ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿ

ಪುಟ ಸಂಖ್ಯೆ: 23:2 close

external-link copy
154 : 2

وَلَا تَقُولُواْ لِمَن يُقۡتَلُ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ أَمۡوَٰتُۢۚ بَلۡ أَحۡيَآءٞ وَلَٰكِن لَّا تَشۡعُرُونَ

154. በአላህ መንገድ (ለሀይማኖቱ) የሚገደሉትን «ሙታን ናቸው።» አትበሉ:: በእውነቱ ሕያው ናቸውና:: እናንተ ግን አትገነዘቡትም:: info
التفاسير:

external-link copy
155 : 2

وَلَنَبۡلُوَنَّكُم بِشَيۡءٖ مِّنَ ٱلۡخَوۡفِ وَٱلۡجُوعِ وَنَقۡصٖ مِّنَ ٱلۡأَمۡوَٰلِ وَٱلۡأَنفُسِ وَٱلثَّمَرَٰتِۗ وَبَشِّرِ ٱلصَّٰبِرِينَ

155. ከፍርሀትና ከርሀብም ከሀብት፣ ከሕይወትና ከአዝመራ በመቀነስም በእርግጥ እንሞክራችኋለን:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ታጋሾችንም (በገነት) አብስር:: info
التفاسير:

external-link copy
156 : 2

ٱلَّذِينَ إِذَآ أَصَٰبَتۡهُم مُّصِيبَةٞ قَالُوٓاْ إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّآ إِلَيۡهِ رَٰجِعُونَ

156. እነዚያ መከራ በነካቸቻው ጊዜ «እኛ ለአላህ ነን። እኛም ወደ እርሱ ተመላሾች ነን።» የሚሉትን አብስር። info
التفاسير:

external-link copy
157 : 2

أُوْلَٰٓئِكَ عَلَيۡهِمۡ صَلَوَٰتٞ مِّن رَّبِّهِمۡ وَرَحۡمَةٞۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُهۡتَدُونَ

157. እነዚያ በእነርሱ ላይ ከጌታቸው የሆኑ ምህረቶችና ችሮታም አሉ:: እነርሱም ወደ ቀናው መንገድ እውነት ተመሪዎቹ እነርሱው ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
158 : 2

۞ إِنَّ ٱلصَّفَا وَٱلۡمَرۡوَةَ مِن شَعَآئِرِ ٱللَّهِۖ فَمَنۡ حَجَّ ٱلۡبَيۡتَ أَوِ ٱعۡتَمَرَ فَلَا جُنَاحَ عَلَيۡهِ أَن يَطَّوَّفَ بِهِمَاۚ وَمَن تَطَوَّعَ خَيۡرٗا فَإِنَّ ٱللَّهَ شَاكِرٌ عَلِيمٌ

158. የሶፋና የመርዋ (ጋራዎች) የአላህን ትዕዛዝ ከመፈጸሚያ ጉልህ ቦታዎች (ምልክቶች) ናቸው:: ካዕባን በሐጅ ወይም በዑምራ ስራ ምክኒያት የጎበኘ ሁሉ በሁለቱ ጋራዎች መካከል በመመላለሱ ምንም ኃጢአት የለበትም:: መልካምንም ስራ በፈቃደኝነት የሰራ (ሁሉ አላህ ይመነዳዋል):: አላህ አመሰጋኝና ሁሉን አዋቂ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
159 : 2

إِنَّ ٱلَّذِينَ يَكۡتُمُونَ مَآ أَنزَلۡنَا مِنَ ٱلۡبَيِّنَٰتِ وَٱلۡهُدَىٰ مِنۢ بَعۡدِ مَا بَيَّنَّٰهُ لِلنَّاسِ فِي ٱلۡكِتَٰبِ أُوْلَٰٓئِكَ يَلۡعَنُهُمُ ٱللَّهُ وَيَلۡعَنُهُمُ ٱللَّٰعِنُونَ

159. እነዚያ (ስለነብዩ ሙሐመድና ሌሎችም) ከአናቅጽና ቅን መመሪያዎች ያወረድነውን ለሰዎች በመጽሐፍ ከገለጽነው በኋላ የሚደብቁትን ሁሉ አላህ ይረግማቸዋል:: ረጋሚዎችም ሁሉ ይረግሟቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
160 : 2

إِلَّا ٱلَّذِينَ تَابُواْ وَأَصۡلَحُواْ وَبَيَّنُواْ فَأُوْلَٰٓئِكَ أَتُوبُ عَلَيۡهِمۡ وَأَنَا ٱلتَّوَّابُ ٱلرَّحِيمُ

160. እነዚያ የተጸጸቱ፤ (ያበላሹትን) ያስተካከሉና (የደበቁትንም) የገለጹ ሲቀሩ:: የእነርሱን ጸጸትንማ እቀበላለሁ:: እኔም ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነኝ:: info
التفاسير:

external-link copy
161 : 2

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَمَاتُواْ وَهُمۡ كُفَّارٌ أُوْلَٰٓئِكَ عَلَيۡهِمۡ لَعۡنَةُ ٱللَّهِ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ وَٱلنَّاسِ أَجۡمَعِينَ

161. እነዚያ በአላህ የካዱና በክህደታቸው ላይ እያሉ የሞቱ ሰዎች በእነርሱ ላይ የአላህ፤ የመላዕክትና የመላው የሰው ዘር ሁሉ እርግማን አለባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
162 : 2

خَٰلِدِينَ فِيهَا لَا يُخَفَّفُ عَنۡهُمُ ٱلۡعَذَابُ وَلَا هُمۡ يُنظَرُونَ

162. በእርግማን ውስጥም ሁልጊዜ ዘውታሪዎች ይሆናሉ:: ቅጣቱ ከእነርሱ አይቃለልም። ጊዜም አይሰጡም:: info
التفاسير:

external-link copy
163 : 2

وَإِلَٰهُكُمۡ إِلَٰهٞ وَٰحِدٞۖ لَّآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلرَّحۡمَٰنُ ٱلرَّحِيمُ

163. (ሰዎች ሆይ!) አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: ከእርሱም ሌላ (ትክክለኛ) አምላክ የለም:: እርሱም እጅግ በጣም ሩህሩህና በጣም አዛኝ ነው:: info
التفاسير: