ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
21 : 32

وَلَنُذِيقَنَّهُم مِّنَ ٱلۡعَذَابِ ٱلۡأَدۡنَىٰ دُونَ ٱلۡعَذَابِ ٱلۡأَكۡبَرِ لَعَلَّهُمۡ يَرۡجِعُونَ

21. ይመለሱ ዘንድ ከትልቁ ቅጣት በፊት (በዚህ ዓለም) ትንሹን ቅጣት በእርግጥ እናቀምሳቸዋለን:: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 32

وَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّن ذُكِّرَ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِۦ ثُمَّ أَعۡرَضَ عَنۡهَآۚ إِنَّا مِنَ ٱلۡمُجۡرِمِينَ مُنتَقِمُونَ

22. በጌታዉም አናቅጽ ከተገሰጸና ከዚያም ከተዋት ሰው ይበልጥ በደለኛ ማነው? (የለም) እኛ ከተንኮለኞቹ ሁሉ ተበቃዮች ነን:: info
التفاسير:

external-link copy
23 : 32

وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ فَلَا تَكُن فِي مِرۡيَةٖ مِّن لِّقَآئِهِۦۖ وَجَعَلۡنَٰهُ هُدٗى لِّبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ

23.ሙሳን መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱን ከመገናኘትህም በመጠራጠር ውስጥ አትሁን:: ለኢስራኢል ልጆችም መሪ አደረግነው:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 32

وَجَعَلۡنَا مِنۡهُمۡ أَئِمَّةٗ يَهۡدُونَ بِأَمۡرِنَا لَمَّا صَبَرُواْۖ وَكَانُواْ بِـَٔايَٰتِنَا يُوقِنُونَ

24. በታገሱና በተዓምራታችን የሚያረጋግጡ በሆኑም ጊዜ ከእነርሱ በትዕዛዛችን የሚመሩ መሪዎችን አደረግን:: info
التفاسير:

external-link copy
25 : 32

إِنَّ رَبَّكَ هُوَ يَفۡصِلُ بَيۡنَهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ فِيمَا كَانُواْ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَ

25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በዚያ ይለያዩበት በነበሩት ነገር ሁሉ በትንሳኤ ቀን በመካከላቸው በፍርድ ይለያል:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 32

أَوَلَمۡ يَهۡدِ لَهُمۡ كَمۡ أَهۡلَكۡنَا مِن قَبۡلِهِم مِّنَ ٱلۡقُرُونِ يَمۡشُونَ فِي مَسَٰكِنِهِمۡۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٍۚ أَفَلَا يَسۡمَعُونَ

26. ከክፍለ ዘመናት ሰዎች ብዙዎችን ያጠፋን መሆናችን በመኖሪያዎቻቸው የሚሄዱ ሲሆኑ እነርሱ አልተገለጸላቸዉምን? በዚህ ውስጥ አያሌ ምልክቶች አሉበት:: አይሰሙምን? info
التفاسير:

external-link copy
27 : 32

أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ أَنَّا نَسُوقُ ٱلۡمَآءَ إِلَى ٱلۡأَرۡضِ ٱلۡجُرُزِ فَنُخۡرِجُ بِهِۦ زَرۡعٗا تَأۡكُلُ مِنۡهُ أَنۡعَٰمُهُمۡ وَأَنفُسُهُمۡۚ أَفَلَا يُبۡصِرُونَ

27. እኛ ውሃን ወደ ደረቅ ምድር የምንነዳ እንስሶቻቸውና ነፍሶቻቸው ከእርሱ የሚበሉለትንም አዝመራ በእርሱ የምናወጣ መሆናችንን አያዩምን? አይመለከቱምን? info
التفاسير:

external-link copy
28 : 32

وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلۡفَتۡحُ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

28. «ከእውነተኞችም እንደ ሆናችሁ ይህ ፍርድ መቼ ነው።» ይላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
29 : 32

قُلۡ يَوۡمَ ٱلۡفَتۡحِ لَا يَنفَعُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِيمَٰنُهُمۡ وَلَا هُمۡ يُنظَرُونَ

29. «በፍርዱ ቀን እነዚያን የካዱትን ሰዎች እምነታቸው አይጠቅማቸዉም:: እነርሱም ጊዜን አይሰጡም።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
30 : 32

فَأَعۡرِضۡ عَنۡهُمۡ وَٱنتَظِرۡ إِنَّهُم مُّنتَظِرُونَ

30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን ተዋቸው:: ተጠባበቅም:: እነርሱም ተጠባባቂዎች ናቸውና:: info
التفاسير: