पवित्र कुरअानको अर्थको अनुवाद - अम्हरी अनुवाद : अफ्रिका एकेडेमी ।

رقم الصفحة:close

external-link copy
118 : 11

وَلَوۡ شَآءَ رَبُّكَ لَجَعَلَ ٱلنَّاسَ أُمَّةٗ وَٰحِدَةٗۖ وَلَا يَزَالُونَ مُخۡتَلِفِينَ

118. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በሻ ኖሮ ሰዎችን ሁሉ አንድ ህዝብ ባደረጋቸው ነበር። የተለያዩም ከመሆን አይወገዱም:: info
التفاسير:

external-link copy
119 : 11

إِلَّا مَن رَّحِمَ رَبُّكَۚ وَلِذَٰلِكَ خَلَقَهُمۡۗ وَتَمَّتۡ كَلِمَةُ رَبِّكَ لَأَمۡلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنَ ٱلۡجِنَّةِ وَٱلنَّاسِ أَجۡمَعِينَ

119. ጌታህ ያዘነለት ብቻ ሲቀር ከመለያየት አይወገዱም:: ለዚሁም ነው የፈጠራቸው:: የጌታህ ቃልም «ገሀነምን ከአጋንንትና ከሰዎች ከሁሉም በእርግጥ እሞላታለሁ።» በማለት ተፈጸመች:: info
التفاسير:

external-link copy
120 : 11

وَكُلّٗا نَّقُصُّ عَلَيۡكَ مِنۡ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَۚ وَجَآءَكَ فِي هَٰذِهِ ٱلۡحَقُّ وَمَوۡعِظَةٞ وَذِكۡرَىٰ لِلۡمُؤۡمِنِينَ

120. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞቹም ዜናዎች ተፈላጊውን ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናጸናበትን እንተርክልሀለን። በዚህችም ሱራ እውነቱ ነገር፣ ለምእምናን ግሳጼና ማስታወሻ መጥቶልሀል:: info
التفاسير:

external-link copy
121 : 11

وَقُل لِّلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ ٱعۡمَلُواْ عَلَىٰ مَكَانَتِكُمۡ إِنَّا عَٰمِلُونَ

121. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነዚያም ለማያምኑት (እንዲህ) በላቸው: «ባላችሁበት ሁኔታ ላይ ሥሩ:: እኛ ሠሪዎች ነን። info
التفاسير:

external-link copy
122 : 11

وَٱنتَظِرُوٓاْ إِنَّا مُنتَظِرُونَ

122. «የራሳችሁን ውጤት ተጠባበቁ እኛ ተጠባባቂዎች ነንና።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
123 : 11

وَلِلَّهِ غَيۡبُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَإِلَيۡهِ يُرۡجَعُ ٱلۡأَمۡرُ كُلُّهُۥ فَٱعۡبُدۡهُ وَتَوَكَّلۡ عَلَيۡهِۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَٰفِلٍ عَمَّا تَعۡمَلُونَ

123. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሰማያትና በምድር ያለው ሚስጥር ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: ሁሉም ነገር ወደ እርሱ ብቻ ይመለሳል:: ስለዚህ እሱን ብቻ ተገዛው:: በእርሱም ላይ ብቻ ተመካ:: ጌታህም ከሚሰሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም:: info
التفاسير: