पवित्र कुरअानको अर्थको अनुवाद - अम्हरी अनुवाद : अफ्रिका एकेडेमी ।

رقم الصفحة:close

external-link copy
74 : 43

إِنَّ ٱلۡمُجۡرِمِينَ فِي عَذَابِ جَهَنَّمَ خَٰلِدُونَ

74. አመጸኞች በገሀነም ስቃይ ውስጥ በእርግጥ ዘወታሪዎች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
75 : 43

لَا يُفَتَّرُ عَنۡهُمۡ وَهُمۡ فِيهِ مُبۡلِسُونَ

75. ከእነርሱም ቅጣት በፍጹም አይቀለልላቸዉም:: እነርሱም በእርሱ ውስጥ ተስፋ ቆራጮች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
76 : 43

وَمَا ظَلَمۡنَٰهُمۡ وَلَٰكِن كَانُواْ هُمُ ٱلظَّٰلِمِينَ

76. አልበደልናቸዉም:: በዳዮቹ ግን እነርሱው ብቻ ነበሩ:: info
التفاسير:

external-link copy
77 : 43

وَنَادَوۡاْ يَٰمَٰلِكُ لِيَقۡضِ عَلَيۡنَا رَبُّكَۖ قَالَ إِنَّكُم مَّٰكِثُونَ

77. «ማሊክ ሆይ! ጌታህ በእኛ ላይ (በሞት) ይፍረድ።» እያሉ ይጣራሉም:: ይላቸዋልም: «እናንተ (በቅጣት ውስጥ) ለዘላለም ነዋሪዎች ናችሁ። info
التفاسير:

external-link copy
78 : 43

لَقَدۡ جِئۡنَٰكُم بِٱلۡحَقِّ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَكُمۡ لِلۡحَقِّ كَٰرِهُونَ

78. «እውነተኛውን መንገድ በእርግጥ አመጣንላችሁ:: ግን አብዛኞቻችሁ እውነትን ጠይዎች ነበራችሁ» ይባላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
79 : 43

أَمۡ أَبۡرَمُوٓاْ أَمۡرٗا فَإِنَّا مُبۡرِمُونَ

79. ይልቁንም (በነብዩ ላይ) በማደም ነገርን አጠነከሩን? እኛም ተንኮላቸውን ወደ እነርሱ በመመለስ አጠንካሪዎች ነን:: info
التفاسير:

external-link copy
80 : 43

أَمۡ يَحۡسَبُونَ أَنَّا لَا نَسۡمَعُ سِرَّهُمۡ وَنَجۡوَىٰهُمۚ بَلَىٰ وَرُسُلُنَا لَدَيۡهِمۡ يَكۡتُبُونَ

80. ወይም እኛ ሚስጥራቸውንና ውይይታቸውን የማንሰማ መሆናችንን ያስባሉን? ነገሩ እነርሱ እንደሚሉት አይደለም:: መልዕክተኞቻችን እነርሱ ዘንድ ናቸው:: የሚሉትን ሁሉ ይጽፋሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
81 : 43

قُلۡ إِن كَانَ لِلرَّحۡمَٰنِ وَلَدٞ فَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلۡعَٰبِدِينَ

81. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ለአር-ረሕማን ልጅ (የለዉም እንጂ) ቢኖረው እኔ ለልጁ የተገዢዎች መጀመሪያ ነኝ» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
82 : 43

سُبۡحَٰنَ رَبِّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ رَبِّ ٱلۡعَرۡشِ عَمَّا يَصِفُونَ

82. የሰማያት፤ የምድርና የዙፋኑ ጌታ ከሓዲያን ስለ እሱ ከሚሉት ነገር ሁሉ ጠራ:: info
التفاسير:

external-link copy
83 : 43

فَذَرۡهُمۡ يَخُوضُواْ وَيَلۡعَبُواْ حَتَّىٰ يُلَٰقُواْ يَوۡمَهُمُ ٱلَّذِي يُوعَدُونَ

83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን ይስፈራሩበት የነበሩትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ በስህተታቸው ውስጥ ይዋኙ ተዋቸው :: ይጫዎቱም:: info
التفاسير:

external-link copy
84 : 43

وَهُوَ ٱلَّذِي فِي ٱلسَّمَآءِ إِلَٰهٞ وَفِي ٱلۡأَرۡضِ إِلَٰهٞۚ وَهُوَ ٱلۡحَكِيمُ ٱلۡعَلِيمُ

84. እርሱም ያ በሰማይ ውስጥ ሊገዙት የሚገባው በምድርም ውስጥ ሊገዙት የሚገባው ብቸኛ አምላክ ነው:: እርሱም ጥበበኛውና ሁሉን አዋቂው ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
85 : 43

وَتَبَارَكَ ٱلَّذِي لَهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَا وَعِندَهُۥ عِلۡمُ ٱلسَّاعَةِ وَإِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ

85. ያም የሰማያት፤ የምድርና በመካከላቸው ያለው ሁሉ ንግስና ለእርሱ ብቻ የሆነው አምላክ ላቀ:: የሰዓቲቱም የመምጫዋ ዘመን ዕውቀት በእርሱ ዘንድ ብቻ ነው:: ወደ እርሱም ብቻ ትመለሳላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
86 : 43

وَلَا يَمۡلِكُ ٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ مِن دُونِهِ ٱلشَّفَٰعَةَ إِلَّا مَن شَهِدَ بِٱلۡحَقِّ وَهُمۡ يَعۡلَمُونَ

86. እነዚያም ከአላህ ሌላ የሚገዟቸው አማልክት ሁሉ እነርሱ ትክክለኛውን የሚያውቁ ሆነው በእውነት ከመሰከሩት ክፍሎች በስተቀር ምልጃ አይችሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
87 : 43

وَلَئِن سَأَلۡتَهُم مَّنۡ خَلَقَهُمۡ لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُۖ فَأَنَّىٰ يُؤۡفَكُونَ

87. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ማን እንደ ፈጠራቸው ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ ነው ይላሉ:: ታዲያ (ከትክክለኛው እምነት) ወዴት ይዞራሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
88 : 43

وَقِيلِهِۦ يَٰرَبِّ إِنَّ هَٰٓؤُلَآءِ قَوۡمٞ لَّا يُؤۡمِنُونَ

88. (ነብዩ) ጌታዬ ሆይ! እነዚህ የማያምኑ ህዝቦች ናቸው የማለቱም እውቀቱ አላህ ዘንድ ብቻ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
89 : 43

فَٱصۡفَحۡ عَنۡهُمۡ وَقُلۡ سَلَٰمٞۚ فَسَوۡفَ يَعۡلَمُونَ

89. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን ተዋቸው:: «ነገሬ ስላም ነው» በልም:: ወደፊትም የሚመጣባቸውን ሲደርስ ያውቃሉ:: info
التفاسير: