വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - മുഹമ്മദ് സ്വാദിഖ്

പേജ് നമ്പർ:close

external-link copy
184 : 26

وَٱتَّقُواْ ٱلَّذِي خَلَقَكُمۡ وَٱلۡجِبِلَّةَ ٱلۡأَوَّلِينَ

«ያንንም የፈጠራችሁን የቀድሞዎቹንም ፍጡሮች (የፈጠረውን) ፍሩ፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
185 : 26

قَالُوٓاْ إِنَّمَآ أَنتَ مِنَ ٱلۡمُسَحَّرِينَ

አሉ «አንተ በብዛት ከተደገመባቸው ሰዎች ነህ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
186 : 26

وَمَآ أَنتَ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُنَا وَإِن نَّظُنُّكَ لَمِنَ ٱلۡكَٰذِبِينَ

«አንተም ብጤያችን ሰው እንጅ ሌላ አይደለህም፡፡ እነሆ ከውሸታሞች ነህ ብለን እንጠረጥርሃለን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
187 : 26

فَأَسۡقِطۡ عَلَيۡنَا كِسَفٗا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ

«ከእውነተኞቹም እንደኾንክ በእኛ ላይ ከሰማይ ቁራጭን ጣልብን፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
188 : 26

قَالَ رَبِّيٓ أَعۡلَمُ بِمَا تَعۡمَلُونَ

«ጌታዬ የምትሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው፤» አላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
189 : 26

فَكَذَّبُوهُ فَأَخَذَهُمۡ عَذَابُ يَوۡمِ ٱلظُّلَّةِۚ إِنَّهُۥ كَانَ عَذَابَ يَوۡمٍ عَظِيمٍ

አስተባበሉትም፡፡ የጥላይቷ ቀን ቅጣትም ያዛቸው፡፡ እርሱ የከባድ ቀን ቅጣት ነበርና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
190 : 26

إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ

በዚህ ውስጥ አስደናቂ ተዓምር አልለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም ምእምናን አልነበሩም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
191 : 26

وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ

ጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
192 : 26

وَإِنَّهُۥ لَتَنزِيلُ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

እርሱም (ቁርኣን) በእርግጥ ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
193 : 26

نَزَلَ بِهِ ٱلرُّوحُ ٱلۡأَمِينُ

እርሱን ታማኙ ጂብሪል አወረደው፤ info
التفاسير:

external-link copy
194 : 26

عَلَىٰ قَلۡبِكَ لِتَكُونَ مِنَ ٱلۡمُنذِرِينَ

ከአስፈራሪዎቹ (ነቢያት) ትኾን ዘንድ በልብህ ላይ (አወረደው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
195 : 26

بِلِسَانٍ عَرَبِيّٖ مُّبِينٖ

ግልጽ በኾነ ዐረብኛ ቋንቋ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
196 : 26

وَإِنَّهُۥ لَفِي زُبُرِ ٱلۡأَوَّلِينَ

እርሱም (ቁርኣን) በቀድሞዎቹ መጻሐፍት ውስጥ (የተወሳ ነው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
197 : 26

أَوَلَمۡ يَكُن لَّهُمۡ ءَايَةً أَن يَعۡلَمَهُۥ عُلَمَٰٓؤُاْ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ

የእስራኤል ልጆች ሊቃውንት የሚያውቁት መኾኑ ለእነርሱ (ለመካ ከሓዲዎች) ምልክት አይኾናቸውምን? info
التفاسير:

external-link copy
198 : 26

وَلَوۡ نَزَّلۡنَٰهُ عَلَىٰ بَعۡضِ ٱلۡأَعۡجَمِينَ

ከአዕጀሞች ባንዱ ላይ ባወረድነውም ኖሮ፤ info
التفاسير:

external-link copy
199 : 26

فَقَرَأَهُۥ عَلَيۡهِم مَّا كَانُواْ بِهِۦ مُؤۡمِنِينَ

በእነርሱ ላይ ባነበበውም በእርሱ አማኞች አይኾኑም ነበር፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
200 : 26

كَذَٰلِكَ سَلَكۡنَٰهُ فِي قُلُوبِ ٱلۡمُجۡرِمِينَ

እንደዚሁ (ማስተባበልን) በተንኮለኞች ልቦች ውስጥ አስገባነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
201 : 26

لَا يُؤۡمِنُونَ بِهِۦ حَتَّىٰ يَرَوُاْ ٱلۡعَذَابَ ٱلۡأَلِيمَ

አሳማሚ ቅጣትን እስከሚያዩ ድረስ በእርሱ አያምኑም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
202 : 26

فَيَأۡتِيَهُم بَغۡتَةٗ وَهُمۡ لَا يَشۡعُرُونَ

እነርሱ የማያውቁ ሲኾኑ (ቅጣቱ) ድንገት እስከሚመጣባቸውም ድረስ (አያምኑም)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
203 : 26

فَيَقُولُواْ هَلۡ نَحۡنُ مُنظَرُونَ

(በመጣባቸው ጊዜ) «እኛ የምንቆይ ነን?» እስከሚሉም (አያምኑም)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
204 : 26

أَفَبِعَذَابِنَا يَسۡتَعۡجِلُونَ

በቅጣታችን ያቻኩላሉን? info
التفاسير:

external-link copy
205 : 26

أَفَرَءَيۡتَ إِن مَّتَّعۡنَٰهُمۡ سِنِينَ

አየህን ብዙ ዓመታትን ብናጣቅማቸው፤ info
التفاسير:

external-link copy
206 : 26

ثُمَّ جَآءَهُم مَّا كَانُواْ يُوعَدُونَ

ከዚያም ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ቢመጣባቸው፤ info
التفاسير: