ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

አል ሉቅማን

external-link copy
1 : 31

الٓمٓ

1. አሊፍ፤ ላም፤ ሚይም፤ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 31

تِلۡكَ ءَايَٰتُ ٱلۡكِتَٰبِ ٱلۡحَكِيمِ

2. እነዚህ አናቅጽ ጥበብ ከተሞላው መጽሐፍ ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
3 : 31

هُدٗى وَرَحۡمَةٗ لِّلۡمُحۡسِنِينَ

3. ለበጎ አድራጊዎች ሁሉ መሪ፣ እዝነት ሲሆን፤ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 31

ٱلَّذِينَ يُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَيُؤۡتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَهُم بِٱلۡأٓخِرَةِ هُمۡ يُوقِنُونَ

4. ለእነዚያ ሶላትን አስተካክለው ለሚሰግዱ፤ ዘካንም ለሚሰጡት፤ በመጨረሻይቱም ዓለም የሚያረጋግጡ ለሆኑት፤ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 31

أُوْلَٰٓئِكَ عَلَىٰ هُدٗى مِّن رَّبِّهِمۡۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ

5. እነዚያ (የተጠቀሱትን ባህሪያት የሚላበሱ ሰዎች ሁሉ) በጌታቸው መመሪያ ላይ የሚጓዙ ናቸው። እነዚያ ፍላጎታቸውንም ያገኙትም እነርሱ ብቻ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 31

وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَشۡتَرِي لَهۡوَ ٱلۡحَدِيثِ لِيُضِلَّ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ بِغَيۡرِ عِلۡمٖ وَيَتَّخِذَهَا هُزُوًاۚ أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ عَذَابٞ مُّهِينٞ

6. ከሰዎች መካከል ያለ ምንም እውቀት ሰዎችን ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና የአላህን መንገድ ማላገጫ ሊያደርግ አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ:: እነዚያ ይህን የሚያደርጉ ሁሉ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አለባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 31

وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِ ءَايَٰتُنَا وَلَّىٰ مُسۡتَكۡبِرٗا كَأَن لَّمۡ يَسۡمَعۡهَا كَأَنَّ فِيٓ أُذُنَيۡهِ وَقۡرٗاۖ فَبَشِّرۡهُ بِعَذَابٍ أَلِيمٍ

7. አናቅጻችን በእርሱ ላይ በሚነበቡ ጊዜ እንዳልሰማትና በጆሮቹ ድንቁርና እንዳለበት የኮራ ሆኖ ይዞራል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህን ሰው በአሳማሚ ቅጣት አብስረው:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 31

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُمۡ جَنَّٰتُ ٱلنَّعِيمِ

8. እነዚያ ያመኑና መልካሞችን ተግባራት የሰሩ ሁሉ ለእነርሱ የጸጋ ገነቶች አሏቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 31

خَٰلِدِينَ فِيهَاۖ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقّٗاۚ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ

9. በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ሲሆኑ አላህ እውነተኛን የተስፋ ቃል ገባላቸው:: እርሱም ሁሉንም አሸናፊና ጥበበኛ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 31

خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ بِغَيۡرِ عَمَدٖ تَرَوۡنَهَاۖ وَأَلۡقَىٰ فِي ٱلۡأَرۡضِ رَوَٰسِيَ أَن تَمِيدَ بِكُمۡ وَبَثَّ فِيهَا مِن كُلِّ دَآبَّةٖۚ وَأَنزَلۡنَا مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَأَنۢبَتۡنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوۡجٖ كَرِيمٍ

10. ሰማያትን የምታዮዋት ምሰሶ ሳያደርግላት ፈጠረ:: በምድርም ውስጥ በእናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለ:: በእርሷም ላይ ከተንቀሳቃሽ ነገሮች ሁሉ በተነ:: ከሰማይም ውሃን አወረድን:: በእርሷ ውስጥ ከመልካም ዓይነት ሁሉ አበቀልን:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 31

هَٰذَا خَلۡقُ ٱللَّهِ فَأَرُونِي مَاذَا خَلَقَ ٱلَّذِينَ مِن دُونِهِۦۚ بَلِ ٱلظَّٰلِمُونَ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ

11. ይህ ሁሉ የአላህ ፍጡር ነው:: እነዚያ ከእርሱ ሌላ ያሉት ምንን እንደ ፈጠሩ እስኪ አሳዩኝ:: በዳዮች በእውነት በግልጽ ጥመት ውስጥ ናቸው:: info
التفاسير: