ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿ

አል ሙምተሂና

external-link copy
1 : 60

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَتَّخِذُواْ عَدُوِّي وَعَدُوَّكُمۡ أَوۡلِيَآءَ تُلۡقُونَ إِلَيۡهِم بِٱلۡمَوَدَّةِ وَقَدۡ كَفَرُواْ بِمَا جَآءَكُم مِّنَ ٱلۡحَقِّ يُخۡرِجُونَ ٱلرَّسُولَ وَإِيَّاكُمۡ أَن تُؤۡمِنُواْ بِٱللَّهِ رَبِّكُمۡ إِن كُنتُمۡ خَرَجۡتُمۡ جِهَٰدٗا فِي سَبِيلِي وَٱبۡتِغَآءَ مَرۡضَاتِيۚ تُسِرُّونَ إِلَيۡهِم بِٱلۡمَوَدَّةِ وَأَنَا۠ أَعۡلَمُ بِمَآ أَخۡفَيۡتُمۡ وَمَآ أَعۡلَنتُمۡۚ وَمَن يَفۡعَلۡهُ مِنكُمۡ فَقَدۡ ضَلَّ سَوَآءَ ٱلسَّبِيلِ

1. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጠላቶቼንና ጠላቶቻችሁን ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዙ:: የመጣላችሁን ትክክለኛ ሃይማኖት የካዱ ሲሆኑ ውዴታን ለእነርሱ ታደርጋላችሁ:: እነርሱ መልዕክተኛውና እናንተን በጌታችሁ በአላህ ስላመናችሁ ብቻ ከሀገራችሁ አስወጧችሁ። በመንገዴ ለመታገልና ውዴታየን ለመፈለግ የወጣችሁ እንደሆናችሁ እነርሱን ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዟቸው:: እኔ የምትደብቁትንና የምትገልጹትን የማውቅ ስሆን ከእነርሱ ጋር ፍቅር ትመሳጠራላችሁ:: ከናንተ መካከልም ይህንን ሚፈጽም ሰው ቀጥተኛውን መንገድ በእርግጥ ስቷል:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 60

إِن يَثۡقَفُوكُمۡ يَكُونُواْ لَكُمۡ أَعۡدَآءٗ وَيَبۡسُطُوٓاْ إِلَيۡكُمۡ أَيۡدِيَهُمۡ وَأَلۡسِنَتَهُم بِٱلسُّوٓءِ وَوَدُّواْ لَوۡ تَكۡفُرُونَ

2. ቢያሸንፏችሁ (ቢያገኟችሁ) ለእናንተ ጠላቶች ይሆናሉ:: እጆቻቸውና ምላሶቻቸውንም ወደ እናንተ በክፉ ይዘረጋሉ:: ብትክዱም ተመኙ:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 60

لَن تَنفَعَكُمۡ أَرۡحَامُكُمۡ وَلَآ أَوۡلَٰدُكُمۡۚ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ يَفۡصِلُ بَيۡنَكُمۡۚ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٞ

3. ዘመዶቻችሁም ሆኑ ልጆቻችሁ በትንሳኤ ቀን አይጠቅሟችሁም:: አላህ በትንሳኤ ቀን በመካከላችሁ (ብይን በመስጠት) ይለያል:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 60

قَدۡ كَانَتۡ لَكُمۡ أُسۡوَةٌ حَسَنَةٞ فِيٓ إِبۡرَٰهِيمَ وَٱلَّذِينَ مَعَهُۥٓ إِذۡ قَالُواْ لِقَوۡمِهِمۡ إِنَّا بُرَءَٰٓؤُاْ مِنكُمۡ وَمِمَّا تَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ كَفَرۡنَا بِكُمۡ وَبَدَا بَيۡنَنَا وَبَيۡنَكُمُ ٱلۡعَدَٰوَةُ وَٱلۡبَغۡضَآءُ أَبَدًا حَتَّىٰ تُؤۡمِنُواْ بِٱللَّهِ وَحۡدَهُۥٓ إِلَّا قَوۡلَ إِبۡرَٰهِيمَ لِأَبِيهِ لَأَسۡتَغۡفِرَنَّ لَكَ وَمَآ أَمۡلِكُ لَكَ مِنَ ٱللَّهِ مِن شَيۡءٖۖ رَّبَّنَا عَلَيۡكَ تَوَكَّلۡنَا وَإِلَيۡكَ أَنَبۡنَا وَإِلَيۡكَ ٱلۡمَصِيرُ

4. ኢብራሂምና እነዚያ ከእርሱ ጋር አብረው የነበሩት አማኞች ለእናንተ መልካም አርአያ ናቸው:: ይኸዉም ለህዝቦቻቸው «እኛ ከናንተና ከዚያ ከአላህ ሌላ ከምትገዙት ጣዖታት ሁሉ ንጹሆች ነን:: በእናንተም ካድን:: በአላህ አንድነት እስከምታምኑ ድረስ በእኛና በእናንተ መካከል ጠብና ጥላቻ ዘወትር ተገለጸ::» ባሉ ጊዜ ኢብራሂም ለአባቱ፡- «ላንተ ከአላህ ቅጣት ምንም የማልጠቅምህ (የማላድንህ) ስሆን ላንተ በእርግጥ ምህረትን እለምንልሃለሁ::» ማለቱ ብቻ ሲቀር «ጌታችን ሆይ ባንተ ላይ ተመካን ወደ አንተም ተመለስን መመለሻም ወደ አንተ ብቻ ነው::» (ባለው ተከተሉ።) info
التفاسير:

external-link copy
5 : 60

رَبَّنَا لَا تَجۡعَلۡنَا فِتۡنَةٗ لِّلَّذِينَ كَفَرُواْ وَٱغۡفِرۡ لَنَا رَبَّنَآۖ إِنَّكَ أَنتَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ

5. ጌታችን ሆይ! ለእነዚያ ለካዱት ሰዎች መሞከሪያ አታድረገን:: ለእኛ ምህረት አድርግልን:: ጌታችን ሆይ! አንተ አሸናፊና ጥበበኛው ነህ:: info
التفاسير: