ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
14 : 9

قَٰتِلُوهُمۡ يُعَذِّبۡهُمُ ٱللَّهُ بِأَيۡدِيكُمۡ وَيُخۡزِهِمۡ وَيَنصُرۡكُمۡ عَلَيۡهِمۡ وَيَشۡفِ صُدُورَ قَوۡمٖ مُّؤۡمِنِينَ

14. (ሙስሊሞች ሆይ!) ተጋደሏቸው:: አላህ በእጆቻችሁ ያሰቃያቸዋል:: ያዋርዳቸዋልም:: በእነርሱም ላይ ይረዳችኋል:: የአማኝ ህዝቦችን ልቦችንም ያሽራል:: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 9

وَيُذۡهِبۡ غَيۡظَ قُلُوبِهِمۡۗ وَيَتُوبُ ٱللَّهُ عَلَىٰ مَن يَشَآءُۗ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ

15. የልቦቻቸውንም ቁጭት ያስወግዳል:: አላህ ከሚፈልገው ሰው ላይ ጸጸትን ይቀበላል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 9

أَمۡ حَسِبۡتُمۡ أَن تُتۡرَكُواْ وَلَمَّا يَعۡلَمِ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ جَٰهَدُواْ مِنكُمۡ وَلَمۡ يَتَّخِذُواْ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَا رَسُولِهِۦ وَلَا ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَلِيجَةٗۚ وَٱللَّهُ خَبِيرُۢ بِمَا تَعۡمَلُونَ

16. አላህ ከመካከላችሁ በትክክል ለአላህ መስዋዕት የሚከፍሉትንና (የታገሉትንና) ከአላህ፣ ከመልዕክተኛውና ከትክክለኛ አማኞች በስተቀር አማካሪ ያልያዙትን ክፍሎች ለይቶ ሳያውቅ (ሳይገልጽ) የምትተዉ መሰላችሁን? አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ዉስጠ አዋቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 9

مَا كَانَ لِلۡمُشۡرِكِينَ أَن يَعۡمُرُواْ مَسَٰجِدَ ٱللَّهِ شَٰهِدِينَ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِم بِٱلۡكُفۡرِۚ أُوْلَٰٓئِكَ حَبِطَتۡ أَعۡمَٰلُهُمۡ وَفِي ٱلنَّارِ هُمۡ خَٰلِدُونَ

17. አጋሪዎች በራሳቸው ላይ በክህደት የሚመሰክሩ ሲሆኑ የአላህን መስጊዶች ሊንከባከቡ አይገባቸዉም:: እነዚያ ሥራዎቻቸው የተበላሹና በአኼራም በእሳት ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 9

إِنَّمَا يَعۡمُرُ مَسَٰجِدَ ٱللَّهِ مَنۡ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِ وَأَقَامَ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتَى ٱلزَّكَوٰةَ وَلَمۡ يَخۡشَ إِلَّا ٱللَّهَۖ فَعَسَىٰٓ أُوْلَٰٓئِكَ أَن يَكُونُواْ مِنَ ٱلۡمُهۡتَدِينَ

18. የአላህን መስጊዶች የሚንከባከቡ ሰዎች በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመኑ፤ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀው የሚሰግዱ፤ ግዴታ ምጽዋትን በትክክል የሚሰጡ፤ ከአላህ ሌላ ምንንም ያልፈሩ ሰዎች ብቻ ናቸው:: እንዲህ ያሉት ሰዎች ቀናዉን መስመር ከያዙት መሆናቸው ይከጀላልና:: info
التفاسير:

external-link copy
19 : 9

۞ أَجَعَلۡتُمۡ سِقَايَةَ ٱلۡحَآجِّ وَعِمَارَةَ ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِ كَمَنۡ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِ وَجَٰهَدَ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِۚ لَا يَسۡتَوُۥنَ عِندَ ٱللَّهِۗ وَٱللَّهُ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلظَّٰلِمِينَ

19. ሰዎችን ማጠጣትንና የተከበረውን መስጊድ መንከባከብን፤ በአላህና በመጨረሻው ቀን እንዳመነና በአላህ መንገድም እንደታገለ ሰው እምነትና ትግል አደረጋችሁትን? በአላህ ዘንድ ፈጽሞ ሁለቱ ተግባሮች አይስተካከሉም:: አላህ በዳይ ህዝቦችን ሁሉ ወደ ቀጥተኛው መንገድ አይመራምና:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 9

ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَهَاجَرُواْ وَجَٰهَدُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ بِأَمۡوَٰلِهِمۡ وَأَنفُسِهِمۡ أَعۡظَمُ دَرَجَةً عِندَ ٱللَّهِۚ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡفَآئِزُونَ

20. እነዚያ በአላህ ያመኑት ከየአገሮቻቸዉም የተሰደዱት በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸዉም በአላህ መንገድ ላይ የታገሉት አላህ ዘንድ በደረጃ በጣም የላቁ ናቸው:: ፍላጎታቸውን ያገኙ ማለትም እነርሱው ናቸው:: info
التفاسير: