ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

external-link copy
93 : 2

وَإِذۡ أَخَذۡنَا مِيثَٰقَكُمۡ وَرَفَعۡنَا فَوۡقَكُمُ ٱلطُّورَ خُذُواْ مَآ ءَاتَيۡنَٰكُم بِقُوَّةٖ وَٱسۡمَعُواْۖ قَالُواْ سَمِعۡنَا وَعَصَيۡنَا وَأُشۡرِبُواْ فِي قُلُوبِهِمُ ٱلۡعِجۡلَ بِكُفۡرِهِمۡۚ قُلۡ بِئۡسَمَا يَأۡمُرُكُم بِهِۦٓ إِيمَٰنُكُمۡ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ

93. የጡርን ጋራ ከበላያችሁ በማንሳት (በተውራት ሕግ እንደትሰሩ) ቃል ኪዳናችሁን በያዝን ጊዜ (የሆነውን አስታውሱ):: «የሰጠናችሁን በጽናት ያዙ:: ያልነውንም ስሙ።» አልን:: «ሰማን ግን አመጽን» አሉ:: የወይፈኑም ውዴታ በክህደታቸው ምክንያት በልቦቻቸው ውስጥ ገብቷል:: «ትክክለኛ አማኞች እንደሆናችሁ እምነታችሁ የሚያዛችሁ ነገር የከፋ ነው።» በላቸው። info
التفاسير: