ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
19 : 35

وَمَا يَسۡتَوِي ٱلۡأَعۡمَىٰ وَٱلۡبَصِيرُ

19. እውርና የሚያይ አይሰተካከሉም፤ info
التفاسير:

external-link copy
20 : 35

وَلَا ٱلظُّلُمَٰتُ وَلَا ٱلنُّورُ

20. ጨለማዎችና ብርሃንም፤ info
التفاسير:

external-link copy
21 : 35

وَلَا ٱلظِّلُّ وَلَا ٱلۡحَرُورُ

21. ጥላና ሐሩርም። info
التفاسير:

external-link copy
22 : 35

وَمَا يَسۡتَوِي ٱلۡأَحۡيَآءُ وَلَا ٱلۡأَمۡوَٰتُۚ إِنَّ ٱللَّهَ يُسۡمِعُ مَن يَشَآءُۖ وَمَآ أَنتَ بِمُسۡمِعٖ مَّن فِي ٱلۡقُبُورِ

22. ህያውና ሙታንም አይስተካከሉም:: አላህ የሚሻውን ሰው ያሰማል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ግን በመቃብር ውስጥ ያሉትን አሰሚ አይደለህም:: info
التفاسير:

external-link copy
23 : 35

إِنۡ أَنتَ إِلَّا نَذِيرٌ

23. አንተ አስጠንቃቂ እንጂ ሌላ አይደለህም:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 35

إِنَّآ أَرۡسَلۡنَٰكَ بِٱلۡحَقِّ بَشِيرٗا وَنَذِيرٗاۚ وَإِن مِّنۡ أُمَّةٍ إِلَّا خَلَا فِيهَا نَذِيرٞ

24. እኛ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን በእውነቱ መምሪያ ላክንህ:: ማንኛይቱም ህዝብ በውስጧ አስፈራሪ ያላለፈባት የለችም:: info
التفاسير:

external-link copy
25 : 35

وَإِن يُكَذِّبُوكَ فَقَدۡ كَذَّبَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ جَآءَتۡهُمۡ رُسُلُهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ وَبِٱلزُّبُرِ وَبِٱلۡكِتَٰبِ ٱلۡمُنِيرِ

25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉህም ከእነዚህ ከበፊታቸው የነበሩትም ህዝቦች በእርግጥ ነብያትን አስተባብለዋል:: መልዕክተኞቻቸው በግልጽ ማስረጃዎች፣ በጹሁፎችም አብራሪ በሆነ መጽሐፍም መጥተዋቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 35

ثُمَّ أَخَذۡتُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْۖ فَكَيۡفَ كَانَ نَكِيرِ

26. ከዚያም እነዚያን የካዱትን ቀጣኋቸው:: ቅጣቴም እንዴት ነበር! (በስፍራው ነው ተገቢ ነው)። info
التفاسير:

external-link copy
27 : 35

أَلَمۡ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَأَخۡرَجۡنَا بِهِۦ ثَمَرَٰتٖ مُّخۡتَلِفًا أَلۡوَٰنُهَاۚ وَمِنَ ٱلۡجِبَالِ جُدَدُۢ بِيضٞ وَحُمۡرٞ مُّخۡتَلِفٌ أَلۡوَٰنُهَا وَغَرَابِيبُ سُودٞ

27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ከሰማይ ውሃን ማውረዱን አላየህምን? በእርሱም ዓይነቶቻቸው የተለያዩ ፍሬዎችን አወጣን:: ከጋራዎችም መልካቸው የተለያዩ ነጮችም፤ ቀዮችም፤ በጣም ጥቁሮችም የሆኑ መንገዶች አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
28 : 35

وَمِنَ ٱلنَّاسِ وَٱلدَّوَآبِّ وَٱلۡأَنۡعَٰمِ مُخۡتَلِفٌ أَلۡوَٰنُهُۥ كَذَٰلِكَۗ إِنَّمَا يَخۡشَى ٱللَّهَ مِنۡ عِبَادِهِ ٱلۡعُلَمَٰٓؤُاْۗ إِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ غَفُورٌ

28. ከሰዎችም፤ ከተንቀሳቃሾችም፤ ከቤት እንስሳዎችም እንደዚሁ መልኮቻቸው የተለያዩ አሉ:: አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት አዋቂዎቹ ብቻ ናቸው:: አላህ አሸናፊና መሃሪ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
29 : 35

إِنَّ ٱلَّذِينَ يَتۡلُونَ كِتَٰبَ ٱللَّهِ وَأَقَامُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَأَنفَقُواْ مِمَّا رَزَقۡنَٰهُمۡ سِرّٗا وَعَلَانِيَةٗ يَرۡجُونَ تِجَٰرَةٗ لَّن تَبُورَ

29. እነዚያ የአላህን መጽሐፍ የሚያነቡ፣ ሶላትን አስተካክለው የሰገዱ፤ ከሰጠናቸዉም ሲሳይ በምስጢርም ሆነ በግልጽ የለገሱ የማትከስርን ንግድ ተስፋ ያደርጋሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
30 : 35

لِيُوَفِّيَهُمۡ أُجُورَهُمۡ وَيَزِيدَهُم مِّن فَضۡلِهِۦٓۚ إِنَّهُۥ غَفُورٞ شَكُورٞ

30. ምንዳዎቻቸውን ሊሞላላቸው ከችሮታዉም ሊጨምርላቸው ተስፋ ያደርጋሉ:: እርሱ በጣም መሃሪና አመስጋኝ ነውና:: info
التفاسير: