ಪವಿತ್ರ ಕುರ್‌ಆನ್ ಅರ್ಥಾನುವಾದ - ಅಮ್ಹರಿ ಅನುವಾದ - ಮುಹಮ್ಮದ್ ಸಾದಿಕ್

ಪುಟ ಸಂಖ್ಯೆ:close

external-link copy
166 : 3

وَمَآ أَصَٰبَكُمۡ يَوۡمَ ٱلۡتَقَى ٱلۡجَمۡعَانِ فَبِإِذۡنِ ٱللَّهِ وَلِيَعۡلَمَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

ሁለቱ ጭፍሮችም በተጋጠሙ ቀን የደረሰባችሁ በአላህ ፈቃድ ነው፡፡ ምእምናንንም (ሊፈትንና) ሊገልጽ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
167 : 3

وَلِيَعۡلَمَ ٱلَّذِينَ نَافَقُواْۚ وَقِيلَ لَهُمۡ تَعَالَوۡاْ قَٰتِلُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ أَوِ ٱدۡفَعُواْۖ قَالُواْ لَوۡ نَعۡلَمُ قِتَالٗا لَّٱتَّبَعۡنَٰكُمۡۗ هُمۡ لِلۡكُفۡرِ يَوۡمَئِذٍ أَقۡرَبُ مِنۡهُمۡ لِلۡإِيمَٰنِۚ يَقُولُونَ بِأَفۡوَٰهِهِم مَّا لَيۡسَ فِي قُلُوبِهِمۡۚ وَٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِمَا يَكۡتُمُونَ

እነዚያንም የነፈቁትንና ለነርሱ «ኑ፤ በአላህ መንገድ ተጋደሉ፤ ወይም ተከላከሉ፤» የተባሉትን ሊገልጽ ነው፡፡ «መዋጋት (መኖሩን) ብናውቅ ኖሮ በተከተልናችሁ ነበር» አሉ፡፡ እነርሱ ያን ጊዜ ከእምነት ይልቅ ወደ ክህደት የቀረቡ ናቸው፡፡ በልቦቻቸው የሌለውን በአፎቻቸው ይናገራሉ፡፡ አላህም የሚደብቁትን ዐዋቂ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
168 : 3

ٱلَّذِينَ قَالُواْ لِإِخۡوَٰنِهِمۡ وَقَعَدُواْ لَوۡ أَطَاعُونَا مَا قُتِلُواْۗ قُلۡ فَٱدۡرَءُواْ عَنۡ أَنفُسِكُمُ ٱلۡمَوۡتَ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

እነዚያ (ከትግል) የቀሩ ሲኾኑ ለወንድሞቻቸው፡- «በታዘዙን ኖሮ ባልተገደሉ ነበር» ያሉ ናቸው፡፡ «እውነተኞች እንደኾናችሁ ከነፍሶቻችሁ ላይ ሞትን ገፍትሩ» በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
169 : 3

وَلَا تَحۡسَبَنَّ ٱلَّذِينَ قُتِلُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ أَمۡوَٰتَۢاۚ بَلۡ أَحۡيَآءٌ عِندَ رَبِّهِمۡ يُرۡزَقُونَ

እነዚያን በአላህ መንገድ የተገደሉትን ሙታን አድርገህ አትገምታቸው፡፡ በእርግጥ እነርሱ እጌታቸው ዘንድ ሕያዋን ናቸው፤ ይመገባሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
170 : 3

فَرِحِينَ بِمَآ ءَاتَىٰهُمُ ٱللَّهُ مِن فَضۡلِهِۦ وَيَسۡتَبۡشِرُونَ بِٱلَّذِينَ لَمۡ يَلۡحَقُواْ بِهِم مِّنۡ خَلۡفِهِمۡ أَلَّا خَوۡفٌ عَلَيۡهِمۡ وَلَا هُمۡ يَحۡزَنُونَ

አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ነገር ተደሳቾች ሲኾኑ (ይመገባሉ)፡፡ በነዚያም ከኋላቸው ገና በእነርሱ ባልተከተሉት በእነርሱ ላይ ፍርሃት ባለመኖሩና እነርሱም የማያዝኑ በመኾናቸው ይደሰታሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
171 : 3

۞ يَسۡتَبۡشِرُونَ بِنِعۡمَةٖ مِّنَ ٱللَّهِ وَفَضۡلٖ وَأَنَّ ٱللَّهَ لَا يُضِيعُ أَجۡرَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

ከአላህ በኾነ ጸጋና ልግስና አላህም የምእምናንን ምንዳ የማያጠፉ በመኾኑ ይደሰታሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
172 : 3

ٱلَّذِينَ ٱسۡتَجَابُواْ لِلَّهِ وَٱلرَّسُولِ مِنۢ بَعۡدِ مَآ أَصَابَهُمُ ٱلۡقَرۡحُۚ لِلَّذِينَ أَحۡسَنُواْ مِنۡهُمۡ وَٱتَّقَوۡاْ أَجۡرٌ عَظِيمٌ

እነዚያ መቁሰል ካገኛቸው በኋላ ለአላህና ለመልክተኛው የታዘዙት ከእነሱ ለነዚያ በጎ ለሠሩትና ለተጠነቀቁት ታላቅ ምንዳ አላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
173 : 3

ٱلَّذِينَ قَالَ لَهُمُ ٱلنَّاسُ إِنَّ ٱلنَّاسَ قَدۡ جَمَعُواْ لَكُمۡ فَٱخۡشَوۡهُمۡ فَزَادَهُمۡ إِيمَٰنٗا وَقَالُواْ حَسۡبُنَا ٱللَّهُ وَنِعۡمَ ٱلۡوَكِيلُ

እነዚያ ሰዎቹ ለእነርሱ፡- «ሰዎች ለእናንተ (ጦርን) አከማችተዋልና ፍሩዋቸው» ይሉዋቸውና (ይህም) እምነትን የጨመረላቸው «በቂያችንም አላህ ነው ምን ያምርም መጠጊያ!» ያሉ ናቸው፡፡ info
التفاسير: