ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಆಫ್ರಿಕಾ ಅಕಾಡೆಮಿ

ಪುಟ ಸಂಖ್ಯೆ:close

external-link copy
38 : 11

وَيَصۡنَعُ ٱلۡفُلۡكَ وَكُلَّمَا مَرَّ عَلَيۡهِ مَلَأٞ مِّن قَوۡمِهِۦ سَخِرُواْ مِنۡهُۚ قَالَ إِن تَسۡخَرُواْ مِنَّا فَإِنَّا نَسۡخَرُ مِنكُمۡ كَمَا تَسۡخَرُونَ

38. ከወገኖቹም መሪዎቹ በእርሱ አጠገብ ባለፉ ቁጥር በእርሱ ላይ እየተሳለቁበት መርከቢቱን ይሠራል። አላቸውም: «በእኛ ብትሳለቁ እኛም እንደተሳለቃችሁብን በእናንተ እንሳለቅባችኋለን። info
التفاسير:

external-link copy
39 : 11

فَسَوۡفَ تَعۡلَمُونَ مَن يَأۡتِيهِ عَذَابٞ يُخۡزِيهِ وَيَحِلُّ عَلَيۡهِ عَذَابٞ مُّقِيمٌ

39. «የሚያዋርደው ቅጣት የሚመጣበትን በእርሱም ላይ ዘውታሪ ቅጣት የሚሰፍርበትን ማንነት ወደ ፊት ታውቃላችሁ።» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
40 : 11

حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَ أَمۡرُنَا وَفَارَ ٱلتَّنُّورُ قُلۡنَا ٱحۡمِلۡ فِيهَا مِن كُلّٖ زَوۡجَيۡنِ ٱثۡنَيۡنِ وَأَهۡلَكَ إِلَّا مَن سَبَقَ عَلَيۡهِ ٱلۡقَوۡلُ وَمَنۡ ءَامَنَۚ وَمَآ ءَامَنَ مَعَهُۥٓ إِلَّا قَلِيلٞ

40. ትዕዛዛችንም በመጣና እቶኑም በገነፈለ ጊዜ «በመርከቧ ውስጥ ከየዓይነቱ ሁሉ ሁለት ሁለት (ወንድና ሴት) ቤተሰቦችህንም ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር ያመነንም ሰው ሁሉ ጫን።» አልነው:: ከእርሱም ጋር ጥቂቶች እንጂ አላመኑም ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
41 : 11

۞ وَقَالَ ٱرۡكَبُواْ فِيهَا بِسۡمِ ٱللَّهِ مَجۡر۪ىٰهَا وَمُرۡسَىٰهَآۚ إِنَّ رَبِّي لَغَفُورٞ رَّحِيمٞ

41. «‹መሄዷም መቆሟም በአላህ ስም ነው።› እያላችሁ በእርሷ ተሳፈሩ:: ጌታዬ መሓሪና አዛኝ ነውና።» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
42 : 11

وَهِيَ تَجۡرِي بِهِمۡ فِي مَوۡجٖ كَٱلۡجِبَالِ وَنَادَىٰ نُوحٌ ٱبۡنَهُۥ وَكَانَ فِي مَعۡزِلٖ يَٰبُنَيَّ ٱرۡكَب مَّعَنَا وَلَا تَكُن مَّعَ ٱلۡكَٰفِرِينَ

42. እርሷም እንደ ተራራዎች በሆነ ማዕበል ውስጥ እነርሱን ይዛቸው የምትንሻለል ስትሆን (በአላህ ስም ተቀመጡባት።) ኑህም ልጁን ከመርከቢቱ የራቀ ሆኖ ሳለ «ልጄ ሆይ! ከእኛ ጋር ተሳፈር። ከከሓዲያንም አትሁን።» ሲል ጠራው። info
التفاسير:

external-link copy
43 : 11

قَالَ سَـَٔاوِيٓ إِلَىٰ جَبَلٖ يَعۡصِمُنِي مِنَ ٱلۡمَآءِۚ قَالَ لَا عَاصِمَ ٱلۡيَوۡمَ مِنۡ أَمۡرِ ٱللَّهِ إِلَّا مَن رَّحِمَۚ وَحَالَ بَيۡنَهُمَا ٱلۡمَوۡجُ فَكَانَ مِنَ ٱلۡمُغۡرَقِينَ

43. ልጁም «ከውሃው ወደሚጠብቀኝ ተራራ እጠጋለሁ።» አለ:: አባቱም «ዛሬ ከአላህ ትዕዛዝ ምንም ጠባቂ የለም:: እርሱ ብቻ ያዘነለት ካልሆነ በስተቀር።» አለው:: ማዕበሉም በመካከላቸው ጋረደ:: ልጁም ከሰማጮች ሆነ:: info
التفاسير:

external-link copy
44 : 11

وَقِيلَ يَٰٓأَرۡضُ ٱبۡلَعِي مَآءَكِ وَيَٰسَمَآءُ أَقۡلِعِي وَغِيضَ ٱلۡمَآءُ وَقُضِيَ ٱلۡأَمۡرُ وَٱسۡتَوَتۡ عَلَى ٱلۡجُودِيِّۖ وَقِيلَ بُعۡدٗا لِّلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ

44. ተባለም «ምድር ሆይ! ዉሃሽን ዋጪ:: ሰማይ ሆይ! ዝናብሽን ያዢ።» ውሃዉም ሠረገ:: ቅጣቱም ተፈጸመ:: ጁዲይ በሚባለም ተራራ ላይ መርከቢቱ ተደላደለች:: «ለከሓዲያን ጥፋት ተገባቸው (ጥፉ)።» ተባለ። info
التفاسير:

external-link copy
45 : 11

وَنَادَىٰ نُوحٞ رَّبَّهُۥ فَقَالَ رَبِّ إِنَّ ٱبۡنِي مِنۡ أَهۡلِي وَإِنَّ وَعۡدَكَ ٱلۡحَقُّ وَأَنتَ أَحۡكَمُ ٱلۡحَٰكِمِينَ

45. ኑህም ጌታውን- «ጌታዬ ሆይ! ልጄ ከቤተሰቤ አንዱ ነው:: ቃል ኪዳንህም እውነት ነው:: አንተም ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ አዋቂ ነህ።» በማለት ጠየቀ (ተጣራ):: info
التفاسير: