पवित्र कुरअानको अर्थको अनुवाद - अम्हरी अनुवाद : अफ्रिका एकेडेमी ।

رقم الصفحة:close

external-link copy
65 : 5

وَلَوۡ أَنَّ أَهۡلَ ٱلۡكِتَٰبِ ءَامَنُواْ وَٱتَّقَوۡاْ لَكَفَّرۡنَا عَنۡهُمۡ سَيِّـَٔاتِهِمۡ وَلَأَدۡخَلۡنَٰهُمۡ جَنَّٰتِ ٱلنَّعِيمِ

65. የመጽሐፉ ባለቤቶች ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ ከእነርሱ ኃጢአቶቻቸውን በእርግጥ ባበስንና የመጠቀሚያ ገነቶችን በእርግጥ ባስገባናቸው ነበር። info
التفاسير:

external-link copy
66 : 5

وَلَوۡ أَنَّهُمۡ أَقَامُواْ ٱلتَّوۡرَىٰةَ وَٱلۡإِنجِيلَ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيۡهِم مِّن رَّبِّهِمۡ لَأَكَلُواْ مِن فَوۡقِهِمۡ وَمِن تَحۡتِ أَرۡجُلِهِمۚ مِّنۡهُمۡ أُمَّةٞ مُّقۡتَصِدَةٞۖ وَكَثِيرٞ مِّنۡهُمۡ سَآءَ مَا يَعۡمَلُونَ

66. እነርሱ ተውራትንና ኢንጂልን ከጌታቸው ወደ እነርሱ የተወረደውን መጽሐፍ በሰሩበት ኖሮ ከበላያቸውና ከእግሮቻቸው ስር በተመገቡ ነበር:: ከእነርሱ መካከል ትክክለኛ ህዝቦች አሉ:: ከእነርሱ መካከል ብዙዎቹ ግን የሚሰሩት ነገር ከፋ! info
التفاسير:

external-link copy
67 : 5

۞ يَٰٓأَيُّهَا ٱلرَّسُولُ بَلِّغۡ مَآ أُنزِلَ إِلَيۡكَ مِن رَّبِّكَۖ وَإِن لَّمۡ تَفۡعَلۡ فَمَا بَلَّغۡتَ رِسَالَتَهُۥۚ وَٱللَّهُ يَعۡصِمُكَ مِنَ ٱلنَّاسِۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلۡكَٰفِرِينَ

67. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን ቁርኣን አድርስ:: ይህን ባትሰራ ግን የጌታህን መልዕክቱን አላደርስክም:: አላህም ከሰዎች (ተንኮል) ይጠብቅሃል:: አላህ ከሓዲያን ሕዝቦችን አያቀናም። info
التفاسير:

external-link copy
68 : 5

قُلۡ يَٰٓأَهۡلَ ٱلۡكِتَٰبِ لَسۡتُمۡ عَلَىٰ شَيۡءٍ حَتَّىٰ تُقِيمُواْ ٱلتَّوۡرَىٰةَ وَٱلۡإِنجِيلَ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيۡكُم مِّن رَّبِّكُمۡۗ وَلَيَزِيدَنَّ كَثِيرٗا مِّنۡهُم مَّآ أُنزِلَ إِلَيۡكَ مِن رَّبِّكَ طُغۡيَٰنٗا وَكُفۡرٗاۖ فَلَا تَأۡسَ عَلَى ٱلۡقَوۡمِ ٱلۡكَٰفِرِينَ

68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ የመጽሐፍ ባለቤቶች ሆይ! ተውራትን፤ ኢንጂልን እና ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ቁርኣንን እስከምትሰሩባቸው ድረስ በምንም ላይ አይደላችሁም።» በላቸው:: ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደው ቁርኣን ከእነርሱ ብዙዎቹን ትዕቢትንና ክህደትን በእርግጥ ይጨምርባቸዋል:: በካሐዲያን ህዝቦች ላይ አትዘን። info
التفاسير:

external-link copy
69 : 5

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَٱلَّذِينَ هَادُواْ وَٱلصَّٰبِـُٔونَ وَٱلنَّصَٰرَىٰ مَنۡ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِ وَعَمِلَ صَٰلِحٗا فَلَا خَوۡفٌ عَلَيۡهِمۡ وَلَا هُمۡ يَحۡزَنُونَ

69. እነዚያ ያመኑ፤ አይሁዳዊያን፤ ሳቢያኖችና ክርስቲያኖች ከእነርሱ መካከል በአላህና በመጨረሻው ቀን በትክክል ያመኑና መልካምን የሰሩ ሁሉ በእነርሱ ላይ ስጋት የለባቸዉም። አይተክዙምም። info
التفاسير:

external-link copy
70 : 5

لَقَدۡ أَخَذۡنَا مِيثَٰقَ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ وَأَرۡسَلۡنَآ إِلَيۡهِمۡ رُسُلٗاۖ كُلَّمَا جَآءَهُمۡ رَسُولُۢ بِمَا لَا تَهۡوَىٰٓ أَنفُسُهُمۡ فَرِيقٗا كَذَّبُواْ وَفَرِيقٗا يَقۡتُلُونَ

70. የኢስራኢል ልጆች የጠበቀ ቃል ኪዳን በእርግጥ ያዝንባቸው:: ወደ እነርሱም መልዕክተኞችን ላክን:: ነፍሶቻቸው በማትወደው ነገር መልዕክተኛ በመጣላቸው ቁጥር ከፊሉን አስተባበሉ:: ከፊሉንም ይገድላሉ:: info
التفاسير: