ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

አል ቀመር

external-link copy
1 : 54

ٱقۡتَرَبَتِ ٱلسَّاعَةُ وَٱنشَقَّ ٱلۡقَمَرُ

1. የትንሳኤ ቀን ተቃረበ:: ጨረቃም ተገመሰ:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 54

وَإِن يَرَوۡاْ ءَايَةٗ يُعۡرِضُواْ وَيَقُولُواْ سِحۡرٞ مُّسۡتَمِرّٞ

2. ከሓዲያን ተዐምርን ቢያዩም እንቢ ብለው ይዞራሉ:: «ይህ ዘውታሪ ድግምት ነው» ይላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 54

وَكَذَّبُواْ وَٱتَّبَعُوٓاْ أَهۡوَآءَهُمۡۚ وَكُلُّ أَمۡرٖ مُّسۡتَقِرّٞ

3.አስተባበሉም :: ዝንባሌዎቻቸውንም ተከተሉ:: ነገርም ሁሉ (ወሰን አለው) ረጊ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
4 : 54

وَلَقَدۡ جَآءَهُم مِّنَ ٱلۡأَنۢبَآءِ مَا فِيهِ مُزۡدَجَرٌ

4. ከዜናዎቹ በእርሱ ውስጥ መገሰጫ የሚሆን ነገር ያለበት በእርግጥ መጣላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 54

حِكۡمَةُۢ بَٰلِغَةٞۖ فَمَا تُغۡنِ ٱلنُّذُرُ

5. ሙሉ ከሆነ ጥበብ (መጣላቸው):: ግን አስፈራሪዎች (ለማያምኑት) አይፈይዱም። info
التفاسير:

external-link copy
6 : 54

فَتَوَلَّ عَنۡهُمۡۘ يَوۡمَ يَدۡعُ ٱلدَّاعِ إِلَىٰ شَيۡءٖ نُّكُرٍ

6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ተውና ዙር። (ይልቁንስ) ጠሪው መልዓክ ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን አስታውስ። info
التفاسير:

external-link copy
7 : 54

خُشَّعًا أَبۡصَٰرُهُمۡ يَخۡرُجُونَ مِنَ ٱلۡأَجۡدَاثِ كَأَنَّهُمۡ جَرَادٞ مُّنتَشِرٞ

7. ዓይኖቻቸው ያቀረቀሩ ሆነውና ፍጹም የተበተኑ አንበጣ መስለው ከየመቃብሮቻቸው ይወጣሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 54

مُّهۡطِعِينَ إِلَى ٱلدَّاعِۖ يَقُولُ ٱلۡكَٰفِرُونَ هَٰذَا يَوۡمٌ عَسِرٞ

8. ወደ ጠሪው አንገቶቻቸውን ሳቢዎችና ቸኳዩች ሆነው ይወጣሉ:: ከሓዲያን ያን ጊዜ «ይህ ብርቱ ቀን ነው» ይላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
9 : 54

۞ كَذَّبَتۡ قَبۡلَهُمۡ قَوۡمُ نُوحٖ فَكَذَّبُواْ عَبۡدَنَا وَقَالُواْ مَجۡنُونٞ وَٱزۡدُجِرَ

9. ከእነርሱ በፊት የ(ነብዩ) ኑህ ህዝቦች አስተባበሉ:: ባሪያችንንም ኑህን አስተባበሉ:: «ዕብድ ነዉም» አሉት:: ተገላመጠም:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 54

فَدَعَا رَبَّهُۥٓ أَنِّي مَغۡلُوبٞ فَٱنتَصِرۡ

10. «ጌታውንም እኔ የተሸነፍኩ ነኝና እርዳኝ» ሲል ተጣራ:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 54

فَفَتَحۡنَآ أَبۡوَٰبَ ٱلسَّمَآءِ بِمَآءٖ مُّنۡهَمِرٖ

11. ወዲያውም የሰማይን ደጃፎች በሚንቧቧ ውሃ ከፈትን:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 54

وَفَجَّرۡنَا ٱلۡأَرۡضَ عُيُونٗا فَٱلۡتَقَى ٱلۡمَآءُ عَلَىٰٓ أَمۡرٖ قَدۡ قُدِرَ

12. የምድርንም ምንጮች በሃይል አፈነዳን:: የሰማዩና የምድሩ ውሃዉም ቀድሞ በተወሰነ ሁኔታ ላይ ተገናኘ:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 54

وَحَمَلۡنَٰهُ عَلَىٰ ذَاتِ أَلۡوَٰحٖ وَدُسُرٖ

13. ባለ ብዙ ሳንቃዎችና ባለ ብዙ ሚስማሮች በሆነቸው ታንኳ ላይም ጫንነው:: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 54

تَجۡرِي بِأَعۡيُنِنَا جَزَآءٗ لِّمَن كَانَ كُفِرَ

14. በጥበቃችን ስር ሆና ትንሻለላለች፡፡ ተክዶ ለነበረ ሰው ምንዳ ይህን ሰራን። info
التفاسير:

external-link copy
15 : 54

وَلَقَد تَّرَكۡنَٰهَآ ءَايَةٗ فَهَلۡ مِن مُّدَّكِرٖ

15. ተዓምር አድርገንም በእርግጥ ተውናት:: ተገሳጭ አለን? info
التفاسير:

external-link copy
16 : 54

فَكَيۡفَ كَانَ عَذَابِي وَنُذُرِ

16. ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ? info
التفاسير:

external-link copy
17 : 54

وَلَقَدۡ يَسَّرۡنَا ٱلۡقُرۡءَانَ لِلذِّكۡرِ فَهَلۡ مِن مُّدَّكِرٖ

17. ቁርኣንን ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው:: ተገንዛቢ አለን? info
التفاسير:

external-link copy
18 : 54

كَذَّبَتۡ عَادٞ فَكَيۡفَ كَانَ عَذَابِي وَنُذُرِ

18. የዓድ ህዝቦች አስተባበሉ:: ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ፤ info
التفاسير:

external-link copy
19 : 54

إِنَّآ أَرۡسَلۡنَا عَلَيۡهِمۡ رِيحٗا صَرۡصَرٗا فِي يَوۡمِ نَحۡسٖ مُّسۡتَمِرّٖ

19. እኛ በእነርሱ ላይ ዘወትር መናጢ በሆነ ቀን በኃይል የምንትሻሻ ነፋስን ላክንባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 54

تَنزِعُ ٱلنَّاسَ كَأَنَّهُمۡ أَعۡجَازُ نَخۡلٖ مُّنقَعِرٖ

20. ሰዎችንም ልክ ከስሮቻቸው እንደተጎለሰሱ የዘንባባ ግንዶች መስለው ከየተደበቁበት ትነቅላቸዋለች:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 54

فَكَيۡفَ كَانَ عَذَابِي وَنُذُرِ

21. ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ? info
التفاسير:

external-link copy
22 : 54

وَلَقَدۡ يَسَّرۡنَا ٱلۡقُرۡءَانَ لِلذِّكۡرِ فَهَلۡ مِن مُّدَّكِرٖ

22. ቁርኣንንም ለማስታወስ በእርግጥ አገራነው:: ተገሳጭ አለን? info
التفاسير:

external-link copy
23 : 54

كَذَّبَتۡ ثَمُودُ بِٱلنُّذُرِ

23. የሰሙድ ህዝቦች በአስፈራሪዎቹ አስተባበሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 54

فَقَالُوٓاْ أَبَشَرٗا مِّنَّا وَٰحِدٗا نَّتَّبِعُهُۥٓ إِنَّآ إِذٗا لَّفِي ضَلَٰلٖ وَسُعُرٍ

24. (እንዲህም) አሉ: «ከእኛ የሆነን አንድን ሰው እንከተለዋለን? እኛ ያ! ጊዜ በስህተትና በእብደት ውስጥ ነን አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
25 : 54

أَءُلۡقِيَ ٱلذِّكۡرُ عَلَيۡهِ مِنۢ بَيۡنِنَا بَلۡ هُوَ كَذَّابٌ أَشِرٞ

25. «ከእኛ መካከል በእርሱ ላይ ብቻ ማስገንዘቢያ ራዕይ ተጣለለትን? አይደለም እርሱ ውሸታም ኩሩ ነው» አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 54

سَيَعۡلَمُونَ غَدٗا مَّنِ ٱلۡكَذَّابُ ٱلۡأَشِرُ

26. ውሸታሙ ኩሩው ማን እንደሆነ ነገ በእርግጥ ያውቃሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
27 : 54

إِنَّا مُرۡسِلُواْ ٱلنَّاقَةِ فِتۡنَةٗ لَّهُمۡ فَٱرۡتَقِبۡهُمۡ وَٱصۡطَبِرۡ

27. እኛ ሴት ግመልን ለእነርሱ መፈተኛ ትሆን ዘንድ ላኪዎች ነን:: ተጠባበቃቸዉም ታገስም:: info
التفاسير:

external-link copy
28 : 54

وَنَبِّئۡهُمۡ أَنَّ ٱلۡمَآءَ قِسۡمَةُۢ بَيۡنَهُمۡۖ كُلُّ شِرۡبٖ مُّحۡتَضَرٞ

28. ውሃዉም በመካከላቸው የተከፈለ መሆኑን ንገራቸው:: ከውሃ የሆነ ፈንታ ሁሉ በየተራ የሚጣዱት ነው። info
التفاسير:

external-link copy
29 : 54

فَنَادَوۡاْ صَاحِبَهُمۡ فَتَعَاطَىٰ فَعَقَرَ

29. ጓደኛቸውንም ጠሩት:: ወዲያዉም (ሰይፉን) ተቀበለ:: ወጋትም:: info
التفاسير:

external-link copy
30 : 54

فَكَيۡفَ كَانَ عَذَابِي وَنُذُرِ

30. ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ? info
التفاسير:

external-link copy
31 : 54

إِنَّآ أَرۡسَلۡنَا عَلَيۡهِمۡ صَيۡحَةٗ وَٰحِدَةٗ فَكَانُواْ كَهَشِيمِ ٱلۡمُحۡتَظِرِ

31. እኛ በእነርሱ ላይ አንዲትን ጩኸት ላክንባቸው። ወዲያዉም ከበረት አጣሪ (አጥር) እንደ ተሰባበረ እርጋፊ ሆኑ። info
التفاسير:

external-link copy
32 : 54

وَلَقَدۡ يَسَّرۡنَا ٱلۡقُرۡءَانَ لِلذِّكۡرِ فَهَلۡ مِن مُّدَّكِرٖ

32. ቁርኣንን ለመገንዘብ አገራነው:: ተገሳጭ አለን? info
التفاسير:

external-link copy
33 : 54

كَذَّبَتۡ قَوۡمُ لُوطِۭ بِٱلنُّذُرِ

33. የ(ነብዩ) ሉጥ ህዝብ በአስፈራሪዎቹ አስተባበሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
34 : 54

إِنَّآ أَرۡسَلۡنَا عَلَيۡهِمۡ حَاصِبًا إِلَّآ ءَالَ لُوطٖۖ نَّجَّيۡنَٰهُم بِسَحَرٖ

34. እኛ በእነርሱ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስ ላክን:: የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ እነርሱንስ በሌሊት መጨረሻ ላይ አዳንናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
35 : 54

نِّعۡمَةٗ مِّنۡ عِندِنَاۚ كَذَٰلِكَ نَجۡزِي مَن شَكَرَ

35. ከእኛ በሆነ ጸጋ አዳናቸው:: ልክ እንደዚሁ ያመሰገነን ሰው እንመነዳለን:: info
التفاسير:

external-link copy
36 : 54

وَلَقَدۡ أَنذَرَهُم بَطۡشَتَنَا فَتَمَارَوۡاْ بِٱلنُّذُرِ

36. ብርቱ አያያዛችንን በእርግጥ አስጠነቀቅናቸው:: በማስጠንቀቂያዎቹም ተከራከሩ። info
التفاسير:

external-link copy
37 : 54

وَلَقَدۡ رَٰوَدُوهُ عَن ضَيۡفِهِۦ فَطَمَسۡنَآ أَعۡيُنَهُمۡ فَذُوقُواْ عَذَابِي وَنُذُرِ

37. ከእንግዶቹም እንዲያስመቻቸው ደጋግመው ፈለጉት። ወዲያዉም ዓይኖቻቸውን አበስን። ቅጣቱንና ማስጠንቀቂያዎቹን ቅመሱ አልናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
38 : 54

وَلَقَدۡ صَبَّحَهُم بُكۡرَةً عَذَابٞ مُّسۡتَقِرّٞ

38. በማለዳም ዘወታሪ የሆነ ቅጣት በእርግጥ ማለደባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
39 : 54

فَذُوقُواْ عَذَابِي وَنُذُرِ

39. ቅጣቱንና ማስጠንቀቂያዎችም ቅመሱ ተባሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
40 : 54

وَلَقَدۡ يَسَّرۡنَا ٱلۡقُرۡءَانَ لِلذِّكۡرِ فَهَلۡ مِن مُّدَّكِرٖ

40 ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው:: ተገሳጭ አለን? info
التفاسير:

external-link copy
41 : 54

وَلَقَدۡ جَآءَ ءَالَ فِرۡعَوۡنَ ٱلنُّذُرُ

41.የፈርዖንን ቤተሰቦችም ማስጠንቀቂያዎች በእርግጥ መጧቸው። info
التفاسير:

external-link copy
42 : 54

كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا كُلِّهَا فَأَخَذۡنَٰهُمۡ أَخۡذَ عَزِيزٖ مُّقۡتَدِرٍ

42. በተዓምራታችንም በሁሏም አስተባበሉ:: የብርቱ ቻይንም አቀጣጥ ቀጣናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
43 : 54

أَكُفَّارُكُمۡ خَيۡرٞ مِّنۡ أُوْلَٰٓئِكُمۡ أَمۡ لَكُم بَرَآءَةٞ فِي ٱلزُّبُرِ

43. የእናንተ ከሓዲያኖቻችሁ ከእነዚያችሁ በላጮች ናቸውን? ወይስ ለእናንተ በመጽሐፎች ውስጥ በተለየ የተነገረ ነፃነት አላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
44 : 54

أَمۡ يَقُولُونَ نَحۡنُ جَمِيعٞ مُّنتَصِرٞ

44. ወይስ «እኛ የተረዳን ክምቹዎች ነን» ይላሉ? info
التفاسير:

external-link copy
45 : 54

سَيُهۡزَمُ ٱلۡجَمۡعُ وَيُوَلُّونَ ٱلدُّبُرَ

45. ክምቹዎቹ በእርግጥ ድል ይመታሉ:: ጀርባዎቻቸውንም ያዞራሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
46 : 54

بَلِ ٱلسَّاعَةُ مَوۡعِدُهُمۡ وَٱلسَّاعَةُ أَدۡهَىٰ وَأَمَرُّ

46. ይልቁንም ሰዓቲቱ ትንሳኤ ቀጠሯቸው ናት:: ሰዓቲቱም በጣም የከበደችና የመረረች ናት:: info
التفاسير:

external-link copy
47 : 54

إِنَّ ٱلۡمُجۡرِمِينَ فِي ضَلَٰلٖ وَسُعُرٖ

47. አመጸኞች በስህተትና በእሳቶች ውስጥ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
48 : 54

يَوۡمَ يُسۡحَبُونَ فِي ٱلنَّارِ عَلَىٰ وُجُوهِهِمۡ ذُوقُواْ مَسَّ سَقَرَ

48. በእሳት ውስጥ በፊታቸው በሚጎተቱበት ቀን የሰቀርን (የገሀነምን) ቅጣት መንካትን ቅመሱ ይባላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
49 : 54

إِنَّا كُلَّ شَيۡءٍ خَلَقۡنَٰهُ بِقَدَرٖ

49. እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው:: info
التفاسير:

external-link copy
50 : 54

وَمَآ أَمۡرُنَآ إِلَّا وَٰحِدَةٞ كَلَمۡحِۭ بِٱلۡبَصَرِ

50. ትዕዛዛችንም እንደ ዓይን ቅጽበት የሆነች አንዲት ቃል እንጂ ሌላ አይደለችም:: info
التفاسير:

external-link copy
51 : 54

وَلَقَدۡ أَهۡلَكۡنَآ أَشۡيَاعَكُمۡ فَهَلۡ مِن مُّدَّكِرٖ

51. ብጤዎቻችሁንም በእርግጥ አጠፋን፤ ተገሳጭ አለን? info
التفاسير:

external-link copy
52 : 54

وَكُلُّ شَيۡءٖ فَعَلُوهُ فِي ٱلزُّبُرِ

52. የሰሩትም ነገር ሁሉ በመጽሐፎች ውስጥ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
53 : 54

وَكُلُّ صَغِيرٖ وَكَبِيرٖ مُّسۡتَطَرٌ

53. ትንሹም ትልቁም ሁሉ የተፃፈ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
54 : 54

إِنَّ ٱلۡمُتَّقِينَ فِي جَنَّٰتٖ وَنَهَرٖ

54. አላህን ፈሪ የሆኑ ሰዎች ሁሉ በአትክልቶችና በወንዞች ውስጥ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
55 : 54

فِي مَقۡعَدِ صِدۡقٍ عِندَ مَلِيكٖ مُّقۡتَدِرِۭ

55. እነርሱም (ውድቅ ቃልና መውወንጀል በሌለበት) በእውነት መቀመጫ ውስጥ ላይ ከሆነው ንጉስ አላህ ዘንድ ናቸው:: info
التفاسير: