വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി

പേജ് നമ്പർ:close

external-link copy
11 : 14

قَالَتۡ لَهُمۡ رُسُلُهُمۡ إِن نَّحۡنُ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُكُمۡ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يَمُنُّ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنۡ عِبَادِهِۦۖ وَمَا كَانَ لَنَآ أَن نَّأۡتِيَكُم بِسُلۡطَٰنٍ إِلَّا بِإِذۡنِ ٱللَّهِۚ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلۡيَتَوَكَّلِ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ

11. መልዕክተኞቻቸውም ለእነርሱ አሉ: «እኛ ብጤያችሁ ሰዎች እንጂ ሌላ አይደለንም:: ግን አላህ ከባሮቹ መካከል በሚሻው ሰው ላይ ይለግሳል:: እኛም በአላህ ፈቃድ እንጂ ማስረጃን ልናመጣላችሁ አይገባንም:: በአላህ ላይ ብቻ ምእመናን ይጠጉ (ይመኩ)። info
التفاسير:

external-link copy
12 : 14

وَمَا لَنَآ أَلَّا نَتَوَكَّلَ عَلَى ٱللَّهِ وَقَدۡ هَدَىٰنَا سُبُلَنَاۚ وَلَنَصۡبِرَنَّ عَلَىٰ مَآ ءَاذَيۡتُمُونَاۚ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلۡيَتَوَكَّلِ ٱلۡمُتَوَكِّلُونَ

12. «መንገዳችንን በእርግጥ የመራን ሲሆን በአላህ ላይ የማንመካበት ምን አለን? በማሰቃየታችሁም ላይ እንታገሳለን:: በአላህ ላይ ብቻ ተመኪዎች ሁሉ ይመኩ።» (አሉ) info
التفاسير:

external-link copy
13 : 14

وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لِرُسُلِهِمۡ لَنُخۡرِجَنَّكُم مِّنۡ أَرۡضِنَآ أَوۡ لَتَعُودُنَّ فِي مِلَّتِنَاۖ فَأَوۡحَىٰٓ إِلَيۡهِمۡ رَبُّهُمۡ لَنُهۡلِكَنَّ ٱلظَّٰلِمِينَ

13. እነዚያ በአላህ የካዱት ለመልእክተኞቻቸው: «ከምድራችን በእርግጥ እናወጣችኋለን ወይም ወደ ሃይማኖታችን ትመለሳላችሁ።» አሉ:: ወደ እነርሱም ጌታቸው እንዲህ ሲል ላከ: «(ከሓዲያን) በዳዮችን እናጠፋለን። info
التفاسير:

external-link copy
14 : 14

وَلَنُسۡكِنَنَّكُمُ ٱلۡأَرۡضَ مِنۢ بَعۡدِهِمۡۚ ذَٰلِكَ لِمَنۡ خَافَ مَقَامِي وَخَافَ وَعِيدِ

14. «ከእነርሱ በኋላም በምድሪቱ በእርግጥ እናስቀምጣችኋለን:: ይህ በፊቴ መቆሙን ለሚፈራና ዛቻዬን ለሚፈራ ነው።» info
التفاسير:

external-link copy
15 : 14

وَٱسۡتَفۡتَحُواْ وَخَابَ كُلُّ جَبَّارٍ عَنِيدٖ

15. እርዳታንም ከአላህ ፈለጉ፤ ተረዱም። ጨካኝ ሞገደኛ የሆነም ሁሉ አፈረ። info
التفاسير:

external-link copy
16 : 14

مِّن وَرَآئِهِۦ جَهَنَّمُ وَيُسۡقَىٰ مِن مَّآءٖ صَدِيدٖ

16. ከስተፊቱ ገሀነም አለበት:: እዥ ከሆነም ውሃ ይጋታል:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 14

يَتَجَرَّعُهُۥ وَلَا يَكَادُ يُسِيغُهُۥ وَيَأۡتِيهِ ٱلۡمَوۡتُ مِن كُلِّ مَكَانٖ وَمَا هُوَ بِمَيِّتٖۖ وَمِن وَرَآئِهِۦ عَذَابٌ غَلِيظٞ

17. ይጎነጨዋል፤ ሊውጠዉም አይቀርብም:: ሞትም ከየስፍራው ሁሉ ይመጣበታል:: እርሱም የሚሞት አይደለም:: ከበስተፊቱም ከባድ ቅጣት አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 14

مَّثَلُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِرَبِّهِمۡۖ أَعۡمَٰلُهُمۡ كَرَمَادٍ ٱشۡتَدَّتۡ بِهِ ٱلرِّيحُ فِي يَوۡمٍ عَاصِفٖۖ لَّا يَقۡدِرُونَ مِمَّا كَسَبُواْ عَلَىٰ شَيۡءٖۚ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلضَّلَٰلُ ٱلۡبَعِيدُ

18. የእነዚያ በጌታቸው የካዱት ሰዎች መልካም ሥራዎቻቸው ምሳሌ በነፋሻ ቀን ነፋስ እንደ በረታችበት አመድ ነው:: በሠሩት ሥራ በምንም ላይ ሊጠቀሙ አይችሉም። ይህ እርሱ ሩቅ ጥፋት ነው:: info
التفاسير: