ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿ

ዩሱፍ

external-link copy
1 : 12

الٓرۚ تِلۡكَ ءَايَٰتُ ٱلۡكِتَٰبِ ٱلۡمُبِينِ

1.አሊፍ፤ ላም፤ ራ፤ እነዚህ አናቅጽ ግልጽና የተብራራ ከሆነው መጽሐፍ አናቅጽ ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
2 : 12

إِنَّآ أَنزَلۡنَٰهُ قُرۡءَٰنًا عَرَبِيّٗا لَّعَلَّكُمۡ تَعۡقِلُونَ

2. እኛ ይህንን ቁርኣንን ትረዱት ዘንድ በዐረበኛ ቋንቋ አወረድነው። info
التفاسير:

external-link copy
3 : 12

نَحۡنُ نَقُصُّ عَلَيۡكَ أَحۡسَنَ ٱلۡقَصَصِ بِمَآ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانَ وَإِن كُنتَ مِن قَبۡلِهِۦ لَمِنَ ٱلۡغَٰفِلِينَ

3.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህንን የቁርኣን ወደ አንተ በማውረዳችን እጅግ ውብና ማራኪ የሆነ ታሪክ እንተርክልሃለን:: ከዚህ በፊት አንተም ይህንን ታሪክ ከማያውቁት ነበርክ:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 12

إِذۡ قَالَ يُوسُفُ لِأَبِيهِ يَٰٓأَبَتِ إِنِّي رَأَيۡتُ أَحَدَ عَشَرَ كَوۡكَبٗا وَٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَ رَأَيۡتُهُمۡ لِي سَٰجِدِينَ

4. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነብዩ ዩሱፍ በልጅነቱ ለአባቱ «አባቴ ሆይ! እኔ አስራ አንድ ኮከቦችን፤ ጨረቃንና ጸሐይን ሲሰግዱልኝ በሕልሜ አየሁኝ።» ባለ ጊዜ የሆነውን ታሪክ ለህዝቦችህ አስታውስ። info
التفاسير: