വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - മുഹമ്മദ് സ്വാദിഖ്

പേജ് നമ്പർ:close

external-link copy
20 : 75

كَلَّا بَلۡ تُحِبُّونَ ٱلۡعَاجِلَةَ

(ከመጣደፍ) ተከልከል፡፡ ይልቁንም (ሰዎች) ፈጣኒቱን (ዓለም) ትወዳላችሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
21 : 75

وَتَذَرُونَ ٱلۡأٓخِرَةَ

መጨረሻይቱንም (ዓለም) ትተዋላችሁ፡፡ (አትዘጋጁላትም)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
22 : 75

وُجُوهٞ يَوۡمَئِذٖ نَّاضِرَةٌ

ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
23 : 75

إِلَىٰ رَبِّهَا نَاظِرَةٞ

ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
24 : 75

وَوُجُوهٞ يَوۡمَئِذِۭ بَاسِرَةٞ

ፊቶችም በዚያ ቀን ጨፍጋጊዎች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
25 : 75

تَظُنُّ أَن يُفۡعَلَ بِهَا فَاقِرَةٞ

በርሳቸውም ዐደጋ እንደሚሠራባቸው ያረጋግጣሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
26 : 75

كَلَّآ إِذَا بَلَغَتِ ٱلتَّرَاقِيَ

ንቁ (ነፍስ) ብሪዎችን በደረሰች ጊዜ፤ info
التفاسير:

external-link copy
27 : 75

وَقِيلَ مَنۡۜ رَاقٖ

«አሻሪው ማነው?» በተባለም ጊዜ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
28 : 75

وَظَنَّ أَنَّهُ ٱلۡفِرَاقُ

(ሕመምተኛው) እርሱ (የሰፈረበት ነገር ከዚህ ዓለም) መልለየት መኾኑን ባረጋገጠም ጊዜ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
29 : 75

وَٱلۡتَفَّتِ ٱلسَّاقُ بِٱلسَّاقِ

ባትም በባት በተጣበቀች ጊዜ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
30 : 75

إِلَىٰ رَبِّكَ يَوۡمَئِذٍ ٱلۡمَسَاقُ

በዚያ ቀን መነዳቱ ወደ ጌታህ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
31 : 75

فَلَا صَدَّقَ وَلَا صَلَّىٰ

አላመነምም አልሰገደምም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
32 : 75

وَلَٰكِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ

ግን አስተባበለ፤ (ከእምነት) ዞረም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
33 : 75

ثُمَّ ذَهَبَ إِلَىٰٓ أَهۡلِهِۦ يَتَمَطَّىٰٓ

ከዚያም እየተንጎባለለ ወደ ቤተሰቡ ኼደ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
34 : 75

أَوۡلَىٰ لَكَ فَأَوۡلَىٰ

የምትጠላውን ነገር (አላህ) ያስከትልህ፡፡ ለአንተ ተገቢህም ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
35 : 75

ثُمَّ أَوۡلَىٰ لَكَ فَأَوۡلَىٰٓ

ከዚያም ጥፋት ይጠጋህ ለአንተ የተገባህም ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
36 : 75

أَيَحۡسَبُ ٱلۡإِنسَٰنُ أَن يُتۡرَكَ سُدًى

ሰው ስድ ኾኖ መትተውን ይጠረጥራልን? info
التفاسير:

external-link copy
37 : 75

أَلَمۡ يَكُ نُطۡفَةٗ مِّن مَّنِيّٖ يُمۡنَىٰ

የሚፈሰስ ከኾነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን? info
التفاسير:

external-link copy
38 : 75

ثُمَّ كَانَ عَلَقَةٗ فَخَلَقَ فَسَوَّىٰ

ከዚያም የረጋ ደም ኾነ (አላህ ሰው አድርጎ) ፈጠረውም፡፡ አስተካከለውም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
39 : 75

فَجَعَلَ مِنۡهُ ٱلزَّوۡجَيۡنِ ٱلذَّكَرَ وَٱلۡأُنثَىٰٓ

ከእርሱም ሁለት ዓይነቶችን ወንድና ሴትን አደረገ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
40 : 75

أَلَيۡسَ ذَٰلِكَ بِقَٰدِرٍ عَلَىٰٓ أَن يُحۡـِۧيَ ٱلۡمَوۡتَىٰ

ይህ (ጌታ) ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ አይደለምን? info
التفاسير: