኾኖ ተከተላቸው፡፡ ከባህሩም የሚሸፍን ሸፈናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
79 : 20

وَأَضَلَّ فِرۡعَوۡنُ قَوۡمَهُۥ وَمَا هَدَىٰ

ፈርዖንም ሕዝቦቹን አሳሳታቸው፡፡ ቅኑንም መንገድ አልመራቸውም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
80 : 20

يَٰبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ قَدۡ أَنجَيۡنَٰكُم مِّنۡ عَدُوِّكُمۡ وَوَٰعَدۡنَٰكُمۡ جَانِبَ ٱلطُّورِ ٱلۡأَيۡمَنَ وَنَزَّلۡنَا عَلَيۡكُمُ ٱلۡمَنَّ وَٱلسَّلۡوَىٰ

የእስራኤል ልጆች ሆይ! ከጠላታችሁ በእርግጥ አዳንናችሁ፡፡ በጡርም ቀኝ ጎን ቀጠሮ አደረግንላችሁ፡፡ በእናንተም ላይ መናንና ሰልዋ (ድርጭትን) አወረድንላችሁ፡፡ {1} info

{1} መን ማር የምመስል ጣፋጭ ምግብ ስሆን ሰልዋ ወፍ ይመስላል፤ ሁላቱም አላህ ለኢስራኢል ልጆች በበረሃ ስንከራተቱ በነበሩበት ግዜ ያወረዳላቸው ምግብ ነው።(ኢብኑከሲር)

التفاسير:

external-link copy
81 : 20

كُلُواْ مِن طَيِّبَٰتِ مَا رَزَقۡنَٰكُمۡ وَلَا تَطۡغَوۡاْ فِيهِ فَيَحِلَّ عَلَيۡكُمۡ غَضَبِيۖ وَمَن يَحۡلِلۡ عَلَيۡهِ غَضَبِي فَقَدۡ هَوَىٰ

ከሰጠናችሁ ሲሳይ፤ ከመልካሙ ብሉ፡፡ በእርሱም ወሰንን አትለፉ፡፡ ቁጣዬ በእናንተ ላይ ይወርድባችኋልና፡፡ በእርሱም ላይ ቁጣዬ የሚወርድበት ሰው በእርግጥ ይጠፋል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
82 : 20

وَإِنِّي لَغَفَّارٞ لِّمَن تَابَ وَءَامَنَ وَعَمِلَ صَٰلِحٗا ثُمَّ ٱهۡتَدَىٰ

እኔም ለተጸጸተ፣ ላመነም፣ መልካምንም ለሠራ፣ ከዚያም ለተመራ ሰው በእርግጥ መሓሪ ነኝ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
83 : 20

۞ وَمَآ أَعۡجَلَكَ عَن قَوۡمِكَ يَٰمُوسَىٰ

«ሙሳ ሆይ! ከሕዝቦችህ ምን አስቸኮለህም» (ተባለ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
84 : 20

قَالَ هُمۡ أُوْلَآءِ عَلَىٰٓ أَثَرِي وَعَجِلۡتُ إِلَيۡكَ رَبِّ لِتَرۡضَىٰ

«እነሱ እነዚህ፤ በዱካዬ ላይ ያሉ ናቸው፡፡ ጌታዬ ሆይ! ትወድልንም ዘንድ ወደ አንተ ቸኮልኩ» አለ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
85 : 20

قَالَ فَإِنَّا قَدۡ فَتَنَّا قَوۡمَكَ مِنۢ بَعۡدِكَ وَأَضَلَّهُمُ ٱلسَّامِرِيُّ

(አላህ) «እኛም ከአንተ በኋላ ሰዎችህን በእርግጥ ፈትተን፡፡ ሳምራዊውም አሳሳታቸው» አለው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
86 : 20

فَرَجَعَ مُوسَىٰٓ إِلَىٰ قَوۡمِهِۦ غَضۡبَٰنَ أَسِفٗاۚ قَالَ يَٰقَوۡمِ أَلَمۡ يَعِدۡكُمۡ رَبُّكُمۡ وَعۡدًا حَسَنًاۚ أَفَطَالَ عَلَيۡكُمُ ٱلۡعَهۡدُ أَمۡ أَرَدتُّمۡ أَن يَحِلَّ عَلَيۡكُمۡ غَضَبٞ مِّن رَّبِّكُمۡ فَأَخۡلَفۡتُم مَّوۡعِدِي

ሙሳም ወደ ሰዎቹ የተቆጣ ያዘነ ኾኖ ተመለሰ፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! ጌታችሁ መልካም ተስፋን አልቀጠራችሁምን? ቀጠሮው በእናንተ ላይ ረዘመባችሁን?» ወይስ በእናንተ ላይ ከጌታችሁ ቅጣት ሊወርድባችሁ ፈለጋችሁና ቀጠሮየን አፈረሳችሁን አላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
87 : 20

قَالُواْ مَآ أَخۡلَفۡنَا مَوۡعِدَكَ بِمَلۡكِنَا وَلَٰكِنَّا حُمِّلۡنَآ أَوۡزَارٗا مِّن زِينَةِ ٱلۡقَوۡمِ فَقَذَفۡنَٰهَا فَكَذَٰلِكَ أَلۡقَى ٱلسَّامِرِيُّ

«ቀጠሮህን በፈቃዳችን አልጣስንም፡፡ ግን እኛ ከሕዝቦቹ ጌጥ ሸክሞችን ተጫን (በእሳት ላይ) ጣልናትም፡፡ ሳምራዊውም እንደዚሁ ጣለ» አሉት፡፡ info
التفاسير: