വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി

አን ነምል

external-link copy
1 : 27

طسٓۚ تِلۡكَ ءَايَٰتُ ٱلۡقُرۡءَانِ وَكِتَابٖ مُّبِينٍ

1. ጣ፤ ሲን፤ ይህ ከቁርኣኑና ከገላጩ መጽሐፍ አናቅጽ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
2 : 27

هُدٗى وَبُشۡرَىٰ لِلۡمُؤۡمِنِينَ

2. ለምዕምናን መሪና ብስራት ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 27

ٱلَّذِينَ يُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَيُؤۡتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَهُم بِٱلۡأٓخِرَةِ هُمۡ يُوقِنُونَ

3. ለእነዚያ ሶላትን ለሚሰግዱት፤ ዘካንም ለሚሰጡ፤ እነርሱም በመጨረሻይቱ ሕይወት እነርሱ የሚያረጋግጡ ለሆኑት:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 27

إِنَّ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ زَيَّنَّا لَهُمۡ أَعۡمَٰلَهُمۡ فَهُمۡ يَعۡمَهُونَ

4. እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ለእነርሱ ክፉ ሥራዎቻቸውን ሸለምንላቸው:: ስለዚህ እነርሱ ይዋልላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 27

أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ لَهُمۡ سُوٓءُ ٱلۡعَذَابِ وَهُمۡ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ هُمُ ٱلۡأَخۡسَرُونَ

5. እነርሱ እነዚያ ክፉ ቅጣት ያላባቸው ናቸው:: እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ በጣም ከከሳሪዎቹ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 27

وَإِنَّكَ لَتُلَقَّى ٱلۡقُرۡءَانَ مِن لَّدُنۡ حَكِيمٍ عَلِيمٍ

6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም ቁርኣንን ጥበበኛና አዋቂ ከሆነው ጌታህ ዘንድ በእርግጥ ትስሰጣለህ:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 27

إِذۡ قَالَ مُوسَىٰ لِأَهۡلِهِۦٓ إِنِّيٓ ءَانَسۡتُ نَارٗا سَـَٔاتِيكُم مِّنۡهَا بِخَبَرٍ أَوۡ ءَاتِيكُم بِشِهَابٖ قَبَسٖ لَّعَلَّكُمۡ تَصۡطَلُونَ

7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳ ለቤተሰቦቹ «እኔ እሳትን አየሁ ከእርሷ ወሬን አመጣላችኋለሁ፤ ወይም ትሞቁ ዘንድ የተለኮሰ ችቦን አመጣላችኋለሁ» ባለ ጊዜ የሆነውን አውሳላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
8 : 27

فَلَمَّا جَآءَهَا نُودِيَ أَنۢ بُورِكَ مَن فِي ٱلنَّارِ وَمَنۡ حَوۡلَهَا وَسُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

8. በመጣትም ጊዜ እንዲህ በማለት ተጠራ፡- «በእሳቲቱ ያለው ሰውና በዙሪያዋ ያሉም ሰዎች ሁሉ ተባረኩ:: የዓለማትም ጌታ አላህ ጥራት ይገባው። info
التفاسير:

external-link copy
9 : 27

يَٰمُوسَىٰٓ إِنَّهُۥٓ أَنَا ٱللَّهُ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ

9. «ሙሳ ሆይ! እነሆ እኔ አሸናፊዉና ጥበበኛው (አምላክህ) አላህ ነኝ። info
التفاسير:

external-link copy
10 : 27

وَأَلۡقِ عَصَاكَۚ فَلَمَّا رَءَاهَا تَهۡتَزُّ كَأَنَّهَا جَآنّٞ وَلَّىٰ مُدۡبِرٗا وَلَمۡ يُعَقِّبۡۚ يَٰمُوسَىٰ لَا تَخَفۡ إِنِّي لَا يَخَافُ لَدَيَّ ٱلۡمُرۡسَلُونَ

10. «በትርህንም ጣል» (ተባለና ጣለም):: እርሷ እንደ ትንሽ እባብ በፍጥነት ስትስለከለክ ባያትም ጊዜ ፊቱን አዙሮ ሸሸ:: አልተመለሰምም:: «ሙሳ ሆይ! አትፍራ:: መልዕክተኞች እኔ ዘንድ ፈጽሞ አይፈሩምና። info
التفاسير:

external-link copy
11 : 27

إِلَّا مَن ظَلَمَ ثُمَّ بَدَّلَ حُسۡنَۢا بَعۡدَ سُوٓءٖ فَإِنِّي غَفُورٞ رَّحِيمٞ

11. «ግን የበደለ ሰው ከዚያም ከመጥፎ ሥራው በኋላ መልካምን የለወጠ እኔ መሓሪ፤ አዛኝ ነኝ። info
التفاسير:

external-link copy
12 : 27

وَأَدۡخِلۡ يَدَكَ فِي جَيۡبِكَ تَخۡرُجۡ بَيۡضَآءَ مِنۡ غَيۡرِ سُوٓءٖۖ فِي تِسۡعِ ءَايَٰتٍ إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ وَقَوۡمِهِۦٓۚ إِنَّهُمۡ كَانُواْ قَوۡمٗا فَٰسِقِينَ

12. «እጅህንም በአንገትየህ ውስጥ አስገባ ያለ ነውር (ወይም ያለ ለምጽ) ነጭ ሆና ትወጣለችና በዘጠኝ ታዐምራት ወደ ፈርዖንና ወደ ሕዝቦቹ ሂድ እነርሱ አመጸኞች ህዝቦች ናቸውና።» info
التفاسير:

external-link copy
13 : 27

فَلَمَّا جَآءَتۡهُمۡ ءَايَٰتُنَا مُبۡصِرَةٗ قَالُواْ هَٰذَا سِحۡرٞ مُّبِينٞ

13. ተዓምራታችንም ግልጽ ሆና በመጣቻቸው ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው።» አሉ። info
التفاسير: