ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಮುಹಮ್ಮದ್ ಸಾದಿಕ್

ಪುಟ ಸಂಖ್ಯೆ:close

external-link copy
114 : 4

۞ لَّا خَيۡرَ فِي كَثِيرٖ مِّن نَّجۡوَىٰهُمۡ إِلَّا مَنۡ أَمَرَ بِصَدَقَةٍ أَوۡ مَعۡرُوفٍ أَوۡ إِصۡلَٰحِۭ بَيۡنَ ٱلنَّاسِۚ وَمَن يَفۡعَلۡ ذَٰلِكَ ٱبۡتِغَآءَ مَرۡضَاتِ ٱللَّهِ فَسَوۡفَ نُؤۡتِيهِ أَجۡرًا عَظِيمٗا

ከውይይታቸው በብዙው ውስጥ ደግ ነገር የለበትም በምጽዋት ወይም በበጎ ሥራ ወይም በሰዎች መካከል በማስታረቅ ከሚያዙ ሰዎች ውይይት በስተቀር፡፡ ይኸንንም (የተባለውን) የአላህን ውዴታ ለመፈለግ የሚሠራ ሰው ታላቅ ምንዳን እንሰጠዋለን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
115 : 4

وَمَن يُشَاقِقِ ٱلرَّسُولَ مِنۢ بَعۡدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ ٱلۡهُدَىٰ وَيَتَّبِعۡ غَيۡرَ سَبِيلِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ نُوَلِّهِۦ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصۡلِهِۦ جَهَنَّمَۖ وَسَآءَتۡ مَصِيرًا

ቅኑም መንገድ ለእርሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምእምኖቹ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው (በዚህ ዓለም) በተሾመበት (ጥመት) ላይ እንሾመዋለን፤ ገሀነምንም እናገባዋለን፡፡ መመለሻይቱም ከፋች! info
التفاسير:

external-link copy
116 : 4

إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَغۡفِرُ أَن يُشۡرَكَ بِهِۦ وَيَغۡفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَآءُۚ وَمَن يُشۡرِكۡ بِٱللَّهِ فَقَدۡ ضَلَّ ضَلَٰلَۢا بَعِيدًا

አላህ በርሱ የማጋራትን (ወንጀል) አይምርም፡፡ ከዚህም ወዲያ ያለውን ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው (ከእውነት) የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
117 : 4

إِن يَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦٓ إِلَّآ إِنَٰثٗا وَإِن يَدۡعُونَ إِلَّا شَيۡطَٰنٗا مَّرِيدٗا

ከእርሱ ሌላ እንስታትን እንጅ አይገዙም፡፡ አመጸኛ ሰይጣንንም እንጅ ሌላን አይግገዙም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
118 : 4

لَّعَنَهُ ٱللَّهُۘ وَقَالَ لَأَتَّخِذَنَّ مِنۡ عِبَادِكَ نَصِيبٗا مَّفۡرُوضٗا

«አላህ የረገመውን ከባሮችህም የተወሰነን ድርሻ በእርግጥ እይዛለሁ» ያለውን (ሰይጣን እንጅ ሌላን አይከተሉም)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
119 : 4

وَلَأُضِلَّنَّهُمۡ وَلَأُمَنِّيَنَّهُمۡ وَلَأٓمُرَنَّهُمۡ فَلَيُبَتِّكُنَّ ءَاذَانَ ٱلۡأَنۡعَٰمِ وَلَأٓمُرَنَّهُمۡ فَلَيُغَيِّرُنَّ خَلۡقَ ٱللَّهِۚ وَمَن يَتَّخِذِ ٱلشَّيۡطَٰنَ وَلِيّٗا مِّن دُونِ ٱللَّهِ فَقَدۡ خَسِرَ خُسۡرَانٗا مُّبِينٗا

በእርግጥ አጠማቸዋለሁም፡፡ (ከንቱን) አስመኛቸዋለሁም፡፡ አዛቸውምና የእንስሶችን ጆሮዎች ይተለትላሉ፡፡ አዛቸውምና የአላህን ፍጥረት ይለውጣሉ፤ (ያለውን ይከተላሉ)፡፡ ከአላህም ሌላ ሰይጣንን ረዳት አድርጎ የሚይዝ ሰው ግልጽ ክስረትን በአርግጥ ከሰረ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
120 : 4

يَعِدُهُمۡ وَيُمَنِّيهِمۡۖ وَمَا يَعِدُهُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ إِلَّا غُرُورًا

(የማይፈጸመውን) ተስፋ ይሰጣቸዋል፡፡ ያስመኛቸዋልም፡፡ ሰይጣንም ለማታለል እንጅ አይቀጥራቸውም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
121 : 4

أُوْلَٰٓئِكَ مَأۡوَىٰهُمۡ جَهَنَّمُ وَلَا يَجِدُونَ عَنۡهَا مَحِيصٗا

እነዚያ መኖሪያቸው ገሀነም ናት፡፡ ከርስዋም መሸሻን አያገኙም፡፡ info
التفاسير: